ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!