• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የተንጋደደው የገዱ መልስ

February 6, 2026 03:05 pm by Editor Leave a Comment

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀድሞ ጭፍራቸውን ገዱ አንዳርጋቸው በፓርላማ በስም ጠርተው ለተናገሩት ገዱ መልስ ሰጥተዋል።

ይህ ጽሑፍ ዓላማ ያደረገው ለገዱ ምላሽ አስተያየት ለመስጠት አይደለም። ምክንያቱም የመጀመሪያና ትልቁ ስህተት ያለው ገዱ በጻፉት የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ስለሆነ ነው። ያ ሳይስተካከል በገዱ ጽሑፍ ላይ ምንም ማለት አይቻልም። ገዱ የጠቅላዩን ንግግር የሰሙት እንዴት እንደሆነ ሲገልጹ “ሰዎች ቆርጠው በላኩልኝ የቪዲዮ ቅጂ” ነው ብለዋል።

ገዱ የግል ታሪካቸው እንደሚያስረዳው “መጀመሪያ ዲግሪ” የያዙት በተለምዶ “የዲግሪ ወፍጮ” ወይም “ድንጋይ ማምረቻ” ከሚባለው ሲቪል ሰርቪስ “ዩኒቨርሲቲ” ነው። ሲቀጥል “ማስተርስ ዲግሪ” ከአዙዛ ነው። መቼም ስለ አዙዛ መናገር እዚህ ላይ አያስፈልግም። ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ግን ከሲቪል ሰርቪስም ሆነ ከአዙዛ የተመረቀ ሁሉ ጭንቅላቱ ገዳዳ ነው ለማለትም አይደለም።

ዩኒቨርሲቲ የገባ ሰው አንድ በመሠረታዊነት የሚማረው፤ የምርምር ጽሑፍ አጻጻፍና አጠቃቀስ ነው። በአግባቡ አለመጥቀስም ሆነ አለመጻፍ ያስቀጣል፤ “የጽሑፍ ሌባ” ተብሎ ሊያስባርርም ይችላል። በተለይ ደግሞ በአንድ ጽሑፍ ላይ የሚሰጥ ትችት ሲሆን በቅድሚያ ሙሉውን ማንበብ የሚጠይቅ ነው። በዚህ መልኩ የማይጽፍ ተማሪ አስተያየቱ የተንጋደደ ስለሆነ ዋጋ ቢስ ነው።

ገዱ የጠቅላዩን ቪዲዮ የተቆረጠውን ነው ያዩት፤ ያውም ሰዎች ቆርጠው የላኩትን። ከየት እንደተቆረጠ፣ ምን ያህል ተቆርጦ እንደተላከላቸው፤ ምናልባትም በሰው ሠራሽ አስተውሎ (AI) ተስተካክሎ የተላከላቸው ይሁን ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ሰሞኑን አሜሪካ በረዶ ወረደ ሲባል ሕንድ ያሉ ወጣቶች በኤአይ በሠሩት ቪዲዮ ላይ ግድግንድ የበረዶ ኳስ በመኪና እና በቤቶች ላይ እየነጠረ ሲወርድ ይታይ ነበር፤ በረዶ ሲነጥር አይገርምም?!

ገዱ በምላሻቸው መጀመሪያ ላይ ነው ምላሻቸው የተንጋደደው፤ ያንን ያነበበ ሰው ደግሞ ለቀሪው ትንታኔያቸው ምላሽ ለመስጠት ብዙ ይቸገራል። ምክንያቱም ሙሉውን ባላዩት ቪዲዮ ምናልባትም እውነተኛ ባልሆነ ቪዲዮ ላይ ነው አስተያየት የሰጡት። ስለዚህ ምላሻቸው ገዳዳ ነው።

የገዱ ምላሽ ለምን ተንጋደደ? የቀድሞው የኢህአዴግ ካድሬ ኤርሚያስ ለገሠ አብዛኛዎቹን ካድሬዎች እሱ እንዳሰለጠናቸው በተደጋጋሚ ሲናገር ተሰምቷል። በሌላ አነጋገር የዲግሪ ቆብ የጫነላቸው ኤርሚያስ ነው። ያኔ ስለ ምርምር ጽሑፍ አጻጻፍ ወይ እነ ገዱን አላስተማራቸውም፤ ወይም ገዱ የብአዴን ስብሰባ ኖሮባቸው ያንን ክላስ ፎርፈው ነበር።

ምክር፤ ገዱ አሜሪካ ያውም ኤርሚያስ በቅርብ በሚገኝበት አካባቢ ስለሆነ ያሉት “ያቺን ያኔ ያመለጠችኝን ትምህርት እስቲ እዚህ በዙም ወይም በቴሌግራም ድገምልኝ” ይበሉት። ከዚያ “በምንባቡ መሠረት” እንደሚባለው በተማሩት መሠረት ለጠቅላዩ አዲስ ምላሽ ይጻፉ።

መቋጫ፤ ኤርሚያስ የቀድሞ ካድሬዎችን ጠንቅቆ ነው የሚያውቃቸው። ዐቢይ ፓርላማ ላይ ስለ ገዱ ከተናገሩ በኋላ፤ ኤርሚያስ ለገዱ ምክር ሰጥቶ ነበር፤ “እኔ ገዱን ብሆን ምላሽ አልሰጥም” ነበር ያለው። ገዱ የዚያን ቀን ያቺን ክላስ መፎረፋቸውን አስታውሶ ይሆን?

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: abiy ahmed, Andargacew, gedu

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule