የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ጃዋር መሃመድ ለድርጅቱ በጀት እንዲመደብና በቋሚነት እንዲረዳ ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ታወቀ። የጎልጉል የኦዲፒ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የድጎማ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ጃዋር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በኦዲፒ ላይ የጥላቻ ሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚሠራ መናገራቸውን አመልክተዋል። በተያያዘ ጃዋር የሚመራው ኦ.ኤም.ኤን. ለሸዋ ተወላጅ ኦሮሞዎች መድረክ እንደማይሰጥና ኦነግ በንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያም ሽፋን እንዲሰጥ እንደማይፈቅድ ተገልጿል። እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ጃዋር ለሚመራው “የትግል ሚዲያ” ከፍተኛ በጀት የጠየቀው ሚዲያው ለተገኘው ለውጥ ትልቁን ሚና ተጫውቷል በሚል ነው። ኦ.ኤም.ኤን. በትግሉ ወቅት የአንበሳውን ድርሻ በመጫወቱ የኦሮሚያ ክልልም ሆነ መንግሥት ሊደጉመው እንደሚገባ በተደጋጋሚ … [Read more...] about መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ