• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

August 26, 2018 10:51 am by Editor Leave a Comment

ገዱ አንዳርጋቸው በምሁራን መድረክ ያድረጉት የመክፈቻ ንግግር

  • ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
  • የተከበራችሁ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች!

እንኳን ወደ አማራ ክልል መዲና ውቢቷ ባህርዳር ከተማ በሠላም መጣችሁ!

ከነገሬ ሁሉ በማስቀደም የአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ የጐደለውን ትሞሉለት ዘንድ ምክራችሁን እና የሙያ ድጋፋችሁን በመሻት ለልጆቹ ያደረገውን ይህን ታሪካዊ ጥሪ ያለምንም ማቅማማት ተቀብላችሁ እዚህ በመካከላችን በመገኘታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ።

በረጅሙ የሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ ህዝብ በስልጣኔ፣ በተለይም በመንግስት አስተዳደር፣ በታሪክ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በአርበኝነት ተጋድሎ እንዲሁም በኢኮኖሚ ዕድገት ለሃገር ያበረከተው ድርሻ ትልቅና አይረሴ ቢሆንም ያለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት በዘመናዊ ትምህርት የጐለመሰው የክልሉ ተወላጅ ቁጥሩ ከፍ እያለ የመገኘቱን ያክል ተሣትፎው ግን እየቀዘቀዘ መጥቷል።

ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ አሳታፊ /አካታች/ የመንግስት አስተዳደር አለመኖሩና በመንግስት አመራር ውስጥ “እኔ አውቅላችኋለሁ” የሚል ደዌ ተጠናውቶን መቆየቱ ነው። ይህ ጉዳይ በሁሉም የሙያ ዘርፍ አንቱ የሚባሉና ለሃገራችንም ሆነ ለዓለም የተረፉ ምርጥ ምሁራን ለፈለቁበት የአማራ ህዝብ “የዐባይን እናት ውሃ ጠማት” እንደሚሉት አይነት ሆኖበት ቆይቷል። በመመካከር ፈንታ መወቃቀስ፣ በመደጋገፍ ፈንታ መገፈታተር፣ በፍቅር አብሮ መሥራት እና አብሮ መብላት የአባት አደር ሆኖ ሳለ የአንድነትና ወንድማማችነት ጽዩፋን እየሆን እንገኛለን።

ለዚህ ሁሉ ችግር ተወቃሽ ባይጠፋም ወቃሽ ሆኖ መቅረብ የሚችለው ግን ትልቁ የአማራ ህዝብ ብቻ በመሆኑና የህዝባችን ዐቢይ ፍላጐትም ሁላችንም የምንችለውን ያክል ሠርተን ከችግር እንድናወጣው ሥለሆነ ዛሬ በመካከላችሁ የቆምኩት ይህንኑ ጥሪ ለማሥተላለፍ ብቻ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች !!

መማር ማለት በርካታ መፃህፍትን ውጦ መቀመጥ ብቻ አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነ መማር በዩኒቨርሲቲ በሚሰጥ የሊቅነት ማረጋገጫ ወረቀት ብቻ ሊገለጥ አይችልም። በእኔ እምነት መማር የህዝብን ህመም አብሮ ታሞ መፈወስ መቻል ነው።

ትምህርት የተጨነቀን ህዝብ ከችግር ለማውጣት የሚያስችል መሣሪያ ሆኖ ካልተገኘ ልሂቃን ሲፈልጉት ብቻ የሚጠቀሙበት ተከቶ የተቀመጠ ትርፍ ሃብት ይሆናል። የክልላችን ህዝብም ይሁን ሃገራችን ዘመናትን ያስቆጠሩ በርከት ያሉ ችግሮች አሉባቸው። ችግሮቹን መንግስት ብቻውን ታግሎ ሊፈታቸው እንደማይችል አሣምረን ተረድተናል። ዛሬ የሁላችሁንም በር ለማንኳኳት ስንወስን ሃገር በዕውቀት እንጂ በልበ ብርሃንነት እንደማይመራ ተገንዝበን ነው። ሃገር በመገንባት ሂደት ውስጥ ህዝብ፣ መንግስት እና ባለሃብቶች ትልቅ ድርሻ አላቸው። ይሁን እንጂ ሁሉም በዕውቀትና በጥበብ ካልተሳሰሩና ካልተደጋገፋ ወንዝ መሻገር አይችሉም።

ምሁራን ያለችውን እውቀት ወደ ተጨባጭ ጠቀሜታ መቀየር የሚችሉት ብቻቸውን በመጓዝ አይደለም። ከመንግስት ጋር አብሮ መሥራትም ፖለቲከኛነት አይደለም። ይልቁንም ዕውቀትን ወደ ህዝብ ለማድረስ ዋነኛ ድልድይ ከሆነው አካል ጋር አብሮ መስራት ነው። የፖለቲካ ሣይንስ ምሁራን እንደሚናገሩትም የአንፃራዊነት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከፖለቲካ ፈፅሞ ነፃ የሆነ ሰው የለም።

ስለሆነም ተገቢነት የሌለውን የፖለቲካ ሃሜት በመፍራት ወይም ይህንኑ ሰበብ በማድረግ መራራቅ ለማናችንም አይበጀንም። ተራርቀን አይተነዋል፤ ዘመን ተሻጋሪ የልማት ገድል መፈፀም የሚያስችል እውቀትና ችሎታ እያለን “የጋን መብራት” ከመባል አላለፍንም። መለያየት፣ ፊት መዟዟር፣ በአለፈው ታሪካችን መወቃቀስም ሆነ የይስሙላ መቀራረብ ይብቃን።

የአማራ ህዝብ ችግር የሚፈታው ከልብ የመነጨ ፍቅር፣ አንድነት፣ እውነተኛ እህትማማችነትና ወንድማማችነት በመካከላችን ሲገነባ ነው። አማራ ክልል ፀጋው ያልተጓደለበት፣ ሁሉም ዘርፍ እንስራ ብንል ልማትን ለማምጣትና ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ወሳኝ የሚባል የሃብት መሠረት ያለው ክልል ነው። በእስካሁኑ ጉዟችን በገባን ልክ ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ ያቅማችንን ተፍጨርጭረናል። ያም ሆኖ ያስመዘገብነው ውጤት ህዝባችን ሙሉ በሙሉ ከችግር ያላቀቀ አይደለም። የምናደርገው ሩጫ ብልሃት ቢጨመርበት፣ በዕውቀት ቢደገፍ ድህነት ከክልላችንና ከሃገራችን የሚቆይበት እድሜ በብዙ እጥፍ ሊያጥር ይቻል እንደነበር አሣምረን እንገነዘባለን።

የምናደርግላችሁ ጥሪ የይስሙላ አይደለም፣ ታሪካዊ ግዴታችሁ የሆነውን ይህን የአብረን እንስራ የጥሪ ደወል ሠምታችሁ በአንድነት በመሠባሰብና በተግባር አብሮ ለመራመድ ለቆረጣችሁ ምንጊዜም ከጐናችሁ በመሆን ለዚህ ተግባር የሚያስፈልገውን የመንግስት አገልግሎት በቀናነት ለመስጠት ዝግጁ ነን። ይህ አጋጣሚ ለእናንተ ግዴታ አይደለም። ይልቁንም ለረጅም ጊዜ ስትመኙት የነበረ ዕድል እንደሆነ አውቃለሁ። ዕድሉን መስጠት እና ሁኔታውን ማመቻቸት የመንግስት ድርሻ ቢሆንም መጠቀም ግን የእናንተ ብቻ ነው። ለመተባበርም ታሪክ ለመቀየርም እኔና እናንተ ከማንም አናንስም። ሳናጣ የጐደለብን፣ ሣይነጥፍ የደረቀብን፣ እያለን እንደሌለን የምንቆጠር ደካሞች አይደለንም።

እኛ የጠፋውን የማልማት፣ የጐበጠውን የማቃናት፣ የተቋጠረውን የመፍታት፣ የተወሳሰበውን መልክ የማስያዝ ብቃትና ተሠጥኦ ያለን ልዩ ልጆች ነን። አንድ ሆነን በመስራት ከእኛ አልፈን ለሃገርም የሚበቃ ትሩፋት መፍጠር እንችላለን። እነሆ መንገዱ ተከፍቷል፣ የጥላቻ መጋረጃውም ተቀዷልና በመሃሉ በመመላለስ ቤታችንን ቤት እናድርገው።

በድጋሜ አክብራችሁን ስለተገኛችሁ እያመሰገንኩ በዚህ አጋጣሚ ይህ ታሪካዊ የምሁራን መማክርት ጉባዔ እንዲቋቋም ምሁራን ለክልሉ ህዝብ ዕድገት የቻሉትን ሁሉ እንዲሰሩ በሚያዚያ ወር በዚሁ በባህር ዳር ከተማ ተገናኝተው ታሪካዊ መሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ምሁራንና በዚሁ ጉባዔ በተላለፈው ውሣኔ መሠረት የመማክርት ጉባዔ ለማዘጋጀት አስፈላጊ የሆኑ መነሻ ጽሁፍ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ እና ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ትክክለኛ የሆነውን የምሁራን ትጋት በአሣዩን እና የአንድነት ተምሣሌት በመሆን ሌት ተቀን ለሰሩ የኮሚቴ አባላት ያለኝን ምስጋና ለማቅረብ ቃላት የለኝም። በተጨማሪም ከዚህ መማክርት ጉባኤ መክፈቻ ቀን ቀደም ብሎ በሙያቸው በመደራጀት የክልሉን የግብርና ልማት ዘርፍ ለማገዝ ሥራ ለጀመሩ የግብርና ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ!!!
ምንጭ፦ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ፌስቡክ ገፅ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: andm, gedu, Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule