ኢህአዴግ ውስጥ ስለተደረገው አመራር ለውጥና ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ያደረገው በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ለመግታት እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ በሌላ በከል አንዳንድ የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች የአመራር ለውጡ የተካሄደው በተለመደው የፓርቲው ደንብና ስርዓት እንደሆነና የአዲሱ ሊቀመንበር ምርጫ በአባል ድርጅቶች የጋራ መግባባት የተመሠረተ እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ ነገር ግን፣ ሁለቱም አመለካከቶች በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አስተያየቶች፤ አንደኛ፦ የለውጡን መነሻ ምክንያት በጥልቀት ካለመረዳት፣ ሁለተኛ፦ የአመራር ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ በግልፅ ካለመገንዘብ የመነጩ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ እንዲያደርግ … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዓቢይ እና ህወሓቶች፡ ለይቶ ማሰር ወይስ አብሮ መሥራት?
ethnic politics
ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው
አባቶች “ሥራ ለሠሪው እሾህ ለአጣሪው” እንዲሉ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት ዘረኝነትን ፖሊሲው ያደረገው ህወሃት ለሃያሰባት ዓመት ኮትኩቶና ውሃ እያጠታ ያሳደገው ዘረኝነት ወይም የጎሰኝነት ገመድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ መተንፈሻ እያሳጣው ነው። ሰው በሰውነቱ ከዚያም ዝቅ ሲል በዜግነቱ ወይም በኢትዮጵያዊነቱ መከበር ሲኖርበት፣ ህዝቡን በጎጥ አጥር ከትቶ እርስ በርሱ እንዲጋደል ወያኔ ሌት ተቀን ሠርቷል። ለዘመናት የቆየው ኢትዮጵያዊ ትስስርና ባህሉ ህዝቡን በአንድነት ቢያቆየውም ብዙ ዜጎች በማንነታቸው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተሰደዋል፣ ተንገላትተዋል። ጊዜ ይውሰድ እንጂ ኢትዮጵያውያን የወያኔ ተንኮል ከመረዳት አልፈው በቃህ በሚል ፍጻሜውን ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዓለምን ያስደነገጠው የሩዋንዳ እልቂት ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸውን ሩዋንዳውያን ቅኝ … [Read more...] about ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው