ከ2 አመት በፊት፦ ጠባብነት እና ትምክህት ኢህአዴግ እንደ ፓርቲና መንግስት የችግሮች ሁሉ መንስዔ አድርጎ የሚወስደው የጥገኝነት አስተሳሰብና ተግባራትን ነው። ለህዝቡ ሰላም እና ለፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ውስጥ፡- ጠባብነት እና ትምክህተኝነት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቃላት በመንግስት ድክመት ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ተጠያቂ (externalize) ለማድረግ ነው። በመሠረቱ “ትምክህተኛ” የሚለው እሳቤ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በባህላቸውና በታሪካቸው ላይ ያላቸውን የራስ መተማመን ስሜት የሚሸረሽር ነው። በዚህ መልኩ የሚደረገው ተፅዕኖ በአማራ ልሂቃን ላይ የማንነት ቀውስ (identity crisis) ይፈጥራል። በዚህ መሰረት፣ አንድ ሰው በአማራነቱ ብቻ “ትምክህተኛ” እየተባለ ታሪኩና ማንነቱ እንደ ጥፋት ሲቆጠር በውስጡ የብሔርተኝነት ስሜት … [Read more...] about ጠባብነት እና ትምክህት