• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው

December 13, 2017 12:34 am by Editor Leave a Comment

አባቶች “ሥራ ለሠሪው እሾህ ለአጣሪው” እንዲሉ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት ዘረኝነትን ፖሊሲው ያደረገው ህወሃት ለሃያሰባት ዓመት ኮትኩቶና ውሃ እያጠታ ያሳደገው ዘረኝነት ወይም የጎሰኝነት ገመድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ መተንፈሻ እያሳጣው ነው። ሰው በሰውነቱ ከዚያም ዝቅ ሲል በዜግነቱ ወይም በኢትዮጵያዊነቱ መከበር ሲኖርበት፣ ህዝቡን በጎጥ አጥር ከትቶ እርስ በርሱ እንዲጋደል ወያኔ ሌት ተቀን ሠርቷል። ለዘመናት የቆየው ኢትዮጵያዊ ትስስርና ባህሉ ህዝቡን በአንድነት ቢያቆየውም  ብዙ ዜጎች በማንነታቸው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተሰደዋል፣ ተንገላትተዋል። ጊዜ ይውሰድ እንጂ ኢትዮጵያውያን የወያኔ ተንኮል ከመረዳት አልፈው በቃህ በሚል ፍጻሜውን ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው።

ዓለምን ያስደነገጠው የሩዋንዳ እልቂት ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸውን ሩዋንዳውያን ቅኝ ግዥዎቹ  በፊት ገጽታ፣ በፍንጫ ቅርፅ ልዩነት ብቻ ከፊሉን ቱትሲ ቀሪውን ሁቱ ብለው በመከፋፈል መታወቂያ ካወጡላቸው በሁዋላ አንድ እንዳይሆኑ ያስፋፉት የልዩነት ቅስቀሳ ነበር የሚሊዮኖችን እልቂት ያስከተለው። ጎረቤት ሶማልያ ህዝብዋ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ባህል እያለው ሰላሳ ዓመት የተጠጋ ብጥብጥ፣ መጋደል፣ መሰደድና እንደሃገር ያለመኖር ጦስ ውስጥ የገባው የጎሳ ልዩንትን እንደወያኔ ያሉ የስልጣን ጥመኞች ስለአጦዙት ነው። የዘር ፖለቲካ አጥፊ ለመሆኑ ብዙ የዓለም አገራትን ምሳሌ ማቅረብ የሚያስፈልገን አይደለም። ከየቀየው የተፈናቀሉ፣ ገደል የተጣሉና የተዘረፋ አማሮች፣ ኦሮሞዎች፣ ሲዳማዎች፣ በቅርቡ የተፈናቀሉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ኦሮሞዎች፣ ዛሬ በየዩኒቨርስቲው የሚገደሉ ኦሮሞ፣ አማራና ትግሬ ወጣቶች ምስክር ወይንም ትምህርት አይሆነንም ወይ? በዚህ ግድያ፣ በዚህ ስደት፣ በዚህ መፈናቀል ማን ነው የሚደሰትው? ዘረኝነትን ከሚያቀነቅነው ከይሲ ወያኔ በቀር!

ወያኔዎች ኢትዮጵያውያንን በመታወቂያቸው ላይ እያስገደዱ ብሄራቸውን ሲያስሞሉ ህዝቡ እንደሩዋንዳ እየተነጣጠለ እንዲጫረስ ነበር። የኦሮምያ አስተዳደር መታወቂያ ላይ የሚሰፍረው ብሄር የሚለው እንዲቀር በማድረጉ ሊመሰገን ይገባል።

የትምህርት ምኩራብ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች ለጋ ወጣቶች ከተለያዩ የአገራቸው ልጆች ጋር እንዳይገናኙ በዘር ሸንሽነው ያደራጁት ይህንን ልዩነት ይዘው እንዲያድጉና በጥላቻ ተለያይትው ለመገዛት እንዲመቹ ነበር። የወጣቶችን ትኩስ መንፈስና ስሜት ተጠቅመው የዘሩት ዘር ሙሉ በሙሉ ባያፈራም የሚያሳዝኑ ጉዳቶች ማድረሳቸው አልቀረም።በነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሽማግሌው የስብሃት ነጋና የዘመዶቹ ልጆች፣ የአባይ ፀሃዬ፣ የስዩም መስፍን፣ የአርከበ እቁባይ፣ የጌታቸው አሰፋና የሌሎችም ዘራፊ ወያኔ ልጆች የሉም። እነሱማ አባቶቻቸውን ተክተው ልጆቻችንን ሊገዙ በቻይናና በምዕራቡ ዓለም ትልልቅ ትምህርት ቤቶች በተዘረፈ የህዝብ ሃብት ይማራሉ። ከፊሎችም በሀሺሽ ናውዘዋል።

በየዩኒቨርስቲና ልዩ ልዩ ተቋማት ያላችሁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሆይ እንደ እናንተ ባሉ ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ እጃችሁን አታንሱ! ጥላቻን የዘራው፣ ተስፋችሁን ያጨለመው የወያኔ ዘረኛ ስርዓት ነው። ይህ እንዲያበቃ የምታደርጉትን ትግል አቅጣጫው እንዲቀይር በተዘጋጀ ወጥምድ ውስጥ አትግቡ።

ህወሃቶች ኢትዮጵያውያን በየጎጣቸውና ጠባብ መንደራቸው ግርግም እንደገባ ክብት በአካባቢያቸው ተወስነው፣ የየክልሉ የወያኔ አሽከሮች ተሹመውባቸው፣ እንዳይንቀሳቀሱ ሲያግዱ ወያኔዎችና ቤተሰቦቻቸው መላ ኢትዮጵያን የመዝረፍ መብት ተጎናፅፈዋል። ለኦሮሞው አጥንቱን ከስክሶ ያስጠበቃት ኦጋዴን እንዳይኖርባት ሲገደልና በግማሽ ሚሊዮን የሚቆጠረው ሲፈናቀልባት ለህወሃት መኳንንትና ከሲአድባሬ ተባብረው ለወጉን ባለስልጣናት የግላቸው ናት። አማራው ከጠላት እየተዋደቀ እስከ ኦሜድላ ላስጠበቀው አገሩ ለጉቫ፣ ለዳንጉር፣ ለፓዊ ባዕድ ሆኖ የባንዳ የሹምባሽ ልጅ መሬቱንና ማዕድኑን ከአድዋ መጥቶ ይዘርፋል፤ አሶሳ ለኦሮሞው ውጭ አገር ሆና ይፈናቀልባታል፤ ጋምቤላን አኝዋኩ ጠብቆ መቆየቱ ሃጢያት ሆኖበት በመቶዎች ተገድሎ የተረፈው ተባርሮ የህወሃት ባለስልታናትና ዘመዶቻቸው በብቸኝነት (እንዳጋጣኢ ሆኖ ብለዋል) ኢንቭስተር ሆነውበታል። የምክር ቤት አባልም ናቸው። ጉራጌ ሠርቶ ያሳደጋት አዲስ አበባ ባዕዱ ሆና ከመርካቶ ተባርሮ እነሃጎስ ሱቆቹን የነጠቁት መሆኑን መናገር ሀቅ አንጂ ዘረኝነት አይደለም።

ለአንድ ኦሮሞ እንኳን ኦሮምያ ኢትዮጵያ ትጠብበዋለች። ልክ ለወያኔና ለቤትሰቦቻቸው እንደጠበበቻቸው። ለአማራው፣ ለጉራጌው፣ ለሲዳማው፣ ለወላይታው …ለሁሉም እንኳን አባቶቻቸው ተዋድቀው ያቆዩአት ኢትዮጵያ ይቅርና አፍሪካም፣ ዓለምም ይጠብባቸዋል። ቻይናና ወያኔ ከነዘመዶቹ የሚፏልልባት ኢትዮጵያ እንዴት ለዜጎቿ አትሆንም? ሁሉም በጠባብ የዘር አጥር ውስጥ ታስሮ ወያኔና አገልጋዮቹ መላ አገሩቱን ሲዘርፉ ለምን ይፈቀዳል?

የኦሮሞ ቄሮዎች፣ የአማራ ፋኖዎች የጠየቁት “እናንተ ማን ናችሁና ነው ሌሎችን አስራችሁ አገር የምትዘርፉት?” እያሉ ነው። በዚህም ሳያበቃ ለሶስት ዓመት በተካሄደው ህዝባዊ ትግል የተደናገጡትና የጌቶቻቸው አልጠረቃ ባይነት ያሳሰባቸው፣ አገልጋይነታችውም የሰለቻቸው የኢህአዴግ አባላት የህዝባቸውን ሮሮ ከመስማት አልፈው ወያኔን እየተገዳደሩ ነው። ለህወሃት ወፍራም ድመቶች በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ ወዘተ እንደወትሮው መዝረፍ ይቅርና መንቀሳቀስም ይክብዳቸዋል። በዚህም አያበቃም፤ የወያኔን አገዛዝ ህዝቡ በቃህ ስለአለው ፍፃሜው ቅርብ ነው።

አርባ ኪሎሜትር ድንበር አልፎ የገባን ሱዳን ተመለስ ማለት የፈራው ወያኔ እስክርቢቶ ብቻ የያዙትን የዩኒቨርስቲ ልጆች በመግደልና በመቀጥቀጥ የሰራዊቱን ሃያልነት ለማስመስከር ይታትራል። “በሸንጎ ቢረታ ሚስቱን ገብቶ መታ” እንዲሉ። ህወህት የዘራው የዘረኝነት መርዝ እንዲጋተው ይገደዳል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ጊዜ በቆየ የአብሮነት ባህሉ ዘረኝነትን አርክሶታልና። ወያኔ በሰፈረው ቁና ይሰፈርበታል።

ከአንተነህ መርዕድ (amerid2000@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Ethiopia, ethnic politics, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule