
ትላንት (May 15) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አበጥር ወርቁ በተባለ የአማራ ብሔር ተወላጅ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግፍ ተመልክተናል፡፡ ይህ ከመሆኑ ከአንድ በፊት ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ527 በላይ አባወራዎች በድምሩ 2000 ከሚሆኑ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅለዋል፡፡
እነዚህ “ሕገ ወጥ ናችሁ” በሚል ሰበብ ተዘርፈውና ተደብድበው የተፈባቀሉት አማራዎች ህጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው ናቸው፡፡ በባለቤትነት ለሚያስተዳድሩት መሬት በአግባቡ ግብር ይከፍላሉ! በፎቶው የሚታዩት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮች ባህርዳር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሶስት አባውራዎች ናቸው።
እነዚህ ሰዎች ያለ ምንም መነሻ ምክንያት ከመሬታቸው አልተፈናቀሉም፣ በግፍ አልተገደሉም፡፡ ከዚህ በስተጀርባ በጥላቻና ማንአለብኝነት የናወዙ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ሃላፊዎች እጅ አለበት፡፡ ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሱት አባወራዎች በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ ከመፈናቀላቸው በፊት ለምሳሌ የበሎ ዲዴሣ ቀበሌ ሃላፊ የሆነው አቶ ንጉሱ ጀርሞሣ በቀን 16/07/2010 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ መሠረት እስከ መጋቢት 30/2010 ዓ.ም በአከባቢው የሚኖሩ አማራዎች ንብረታቸውን ሸጠው ወይም ጥለው እንዲወጡ አዝዟል፡፡
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚኖሩ አማራዎችን ያለ አግባብ እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ የሚያደርጉት እንደ አቶ ንጉሱ ያሉ የቀበሌ ሃላፊዎች አይደሉም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ በወረዳ፥ ዞን፥ ክልል፥ እንዲሁም በፌደራል ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ሃላፊዎች እጅ አለበት፡፡ ከታች እስከ ላይ ያሉት የመንግስት ሃላፊዎች ለአማራ ህዝብ ባላቸው ሥር-የሰደደ ጥላቻ ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ አማራዎችን በማፈናቀልና በመግደል ተሳታፊ ባይሆኑ እንኳን አማራዎች ለሚያሰሙት ብሶትና ቅሬታ ግድየለሽ መሆናቸው እርግጥ ነው፡፡ ላለፉት 27 አመታት በኦሮሚያ፥ ደቡብ፥ ጋምቤላ፥ ትግራይ፥ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአማራ ብሔር ተወላጆች ሲገደሉና ሲፈናቀሉ ማስቆም ይችሉ ነበር፡፡
ዛሬ ላይ ከ2000 በላይ አማራዎች ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉት፣ አበጥር ወርቁ በተባለው ግለሰብ ላይ አሰቃቂ ግፍ የተፈፀመው ትላንት ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው የማያዳግም እርምጃ ባለመወሰዱ ነው፡፡ባለፈው የሚያዚያ ወር አማራዎች ከክልሉ የተፈናቀሉት መጋቢት ላይ የበሎ ዲዴሣ ቀበሌ ሃላፊ የሆነው አቶ ንጉሱ ጀርሞሣ በፖሊስ ለፍርድ ባለመቅረቡ ነው፡፡ አቶ ንጉሱ በአከባቢው የሚኖሩ አማራዎች እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ የሚያደርገውን ትዕዛዝ ያስተላለፈው የቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል የርዕሰ መስተዳደር እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ለፍርድ ባለመቅረባቸው ነው፡፡
የቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል የርዕሰ መስተዳደር እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ጂሬኛ በዚህ አመት የጥቅምት ወር (እ.አ.አ በ04/03/2017 ዓ.ም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የትግራይ ክልል ተወላጆችን 600ሺህ ብር እና የአውሮፕላን ትኬት ሸፍኖ ልኳቸዋል”። በክልሉ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች በተመለከተ ደግሞ “በሕገ ወጥ መንገድ የያዙት መሬት እንዲለቁና ወደ መጡበት ክልል እንዱመለሱ ተደርጓል” ብለው ነበር፡፡ ይህ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ህወሓት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ በደቡብ አፍሪካ የወደቀው የአፓርታይድ ስርዓት ዛሬም ድረስ ኢትዮጲያ ውስጥ በተግባር እንዳለ በመንግስት ሚዲያ ላይ በይፋ ተናግሮ ማንም ምንም አላለውም፡፡
አቶ ሰለሞን ጂሬኛ የቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል በአማራዎች ላይ ተግባራዊ ያደረገውን አድልዎና ግፍ በይፋ በራሱ አንደበት ያረጋገጠበት ምክንያት ምንድነው? አጭርና ግልፅ፣ መንግስታዊ ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ የፈለገውን አሰቃቂ ተግባር እንዲፈፅም ይፈቅድለታል፡፡ ምክንያቱም በህወሓት መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ዓላማና ግቡ የአማራን ህዝብ መበቀል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ “የአማራ የበላይነት፥ ነፍጠኛ፥ ትምክህተኛ፥ የድሮ ስርዓት ናፋቂ፥…” እያለ በአማራ ህዝብ ላይ ዘወትር ጥላቻ ይሰብካል፡፡
በዚህ መሠረት በቂም-በቀል የታወሩ ሰዎች በኦሮሚያ፥ ደቡብ፥ ጋምቤላ፥ ትግራይና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች በሚገኙ አማራዎች ላይ በማንአለብኝነት አሰቃቂ ግፍና በደል ሲፈፀሙ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ሃላፊዎች ነገሩን በቸልታና ግድየለሽነት እንዳልሰማ-እንዳላየ ሆነው ያልፉታል፡፡ በመሆኑም በአማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ በደልና ግፍ እንዲፈፀም በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ፈቅደዋል፡፡ በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ የሚፈናቀለው ሆነ የሚገደለው በመንግስት ፍቃድ ነው!
ስዩም ተሾመ
ሰው ከመሆን ደረጃ ለምን ወደ ዘር ወርድን?
የትኛው ይቀድማል?ሰውነት ወይስ ትግሬነት/ኦሮሞነት አማራነት/ሃድያነት/ ወዘተ?
የአማራ ሕዝብ መከራ ምንጩ በእውነት ምንድነው?
መከራ ያበዙበትን እነዚህን ሰዎች በእውነት ምን አድርጓቸው ነው?
በእውነት አማራ በአማራነቱ በትግራይ፣ በኦሮሞና በሌሎች ላይ የሠራው ግፍ አለ?
አማራና አማርኛ ለምን በራሳችን ወገኖች ተጠላ?
የሰማሁትን እንካችሁ፡
1)አንድ የኤርትራ ሕጻን ስታድግ ምን መሆን ትሻለህ ሲባል
የጦር አውሮፕላን አብራሪ! ለምን እሱን ሥራ መረጥክ?
ኢትዮጵያያን ለመደብደብ ብሎ እርፍ!
በወላጆቹና በሰፈሩ ቂመኛ ሰዎች ሲባል የሰማውን!!
2) አንድ ለጋብቻ የደረሰ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ፡
አብራው ቤ/ክ የምታመልክን የወለጋ ወጣት ሴት
ለጋብቻ ከልቡ በእውነት ይጠይቃታል፤
አንተን በፍጹም አላገባሃም ብላው እርፍ!
ምነው???? ሲላት
አማራ ስለሆንክ ነው።
/ኢሕአዴግ በገባ ከ3 ዓመት በኋላ የተፈጸመ እውነት/
ከዚህ የበለጠ ከሰውነት ደረጃ መውረድ ምን አለ????
ኧረ እናስተውል???ምነው ሰው ሰው መሆኑን እረሳ??
ልጄ ሰለሞን ሆይ!
ሰው ሁን!!!
/1ኛ ነገሥት 2፡1-4/
Therefore, are we really CHRISTIAN ?????
Eunteu Yeneger