ለቀረበለት ሕጋዊ ደብዳቤ ዛቻን አስቀድሟል ከለውጡ በኋላ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የመጠጋጋት ህልምና ውጥን እንደሌለው ሲወተውት የነበረው ጃዋር በቅርቡ ኦፌኮን መቀላቀሉን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ሊልክለት በዝግጅት ላይ መሆኑ ትላንት በመረጃ ገልጸን ነበር። ዛሬ (ማክሰኞ) የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳመለከተው ጃዋር የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ እጁ ገብቷል፤ ፈርሞ ተቀብሏል። ደብዳቤው እንዳይዘጋጅ ያደረገው ሩጫ ሳይሳካ በመቅረቱ ዛቻ እየሰነዘረ መሆኑም ታውቋል። በተደጋጋሚ የሕግ የበላይነትን በማንሳት ዲስኩርና ማብራሪያ የሚሰጠው ጃዋር፣ ምርጫ ቦርድ በጻፈለት ደብዳቤ መቆጣቱና ወይዘሪት ብርቱካን ላነሱት የሕግ ጥያቄ መልስ ከመመለስ ይልቅ ዛቻን መመረጡን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ይፋ አድርገዋል። በሚያስተዳድራቸው ሠራተኞቹና አበል … [Read more...] about ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ
jawar
የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር
ሕግን በማስከበር ስመጥር የሆኑትና ለዚህም የቀድሞው ታሪካቸው የሚመሰክርላቸው የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለጃዋር መሃመድ የማስጠንቀቂና የማብራሪያ ደብዳቤ ሊልኩ መሆኑን ታወቀ። ጃዋር ለደብዳቤው በቂ ምላሽ ካልሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚያደርጋቸው የፖለቲካ ተግባራት በሙሉ ሊታገዱ እንደሚችሉ አብሮ ለመረዳት ተችሏል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በላከው መረጃ መሠረት ምርጫ ቦርድ ለጃዋር ለመላክ ያረቀቀው ደብዳቤ ጃዋር በየትኛው የሕግ አግባብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሳይኖረው በኢትዮጵያ የምርጫ ሒደትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ማስረጃና ማብራሪያ በቀነ ገደብ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው። በምርጫ ቦርድ ውስጥ የሚገኙ የጃዋር ሰዎች ደብዳቤው ሊላክለት መሆኑን ያስታወቁት ሲሆን ጃዋርም ደብዳቤው ወጪ ከመደረጉ በፊት የቦርዱ ሰብሳቢዋን … [Read more...] about የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር
“እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
ታዬ ደንደኣ እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው። የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረግክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረግክ። ራስህ የሰራኸውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች። ለበርካታ ዓመታት በድራማ ከኦሮሞው ላይ ገንዘብ ሰበሰብህ። አሁን ግን ያን ጊዜ አልፏል፤ ድራማ አዘጋጅቶ የኦሮሞን ድጋፍ መጠየቅ ቀርቷል። ህዝቡ ያንተን አጀንዳ አውቋል። ሀበሻና ሚኒሊክ የአንተ ገበያ ናቸው። የኦሮሞ ድጋፍ ሲቀዘቅዝ ጠዋት ተነስተህ ሀበሻ እና ሚኒሊክ ብለህ ስድብ በመልቀቅ ገንዘብ ትሰበስባለህ። በዚህ መልክ የራስን ብሄር ታልባለህ። … [Read more...] about “እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
የጃዋር ትልቁ የመጫወቻ ካርድ ተቃጠለ – መቀሌ ለለማ የተጋገረውን ኬክ ኦዴፓ ቆረሰው
ጃዋር የሬዲዮ ፈቃድ ተከለከለ - አበደንን እያስተዋወቀ ነው ከአጋሮቹና አቻዎቹ ጋር እኩል ረድፍ ገብቶ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በመቀየር ለመጪው ምርጫ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓን ለመሰንጠቅ በፌዴራሊስቶች ስም መቀሌ የተጋገረውን ኬክ የብልጽግና ፓርቲ እንደቆረሰው ተሰማ። ጃዋር መሃመድ አሁን ካሉት ሁለት የቴሌቪዥንና አንድ የሬዲዮ ስርጭት ጣቢያ በተጨማሪ ለመክፈት ያሰበው ሬዲዮ ፈቃድ መከለከሉ ታወቀ። ራሱን በተገንጣይ ስም እየጠራ “የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል” በሚል “የፌደራሊስት ኃይሎች” ብሎ ራሱ የሰየማቸውን ለቃቅሞ መቀሌ ላይ ትህነግ የጋገረውን ኬክ ይቆርሳሉ ተብሎ የታሰበው አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ። ለዚሁም ዝግጅት መንደረደሪያ አቶ ለማ በኦሮሚያ ይቋቋማል የተባለውን የኦሮሞ ፓርቲዎች ኅብረት እንዲመሩ ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቆ ነበር። … [Read more...] about የጃዋር ትልቁ የመጫወቻ ካርድ ተቃጠለ – መቀሌ ለለማ የተጋገረውን ኬክ ኦዴፓ ቆረሰው
Jawar Mohammed is the Al-Baghdadi of Addis Not an Oromo Activist!
Political/Social activists fight against injustice, suppression, and inequality and in the process, they give their lives to make life a little better for millions of others. Two world-famous activists are Martin Luthor King and Nelson Mandela. While the former gave his life fighting for equality for African Americans in the USA, the latter spent twenty years of his life in prison fighting Apartheid. While activists may naturally belong to one religious group, they never encourage beheadings … [Read more...] about Jawar Mohammed is the Al-Baghdadi of Addis Not an Oromo Activist!
“አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል። ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን … [Read more...] about “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው። ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች … [Read more...] about የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!
የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው። ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት … [Read more...] about ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!
መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የጃዋር ሰለባዎች ዝርዝር በከፊል!
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው የጫትና የመጠጥ ሱሰኛው ጃዋር መሐመድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሃን ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ ጃዋርን የምትደግፉ እፈሩ! ኅሊና ካላችሁ ወደምታምኑት አምላክ ንሰሐ ግቡና ተመለሱ፤ ከሌላችሁ ከሱ ያላነሰ ፍርድን በራሳችሁ ወይም በልጆቻችሁ እንደምታገኙ አትጠራጠሩ፤ አምቦ በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ከተገደሉት መካከል … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች ዝርዝር በከፊል!