• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

November 6, 2019 09:21 am by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው።

ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት ነው የተከበበው?” ብሎ መጠየቅ ነበረበት። ይህን ቢያደርግ ኖሮ ያ ሁሉ መከራና ሁከት አይከሰትም። የ86 ሰዎች ህይወት በከንቱ አይቀጠፍም ነበር። ጥያቄ መጠየቅ ስንጀምር እውነታው ይፋ ይወጣል። የጃዋር አጋች-ታጋች ድራማ ውሸት መሆኑን ካወቅን ሁከትና ብጥብጥ የሚነሳበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም ጃዋር መሄመድ ትውልዱ ኢትዮጵያ ይሁን እንጂ ዜግነቱ አሜሪካዊ ነው። የተከበበው ደግሞ ባሌ ወይም ነገሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ቦሌ ነው። ቀጣዩ ጥያቄ “ማን ከበበው? ለምንና እንዴት ተከበበ?” የሚል አይደለም።

ከዚያ ይልቅ ጥያቄው መሆን ያለበት “የአሜሪካ ኢምባሲ ከአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት ምን ያህል ይርቃል?” የሚል ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ ኢትዮጵያ እንደገባ በማንኛውም አግባብ የማይቋረጥ ወይም የማይጠለፍ ቀጥተኛ የስልክ መስመር ይሰጠዋል። ይህ ስልክ ለአደጋ ግዜ የሚያገለግለው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ በሕይወቱ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ቢገጥመው ከእሱ የሚጠበቀው በዚህ የስልክ መስመር መደወል ብቻ ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ዓላማ ተብለው ሁሌም በተጠንቀቅ የቆሙ ስድስት ሄሌኮፕተሮች፣ ሁሌም በከተማው ቅኝት የሚያደርጉ 13 ፈጣን መኪኖች አሉ። አንድ አሜሪካዊ አደጋ ደረሰብኝ ብሎ በደወለ በጥቂት ቅፅበት ውስጥ እነዚህ መኪኖች እና ሄሌኮፕተሮች ከቦታው ደርሰው ከአደጋ ይታደጉታል።

ስለዚህ ጃዋር መሃመድ ትክከለኛ አደጋ ተጋርጦበት ቢሆንና ከአሜሪካ ኢምባሲ በተሰጠው የስልክ መስመር ደውሎ ቢሆን ኖሮ ኮማንደር እንዳለ “የተባለው” ሰውዬ ከጃዋር ጠባቂዎች ጋር በስልክ አውርቶ ሳይጨርስ ሄሌኮፕተሮቹ ከጃዋር ቤት ጋር ደርሰዋል። “ቄሮ ተከብቤያለሁ!” ብሎ ፌስቡክ ላይ ከመለጠፉ በፊት አሜሪካን ኢምባሲ ይደርሳል። ነገር ግን የጃዋር ፍላጎት የአጋች-ታጋች ድራማ መስራት እንጂ የደህንነት ስጋት አልነበረበትም። እኛም ደግሞ ማን፣ ለምን፣ የትና እንዴት ብለን አንጠይቅም። በመሆኑም ማንም እየተነሳ የፈለገውን ባደረገና በተናገረ ቁጥር እንደ እሳት እራት ለሞት እንጣደፋለን። መጠየቅ ምክንያታዊ ያደርጋል፣ ማወቅ ከጥፋትና ፀፀት ይታደጋል። እኛ ግን አናውቅም፣ አንጠይቅም። ስለዚህ ለአንድ ቀን እንኳን በአካል አግኝተን፥ አናግረን የማናውቀው ሰው ፌስቡክ ላይ የፃፈውን ውሸት አይተን አሊያም በቴሌቪዥን የተናገረውን ጥላቻ ሰምተን አብሮ አደግ የጎረቤት ልጅን በድንጋይ ቀጥቅጠን፣ በስለት ቆራርጠን እንገድላለን።

በእርግጥ ጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ የኦሮሞ ወጣቶች ችግር ብቻ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ከቅማንት እስከ ወላይታ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ፣ ከአሶሳ እስከ አሳሳ፣ ከአፋር እስከ ሀረር፣ ከመቀሌ እስከ ሶሜሌ፣… በአጠቃላይ በሁሉም የሀገሪቱ አባቢዎች የሚስተዋል ችግር ነው። የጃዋር ደጋፊዎች ሆኑ ተቃዋሚዎች፣ “ዶ/ር አብይ ከጎንህ ነን” እና “እኔም ጌታቸው አሰፋ ነኝ” የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው አደባባይ ከወጡት ውስጥ አብዛኞቹ ማንን ለምን እንደሚደግፉት በግልፅ ለይተው አያውቁም። እንዲህ ያለ ነገሮችን በዝርዝር ለመጠየቅና ለማወቅ ፍላጎትና ተነሳሽነት የሌለው ትውልድ ደግሞ የአፈ-ጮሌዎች መጫወቻ ይሆናል። እነዚህ አፈ-ጮሌዎች በራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አይን-ያወጣ ውሸት የሚያሰራጩት የተባለውን ሁሉ ሳይጠይቅና ሳያውቅ ባሰቡት መንገድ የሚነዳ ወጣት እንዳለ ስለሚያውቁ ነው።

ጃዋር መሃመድ ወያኔን ለማስወገድ በተደረገው ትግል ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክቷል። በኦሮሚያ ክልል የታየውን ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ በማስተባበር ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውቷል። ለዚህም ተገቢ ክብርና ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል። ይሁን እንጂ እስከ 2010 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ከወያኔ ጋር ሲታገልና ሲያታግል የነበረ ግለሰብ 2012 ላይ “ወያኔ የኦሮሞ ህዝብ አጋር ነው” ሲል የጃዋር ደጋፊዎች “ለምንና እንዴት?” ብለው መጠየቅ አለባቸው። ሌሊት ላይ ጃዋር “ተከብቤያለሁ” ብሎ ከመፃፉ የተወሰኑ ሰዓታት በፊት “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምሽት ላይ ወደ ሩሲያ እንደሚጓዙ እና ጃዋር መሃመድ በመኖሪያ ቤቱ እንደሚገኝ ስላረጋገጥን ዕቅዳችንን ለመፈፀም ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል” የሚል መልዕክት የያዘ ኢሜይል ላይ የተነጋገርነውን ለመፈፀም ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል” የሚል መልዕክት ከአቶ ጌታቸው ረዳ በኢሜይል የተላከለት መሆኑ ታውቋል።

ስለዚህ ከወያኔ ጋር በተደረገው ትግል ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ውለታ የዋለው ጃዋር ዛሬ ደግሞ መልሶ ከወያኔ ጋር በመመሳጠር የኦሮሞን ህዝብ አሳልፎ ሊሸጥ እንደሆነ መጠርጠር ተገቢ ነው። ይህን ማድረግ ከተሳነን ግን ላለፉት አመታት በተደረገ ትግል የተወገደውን የጭቆና ስርዓት መልሰን በራሳችን የምንጭን መሆኑ የማይቀር ነው። ነገሩን ይበልጥ አሳፋሪ የሚያደርገው በስንት ትግል ወደ ስልጣን የመጣውን የዶ/ር አብይ አመራር አስወገድን በስንት መስዕዋት የተወገደውን የዘራፊዎች ስብስብ መልሰን ወደ ስልጣን መምጣታችን ነው። ይህ በማንኛውም አግባብ ለማድረግ ቀርቶ ለማሰብ እንኳን የሚከብድ ነገር ነው።

በዚህ ሳይጠይቅና ሳያውቅ በሚደግፍና በሚቃወም ትውልድ የፖለቲካ ቁማር የሚጫወተው ጃዋር ብቻ አይደለም። በዚህ ረገድ ህወሓቶች ከማንም የላቀ ልምድና ክህሎት አላቸው። አሁን ላይ የህወሓቶች ዓላማና ግብ በማንኛውም አግባብ ቢሆን ተመልሶ ወደ ስልጣን መምጣት ነው። ለዚህ ደግሞ ሀገር በጦርነት ቢፈርስ፣ ህዝብ በግጭት ቢተራመስ ደንታ የላቸውም። ምክንያቱም የሀገር አንድነትና እድገት፣ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ለእነሱ አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም። የህወሓቶች ዓላማና ግብ እድሜ ልክ ህዝቡን ማፈንና ሀገሪቱን መዝረፍ ነው። ይሄን ደግሞ ባለፉት 27 አመታት በተግባር ታይቶ የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ስለዚህ በማንኛውም አግባብ ከህወሓቶች ጋር በአብሮነትና ትብብር መስራት የአፈናው ተሳታፊ፣ የዘረፋው ተቋዳሽ ለመሆን ከመፈለግ የመነጨ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል። ነገር ግን ወጣቱ ትውልድ “ለምንና እንዴት?” ብሎ መጠየቅ እስካልጀመረ ድረስ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች የውሸት መዓት ይናገራሉ፣ የሃሰት ማስረጃ ያሰራጫሉ። ምክንያቱም የማያውቅ፥ የማይጠይቅ ትውልድ እያደር አምኖ እንደሚቀበላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ላለፉት 27 አመታት በስልጣን ላይ በቆዩበት መልኩ ሌላ 27 አመታት ለመቆየት ቢያስቡ ሊገርመን አይገባም። ከዚያ ይልቅ የሚገርመው የጃዋር ከእነሱ ጋር በአብሮ ለመስራት ፍቃደኛ መሆኑ ነው። የእነ ጃዋር እና ህወሓቶች ትብብር በዋናነት በሦስት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው። ሁለቱ ወገኖች የኦሮማራ ጥምረትን ማፍረስ፣ የኢህአዴግን ውህደት ማደናቀፍ እና የመደመር እሳቤን በማጣጣል ረገድ በተቀናጀ መልኩ በመስራት ላይ ይገኛሉ። የኦሮማራ ጥምረት የህወሓትን አከርካሪ በመስበር የዶ/ር አብይ አመራር ወደ ስልጣን እንዲመጣ ያስቻለ ነው። የኢህአዴግ ውህደት ደግሞ በህወሓት መሪነት የተዘረጋውን የአፓርታይድ ስርዓት ጨርሶ በማስወገድ የሀገሪቱን አንድነትና ሰላም በማረጋገጥ ረገድ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል። የመደመር እሳቤ ደግሞ የኦሮማራ ጥምረት እና የኢህአዴግ ውህደት፣ ብሎም የሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የሚመራበት የለውጥ አቅጣጫ ነው። እነዚህ ደግሞ የተጀመረውን ለውጥ በማስቀጠል ረገድ ቁልፍ ሚና አላቸው። ስለዚህ የእነ ጃዋር እና የህወሓቶች ጥምረት የተጀመረውን ለውጥ በማጨናገፍ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

ህወሓቶች የተጀመረውን ለውጥ ማደናቀፍ የሚሹበት መሰረታዊ ምክንያት እንደ ቀድሞ የራሳቸውን የበላይነት ለማረጋገጥ ነው። የህወሓቶች የስልጣን የበላይነት የሚለው አገላለፅ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ስለዋለ ለዛና ትርጉም እያጣ መጥቷል። ይህ ግን ላለፉት 27 አመታት የነበረውን የህወሓት የበላይነት ለመካድ አያስችልም። በዚህ ረገድ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ የተባሉትን የህወሓት/ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባልን እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል። በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም 17 ቀን በፈጀው የኢህአዴግ ስብሰባ ላይ “ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ከሚመረጥ ሞት ይሻላል” ብሎ ሲፎክር ነበር። በተለይ ደግሞ “ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መፈታት አለባቸው” የሚለው ውሳኔ ለህዝብ ይፋ መደረጉን ተከትሎ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና ምክትል ጠቅለይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን “የቀለም አብዮተኞች ናችሁ” ብሎ ከመሳደብ ጀምሮ “በሽጉጥ እገድላለሁ” እስከማለት ደርሶ እንደነበር በቦታው የነበሩ ዓይን-እማኞች ይናገራሉ።

ከሰሞኑ ደግሞ አቶ አስመላሽ የኦሮማራን ጥምረት፣ የኢህአዴግን ውህደት እና የመደመር እሳቤን የሚያጠጥል ቃለ ምልልስ አድርገዋል። አሁን ያለው ለውጥና አካሄድ ፈፅሞ ሊወጥላቸው እንደማይችል በቃለ ምልልሳቸው በዝርዝር ገልፀዋል። ማወቅ የሚሻ ሰው “አቶ አስመላሽ ለውጡን አምርሮ የሚቃወመው ለምድነው?” ብሎ ቢጠይቅ መልሱን በቀላሉ ያገኘዋል። በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ግለሰብ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የማይገቡበት ቦታ አልነበረም ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ሰውዬው በጥቅሉ 14 ስልጣኖች ነበሩት። እነሱም፡- 1) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ 2) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የመንግስት ዋና ተጠሪ.፣ 3) በኢፌዴሪ መንግስት የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ፣ 4) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ 5) የበጎ አድርጎት ድርጅቶች ቦርድ ሰብሳቢ፣ 6) የብሮድካስት ባለስልጣን ቦርድ ሰብሳቢ፣ 7) የሜቴክ ቦርድ አባል፣ 8) የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሰብሳቢ፣ 9) የትግራይ አካል ጉዳተኞች ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ፣ 10) የኢፈርት ድርጅቶች ቦርድ አባል፣ 11) የኢትዮጵያ ፓራኦሎምፒክ ሊቀመንበር፣ 12) የኢትዮጵያ ወዳጅነት ፎረም ሰብሳቢ፣ 13) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቦርድ ሰብሳቢ፣ እና 14) የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ ነበር።

በዚህ መሰረት አቶ አስመላሽ ማለት በሀገሪቱ የፍትህ ስርዓት ሲጫወት የነበረ፣ የፀረ-ሽብር አዋጁን ጨምሮ አፋኝና ጨቋኝ የሆኑ አዋጆችን ሲያረቅቅና ሲያፀድቅ የነበረ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በዜጎች እምባ ላይ ሲያላግጥ የነበረ፣ እንደ ዘርዓይ ወልደሰንበት ያሉ ጋጥወጥ የሆኑ ሰዎች ከሜዳ ላይ እያነሳ በዳኝነት ሲሾም የነበረ፣ ከዚህ አልፎ ተርፎ ዳኞች ጋር ስልክ በመደወል የፍርድ ቤት ውሳኔን ሲያስቀይር የነበረ ሰው ነው። በዘረፋና ሌብነትም ቢሆን ትልቅ ድርሻ አለው። በአፋር የሚገኘው የጨው ማዕድን ማውጫ በባለቤቱ ስም ተቆጣጥሯል። ከዚህ በተጨማሪ እንግሊዝ ሀገር፣ አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ የራሱ መኖሪያ ቤት አለው። አሁን ላይ ሁለት ልጆቹና ባለቤቱ እንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ቤቱ ይኖራሉ። እሱ ራሱ በቅርቡ ለሥራ እንደሄደ በማስመሰል በመንግስት ወጪና አበል እንግሊዝ ለ28 ቀናት ያህል ቆይቶ መምጣቱን ተሰምቷል።

ሆኖም ግን በትላንቱና በዛሬው መካከል የሰማይና የምድር ያህል የሰፋ ልዩነት አለ። ቀደሞ 14 የስልጣን ዓይነቶችን በግሉ ጠቅልሎ ይዞ የነበረው ሰውዬ ዛሬ የአቶ ጌታቸው አሰፋ ሁለተኛ ተላላኪ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በሁሉም ዘርፍ እጁን ማስገባት የለመደ ሰውዬ ዛሬ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ቀጥሎ የሁለተኛ የአቶ ጌታቸው አሰፋ ተላላኪ መሆኑ መቼም፣ እንዴትም ሊወጥለት አይችልም። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ የኦሮማራ ጥምረትን፣ የኢህአዴግ ውህደትን ሆነ የመደመር መጽሃፍን ያጣጥላል። ለዚህ ደግሞ እንኳን እንደ ጃዋር መሃመድ ካለ ሰው ጋር ቀርቶ ከሰይጣን ጋርም ቢሆን በትብብር መስራት ይፈልጋል። ምክንያቱም አቶ አስመላሽ ቀድሞ የነበረውንና አሁን ያጣውን የሥልጣን የበላይነት መልሶ ማግኘት ይፈልጋል። አስገራሚው ነገር ጃዋር መሃመድ ከእነ አስመላሽ ጋር በአጋርነት መስራት የፈለገው ለምድነው? ምርጫው ሁለት ነው፤ አንደኛ በህወሓቶች ምትክ የራሱን የበላይነት ማረጋገጥ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የህወሓት አገልጋይ መሆን ነው። ይህን ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ መራራ ትግል አድርጎና ከባድ መስዕዋት ከፍሎ ያስወገዳቸው ናቸው። ስለዚህ የእነ ጃዋር ዓላማና ግብ የኦሮሞን ህዝብ ትግልና ነፃነት ለህወሓት አሳልፈው እየሰጡ አይደለምን? እውነታው ይሄ ነው! በእርግጥ ከህወሓቶች ጥምረት መፍጠር የኦሮሞን ህዝብ ለጠላት አሳልፎ መሸጥ ነው!

Seyoum Teshome

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre, Left Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule