ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እያወቁ ሕግን በመጣስ የወሰኑት ውሳኔ ወደ ሌላ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል ስጋት የገባቸው ወገኖች የተማጽንዖ ጥሪ አቀረቡ። ኦፌኮ ስህተቱን ከማረም ይልቅ እርስ በርስ የሚጣረስ መረጃ ማሰራጨቱ በፓርቲው ውስጥ መለያየት እየፈጠረ መሆኑና ጃዋር ደጋፊዎቹን በጅምላ ወደ አመጽ ለመምራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ። ጸሃፊው ያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ በጃዋር መመሪያ ነው። ስጋቱ የተነሳው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ለኦፌኮ በድጋሚ የላከው የጃዋር ዜግነት ጉዳይን የሚመለከተውን ደብዳቤ ተከትሎ አዲስ “አስተምህሮት” መጀመሩ ነው። ለዚሁ የሕግ ይከበር ጥያቄ ቅድሚያ መልስ የሰጡት ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ነበሩ። በምላሻቸው “(ጃዋር) መልኩም ሲታይ ኢትዮጵያዊ ይመስላል” በማለት ስላቅ አዘል መላምት ካስቀመጡ በኋላ ጃዋር መልስ እንዲሰጥበት ደብዳቤው … [Read more...] about ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ
ofc
ኦፌኮ ከለዘብተነት ወደ ነውጠኝነት
ህግ ያልገዛውን ሀይል ይገዛዋል ዛሬ ጦርነቱ ግልፅ ሆኗል። ኦፌኮ መንግሥትን ምንም አታመጣም እስኪ የምታደርገውን አይሃለሁ እያለው ነው። ኦቦ መረራ በስተርጅና ዋልታ ረገጥ ሆነው ፈንድተዋል። ሀይማኖት ውስጥ ያሸመቁ መናፍቃን ባደባባይ ፖለቲካውን ተቀላቅለዋል። ነውጠኛው ጃዋር ራሱን እንደ አሜባ አራብቷል። ጦርነቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ላይ አይደለም ያጠነጠነው የሀገሪቱን መሰረት የመፈነቃቀል ስትራቴጂ ፊት ለፊት አንግቦ እንጂ። ይህ ሀገር ላይ የተመዘዘ ሰይፍ የቱንም እምነት አይምርም። ሀገር ሳለች ነው እምነት፣ ክብርም፣ ራሱ መኖርም። ማንም ራሱን ካላሞኘ በስተቀር፣ ሁሉም በሰላም በማይኖርባት አገር ውስጥ የብቻዬን የሰላም ደሴት እፈጥራለሁ ሊል የሚቻለው አይደለም። እነሆ ዛሬ አንዳች ስውር፣ አንዳች ያልተገለጠ ምስጢር የለም። ዕቅዱ በገሀድ … [Read more...] about ኦፌኮ ከለዘብተነት ወደ ነውጠኝነት
“የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
መረራ - ሲያልቅ እጅ ሰጡ!! ኦነግን ይዞት በነበረው አቋም አማካይነት ፍጹም እንደማይነሳ አድርገው የቀጠቀጡት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ናቸው። “ኦሮሞ ግንድ እንጂ ቅርንጫፍ አይደለም ” ሲሉም የኦሮሞን አካታችነትና ታላቅ ሕዝብነት በማስረገጥ የጎጥ ፖለቲካ ረብ የለሽ መሆኑንን በጥናት አስደግፈው ኦነግን ያኮሰሱት መረራ፤ ኦነግ ውጤት እንደማያመጣም ተናግረው ነበር። ዛሬ ግን “ተመልሰው ለኦነግ እጅ ሰጡ” ሲሉ ወዳጆቻቸው ሳይቀሩ እየወቀሷቸው ነው። የአምቦ ክፋይ በሆነችው ጊንጪ የተለኮሰው የኦሮሞ ትግል አድማሱን አስፍቶ ወደ ሌሎች ክልሎችም ተስፋፍቶ በጥምረት ለውጤት ሲበቃ፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲንከላወስ የነበረውና ተፈረካክሶ በየአቅጣጫው የተበተነው የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ቤት “በጀግንነት” የመግባት ዕድል ተጎናጸፉ። እናም የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው የጠመንጃውንና … [Read more...] about “የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?
“አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” በማለት “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” (ኦዴግ) ODF የሚባል አዲስ ግንባር መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) ያቋቋሙት የቀድሞው የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የቀድሞውን ኦህዴድ የአሁኑን ኦዴፓን ተቀላቅለዋል። ከኦነግ ተገንጥሎ ኦዴግ የሆነው የሌንጮ ለታ ፓርቲ ኦዴፓን መቀላቀሉና በኢህአዴግና በግንቦት 7 ላይ የሚያስከትለው የፖለቲካ ተጽዕኖ ገና አልጠራም። ከዳውድ ኢብሣ ኦነግ ጋር እቀላቀላለሁ ያለው የመረራ ጉዲና ኦፌኮም መጨረሻው አልታወቀም። የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ ከብሪታንያ፣ ከስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት ላይ ስለ ኦዴግ ማብራሪያ የሰጡት ሌንጮ አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች … [Read more...] about ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?