• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጠባብነት እና ትምክህት

May 20, 2018 06:07 am by Editor 3 Comments

ከ2 አመት በፊት፦ ጠባብነት እና ትምክህት

ኢህአዴግ እንደ ፓርቲና መንግስት የችግሮች ሁሉ መንስዔ አድርጎ የሚወስደው የጥገኝነት አስተሳሰብና ተግባራትን ነው። ለህዝቡ ሰላም እና ለፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ውስጥ፡- ጠባብነት እና ትምክህተኝነት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቃላት በመንግስት ድክመት ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ተጠያቂ (externalize) ለማድረግ ነው።

በመሠረቱ “ትምክህተኛ” የሚለው እሳቤ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በባህላቸውና በታሪካቸው ላይ ያላቸውን የራስ መተማመን ስሜት የሚሸረሽር ነው። በዚህ መልኩ የሚደረገው ተፅዕኖ በአማራ ልሂቃን ላይ የማንነት ቀውስ (identity crisis) ይፈጥራል። በዚህ መሰረት፣ አንድ ሰው በአማራነቱ ብቻ “ትምክህተኛ” እየተባለ ታሪኩና ማንነቱ እንደ ጥፋት ሲቆጠር በውስጡ የብሔርተኝነት ስሜት ያቆጠቁጣል።

በተመሣሣይ “ጠባብ ብሔርተኛ” የሚለው እሳቤ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለውን ድርሻ የሚያንኳስስ፤ በሀገሪቱ አንድነት ላይ ያለውን የምሶሶነት ሚና ወደ አንድ ግንጣይ ቅርጫፍነት የሚያሳንስ ነው። በሀገሪቱ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ የሚገባውን መጠየቁ እንደ ጥፋት ተቆጥሮ “በጠባብነት” ሲፈረጅ በኃይል ሚዛኑን ውስጥ የሚገባውን ድርሻ ለመያዝ በራሱ መንቀሳቀስ ይጀምራል።

ከላይ በተገለፀው መሠረት ላለፉት 25 አመታት ኦሮሞ “ጠባብ ብሔርተኛ” እየተባለ በሀገሪቱ አንድነት ውስጥ የሚገባውን ጥቅምና ኃላፊነት ተነፍጎ ስለቆየ የፖለቲካ አሰላለፉን በሂደት ከብሔርተኝነት ወደ “የኢትዮጵያ አንድነት” እየቀየረ መጥቷል። አማራ ደግሞ “የትምክህት አንድነት” በሚል እንደ ብሔር የሚገባውን ጥቅምና ኃላፊነት ተነፍጎ ስለቆየ የፖለቲካ አሰላለፉን በሂደት ከአንድነት ወደ “አማራ ብሔርተኝነት” እየቀየረ መጥቷል። በዚህ የሽግግር ሂደት የሁለቱ ሕዝቦች ጥያቄ ከተቃራኒ ጫፎች ወደ መሃል በመምጣት አሁን ላይ ያልተጠበቀ ጥምረት ፈጥሯል።

ይህ አንደ ቀድሞው በሁለት ተቃራኒ ፅንፈኞች መካከል የተፈጠረ ጥምረት አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ሁለቱም ሕዝቦች በሆኑትና በሚገባቸው ልክ ጥቅምና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በሚያደርጉት የጋራ እንቅስቃሴው የተፈጠረ ጥምረት ነው። በመሆኑም፣ የኦሮሞና አማራ ህዝቦች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ረገድ እየታየ ያለው ጥምረት በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አስችሎታል።

ከ2 አመት በኋላ፦ ጠባብነት እና ትምክህት

“ኦሮማራ” በሚል የሚታወቀው የሁለቱ ህዝቦች ትብብርና አንድነት በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በዋናነት በኦህዴድና ብአዴን መካከል የተፈጠረውን ጠንካራ ጥምረት መጥቀስ ይቻላል። በሀገራችን ፖለቲካ መሠረታዊ ችግር የነበረው የህወሓት የበላይነት እንዲያከትም በማድረጉ ሂደት የማይተካ ሚና ተጫውቷል። ስለዚህ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት የቻሉት በዚህ ጥምረት አማካኝነት ነው።

ስለዚህ ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣበት ግዜ ጀምሮ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ከሚገቡ ተግባራት ጠባብነት እና ትምክህት ከመንግስት መዝገበ-ቃላት ውስጥ መሰረዝ ነው። ምክንያቱም፣ አንደኛ፦ የእነዚህ ቃላት አጠቃቀም የኦሮሞና አማራ ህዝቦችን የእኩልነት ጥያቄ ለማፈን፥ ለማጣጣል፥ ለማንኳሰስና ተቀባይነት እንዳያገኙ ለማድረግ ያለመ ነው። ሁለተኛ፦ በኢህአዴግ የአመራር ለውጥ እንዲመጣ የቻለው እነዚህን አፍራሽ ቃላትና አመለካከት በመቃወም በተፈጠረ የኦሮማራ ጥምረት አማካኝነት ነው።

በመሆኑም ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ ከተመረጠበት ዕለት አንስቶ ጠባብነት እና ትምክህት የሚሉት ቃላት ከስነ-ምግባር ሆነ ነባራዊ እውነታ ያፈነገጡ እንደሆኑ ታሳቢ በማድረግ ከመዝገበ-ቃላት ውስጥ መሰረዝ ነበረባቸው። ነገር ግን፣ ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ ከሁለት ወራት በኋላ እነዚህ ቃላት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል። ለምሳሌ የፌዴራል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት 27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓልን አስመልክቶ ባዘጋጀው የመወያያ ሰነድ ላይ ጠባብነት እና ትምክህት የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸው ተገልጿል፦

በተጠቀሰው ሰነድ መሠረት የፌዴራል ስርዓቱ የመጀመሪያ ተግዳሮት “ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አለመዳበር” እንደሆነ ይገልፃል፦

“ብዝሃነትን በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችል የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ በሚፈለገው ደረጃ ባለመዳበሩ ሳቢያ ጥበትና ትምክህት በብሄር ካባ የግል ጥቅም ማሳደጃ መሆን በመጀመራቸው የፌዴራል ስርዓታችን የመጀመሪያ ተግዳሮቶች ሆነዋል። የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነትና የዴሞክራሲያዊ አንድነት ጠላት የከረረ ብሔርተኝነት ነው። የከረረ ብሔርተኝነት ትምክህትን ወይንም ጠባብነትን ይወልዳል። ትምክህት በገዥ መደብነት በመሰለፍ የሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች ማንነት በስመ ኢትዮጵያዊነት ካባ የሚንድ አስተሳሰብ ነው። ጠባብነት ደግሞ ተስፈኛ የሆነ የገዥ መደብ አስተሳሰብ ሲሆን ጭቆናን ምክንያት በማድረግ ያለአግባብ በሚሰጠው መፍትሄ የብሄሩ ገዥ መደብ የመሆን ፍላጎትን የሚያሳይ ነው። ሁሉም አስተሳሰቦች ፀረ እኩልነትና ፀረ ዴሞክራሲ ናቸው። እነዚህ አስተሳሰቦች ኢ-ምክንያታዊነትን በማጎልበትና በማሳደግ አንዱን ህዝብ በማቅረብ ሌላውን በማራቅ ፋሺስታዊ የዘር ፍጅትን የሚያመጡ አስተሳሰቦች ናቸው። በተለይም በአሁኑ ጊዜ ጥገኝነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት የጋራ አጀንዳቸው በመሆኑ ምክንያት ጠባብነትና ትምክህት በአንድነት የሚሰለፉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዓለማችን በከረረ ብሔርተኝነት የተነሳ በጀርመን እንዲሁም በ1990ዎቹ መጀመሪያ በጎረቤታችን ሩዋንዳ ለሚሊዮን ህዝቦች እልቂት ምክንያት ሆኗል።”

የፌዴራል ስርዓቱ ሁለተኛው ተግዳሮት “የልማታዊነት አስተሳሰብ የበላይነት አለመረጋገጥ” ሲሆን ለዚህም በመንስዔነት የተጠቀሱት ጠባብነትና ትምክህት ናቸው፦

“የፌዴራል ስርዓት ተግዳሮት ተደርገው ከሚወሰዱት መካከል ኪራይ ሰብሳቢነትና ውላጆቹ የሆኑት ትምክህትና ጥበት ናቸው። እነዚህ ሁለት ፅንፎች እርስ በርስ በመጓተት የአገራችንን የፌዴራል ስርዓት በመፈታተን ላይ ናቸው። የትምክህት ሃይሉ የቀድሞው አህዳዊ ስርዓት መመለስ አለበት፤ እኛ ካላስተዳደርነው “አንድነትና ኢትዮጵያዊነት” ሊኖር አይችልም እኛ አዋቂ ነን በማለት ኢትዮጵያዊነትን በሃይል ለመጫን የሚፈልጉ አካላት ናቸው።… ሌላኛው አካል ደግሞ አብረው የኖሩ ህዝቦችን ለመነጣጠል፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ፈጽሞ መስማት የማይፈልግ፣ አብሮ የመኖር ፈይዳ የማይታያቸው፣ ያለፈው ስርዓቶች አደረሱ የተባለውን በደል አሁን ላይ ያለው ትውልድ ለማወራረድ ህዝቦችን የሚያነሳሱ፣ ንጹሃንን በማጋጨት ወደ ስልጣን መሰላል መሰቀል የሚፈልጉ ናቸው። ሁሉም ፀረ ልማትና ዕድገት ሆነው በአንድ ጎራ ተሰልፈው ፌዴራላዊ ሥርዓቱን እየተፈታተኑት ይገኛሉ።”

ምንጭ፤ Ethiopian Think Thank Group by Seyoum Teshome

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: abiy, gedu, Left Column, lemma, oromara

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    May 22, 2018 09:03 pm at 9:03 pm

    ጎልጉሎች!እንዲያው ኣሰሱን ገሰሱን ያለ ጥናት፤ ኦሮሞ ጠባብ፤ ኣማራ ትምክህተኛ ብላችሁ፤ ድፍድፉን ኣቀረባችሁልን። ጥበት እንዴት ይመነጫል?መንስዔውስ? መፍትሄውስ? የሚለውን ማየት ተገቢ ነው። ትምክህትንም እንደዚሁ። ከላይ የቀረበው የዘንጋዳ ቂጣ፤ ጠላ ወይም ስዋ ወይም ጽራይ ወይም ጉሽ ሆኖ ኣልቀረበም። ልንጠጣው ኣልቻልንም። ኣብራራልን የምትሉኝ ከሆነ፤ ኣሰማምረዋለሁ።

    Reply
  2. ኪሮስ says

    May 24, 2018 04:27 pm at 4:27 pm

    ጎልጉሎችና ሙሉጌታ፣ ትግሬ ጠባብና ትምክህተኛ እንደ ሆነ ዘነጋችሁ!

    Reply
    • Mulugeta Andargie says

      May 25, 2018 05:19 pm at 5:19 pm

      እሱንማ እኔም አልክድም። ያልኩት ጎልጉሎች አብራራልኝ እንደማለት ድፍድፉን አቀረቡልን ነው!! ቂቂቂ!

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule