ውሳኔ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢ ነው፤ የህግ ባለሙያዎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ መንግስት “ሸኔ” እና “ህወሓት” ቡድንን በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ለማድረግ መዘጋጀቱ መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡ እንዲህ አይነት ፍረጃ የቀድሞ መንግስትም ሲያደርገው የነበረ ነዉ የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ ዓይነቱ ፍረጃ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ቢሆን እዚህ ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር፤ ይህም ተግባር ቀድሞ ከነበረው መንግስት የተለየ ነው ብዬ አላስብም ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፡፡ “ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በተዘዋዋሪ መጥራት ይመስለኛል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ በዚህ ስም ራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት፣ መንግስት ግን በኦሮሚያ አካባቢ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን ኢላማ … [Read more...] about ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ ህወሃትና ሸኔ አሸባሪ መባላቸው ለውጥ አያመጣም፤ መረራ ጉዲና
merera gudina
ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እያወቁ ሕግን በመጣስ የወሰኑት ውሳኔ ወደ ሌላ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል ስጋት የገባቸው ወገኖች የተማጽንዖ ጥሪ አቀረቡ። ኦፌኮ ስህተቱን ከማረም ይልቅ እርስ በርስ የሚጣረስ መረጃ ማሰራጨቱ በፓርቲው ውስጥ መለያየት እየፈጠረ መሆኑና ጃዋር ደጋፊዎቹን በጅምላ ወደ አመጽ ለመምራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ። ጸሃፊው ያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ በጃዋር መመሪያ ነው። ስጋቱ የተነሳው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ለኦፌኮ በድጋሚ የላከው የጃዋር ዜግነት ጉዳይን የሚመለከተውን ደብዳቤ ተከትሎ አዲስ “አስተምህሮት” መጀመሩ ነው። ለዚሁ የሕግ ይከበር ጥያቄ ቅድሚያ መልስ የሰጡት ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ነበሩ። በምላሻቸው “(ጃዋር) መልኩም ሲታይ ኢትዮጵያዊ ይመስላል” በማለት ስላቅ አዘል መላምት ካስቀመጡ በኋላ ጃዋር መልስ እንዲሰጥበት ደብዳቤው … [Read more...] about ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ