
ጃዋር የሬዲዮ ፈቃድ ተከለከለ – አበደንን እያስተዋወቀ ነው
ከአጋሮቹና አቻዎቹ ጋር እኩል ረድፍ ገብቶ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በመቀየር ለመጪው ምርጫ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓን ለመሰንጠቅ በፌዴራሊስቶች ስም መቀሌ የተጋገረውን ኬክ የብልጽግና ፓርቲ እንደቆረሰው ተሰማ። ጃዋር መሃመድ አሁን ካሉት ሁለት የቴሌቪዥንና አንድ የሬዲዮ ስርጭት ጣቢያ በተጨማሪ ለመክፈት ያሰበው ሬዲዮ ፈቃድ መከለከሉ ታወቀ።
ራሱን በተገንጣይ ስም እየጠራ “የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል” በሚል “የፌደራሊስት ኃይሎች” ብሎ ራሱ የሰየማቸውን ለቃቅሞ መቀሌ ላይ ትህነግ የጋገረውን ኬክ ይቆርሳሉ ተብሎ የታሰበው አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ። ለዚሁም ዝግጅት መንደረደሪያ አቶ ለማ በኦሮሚያ ይቋቋማል የተባለውን የኦሮሞ ፓርቲዎች ኅብረት እንዲመሩ ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቆ ነበር። ለዚሁ ይመስላል አቶ ለማ በአሜሪካን ድምጽ የብልጽግናን ፓርቲ እንደማይደግፉና ከሕዝብ ጋር መክረው አቋማቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ይፋ ያደረጉት።
ጃዋር አስቀድሞ የሚያውቀው የአቶ ለማ የቪኦኤ መግለጫ ኤዲት ለማደረግ እንኳን ጊዜ ሳያገኝ “ታፈነ፣ እንዳይተላለፍ ተደረገ” በሚል አየሩን አጣበበ። ይሁን እንጂ የአሜሪካ ድምጽ ዜናውን አመጣጥኖ ይፋ ካደረገው በኋላ እነ ጃዋር የሚመሯቸው የሚዲያ ተቋማት ዜናውን አጡዘው በሎሬት ዶ/ር ዐቢይና አቶ ለማ መገርሳ መካከል ልዩነት መፈጠሩ ኦዲፒን እንደሚፈረካከሰው አስተጋቡ። የትህነግ አራጋቢዎችም ዜናውን ተቀባበሉት። እንደ አንድ ትልቅ ድል አድርገው ወሰዱት።
አቶ ለማ “ተሰሚነት አጥቻለሁ” በሚል የብልጽግናን ፓርቲ እንደሚሰናበቱ ባሳወቁ ማግስት አሜሪካ ለሥራ ተጓዙ። ጉብኝቱ በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል በየዓመቱ የሚካሄድ ስብሰባ አካል የነበረ ቢሆንም ለአቶ ለማ ግን ከዚህ በፊት ለሌሎች ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ ከአንድ መሪ የማይተናነስ አቀባበል ተደረገላቸው።
ሆኖም አቶ ለማ ለቪኦኤ ሰጡ የተባለው ቃለምልልስ ከተሰማ በኋላ ኦዲፒ ልዩነት መኖሩ የዴሞክራሲው ማሳያ አንዱ ገጽታ መሆኑንን፤ ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም ትህነግ ይነዳው በነበረው ኢህአዴግ ውስጥ እንደማይታሰብ በማስታወቅ የተለሳለሰ መልስ በመስጠት ነባር አመራሮቹን ለፖለቲካ ሥራ አሰማራ።
ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ ዞሮ በውል በማይታወቅ ዓላማ፣ አንድ እግራቸው ከመንግሥት ጋር በሆኑ ሃብታም ግንበኛችና የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚደጎመው የእነ ኤርሚያስ፣ ሃብታሙና ርዕዮት ዓለሙ ዩትዩብ ከትህነግ ፍልፍል ሚዲያዎች ባልተናነሰ የተከሰተው ልዩነት ብልጽግናን እንደሚበላው በእርግጠኝነት አወጁ።
እሁድ ዕለት ኦዴፓ ይፋ ያደረገው ዜና እንዳስታወቀው አቶ ለማ መገርሳ እንዲቆርሱት የተዘጋጀው ኬክ ተቆርሷል። ድርጅቱን ገልጾ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው አቶ ለማ መገርሳ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር አብረው ለመሥራት ቃላቸውን አድሰዋል።
አባ ገዳዎችና በአቶ አባ ዱላ የሚመራው የድርጅቱ የቀድሞ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲና በአቶ ለማ መካከል ያለውን ልዩነት በመሸምገል ስምምነት ማወረዳቸው ይፋ ሆኗል። ልዩነቱን ሲያጦዝ የነበረው ጃዋር መሐመድ የሚያስተዳድራቸው የሚዲያ ተቋማት ስምምነቱን አስመልክቶ ይህ እስከታተመ ድረስ ያሉት ነገር የለም። ዛፍ ለምን ውሃ ጠጣ፣ ከተማ ለመን ጸዳ፣ ሰብል ለምን ታጨደ፣ … እያሉ የሚነተከተኩት የትህነግ ጭፍራ ሚዲያና ሎሌውችም ያሉት ነገር የለም። የሚሉት ይጠፋቸዋል ተብሎ ግን አይጠበቅም።
የአቶ ለማና የዶ/ር ዐቢይ ተስማምቶ ለመሥራት መወሰናቸው እንዳስደሰታቸው ብዙዎች ስሜታቸውን በስፋት በማኅበራዊ ገጾች እየገለጹ ነው። አቶ ለማም በቅርቡ ሰፊ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። ዜናው ግን ጃዋር ኦዴፓን ለመናድ በየተራ ሊጠቀምባቸው ካሰባቸው የሤራ ካርዶች መካከል አንዱ እንደተቃጠለ የሚይሳይ መሆኑንን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናግረዋል።
በሌላ ዜና ጃዋር አዲስ የሬዲዮ ስርጭት ለመክፈት ያቀረበውን ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳገደው የጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮች አመልክተዋል። የዜናው አቀባዮች እንዳሉት ጃዋር ያቀረበው ጥያቄ ለምን እንደታገደ ምንጮቹ በዝርዝር ማሳወቅ አልፈለጉም። ቀደም ባሉት ወራቶች ጃዋር ለኦኤምኤን መንግሥት የሃምሳ ሚሊዮን ብር ድጎማ እንዲሰጥ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው።
የአቶ ለማን መመለስ አስመልክቶ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሚከተለውን ዘግቧል፤
አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ የነበረቸውን ልዩነት አጥብበው የሕዝቡን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሻገር መስማማታቸው ተገለጸ።
አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ልዩነት በኦሮሞ ባህል መሠረት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ልዩነታቸውን አጥበው ከዚህ በኋላ በጠንካራ አንድነት በጋራ በመስራት የህዝቡን ድል ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነት ተደርሷል።
ይህ ስምምነት የተደረሰው የቀድሞ የODP ስራ አስፈጻሚዎችና ነባር አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት ነው።
ፓርቲው የዴሞክራሲ ሥርዓትንና በኦሮሞ ባህል መሠረት ውስጣዊ ችግሩን እና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጠንክሮ እንደሚሠራ ተገልጿል።
በፖለቲካ ሂደት ውስጥ በተለይ ደግሞ ሪፎርም በሚደረግበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑ ነው የተጠቆመው።
የሀሳብ ልዩነት መኖር በራሱ ችግር እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ትልቁ ነገር የሀሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆን ነው መባሉን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጎልጉል ከአንድ የኦዲፒ አባል ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው የመደመር ርዕዮትም ሆነ የብልጽግና መመሪያ ከቀድሞው ጠርናፊ የኢህአዴግ አሠራር፣ ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትም ሆነ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍጹም የተለየ መሆኑ መናገራቸውን ነው። አመራር አባሉ እንዳሉት አቶ ለማ በቪኦኤ የተናገሩት የሃሳብ ልዩነት ለአገራችን ጠላቶችና አፍራሽ ሃሳብ አራማጆች የሚዲያ ፍጆታ የዋለውና አንዳዶችም የተቀበሉት በፓርቲያችን ውስጥ እየጀመርን ያለነውን ግልጽ አሠራር ካለመረዳታቸው የተነሳ ነው። በሁለቱ ጓዶቻችን መካከል የተካሄደው ዕርቅና የአቶ ለማ በብልጽግና መቀጠል ለእኛ ያልተጠበቀ ባይሆንም አገር እናድናለን እያሉ አገራችንን እየበጠበጡ ላሉትና ከእነርሱ ጋር ባልተቀደሰ ፍቅር ውስጥ ለሚገኙት ትልቅ መርዶ እንደሆነባቸው ለማወቅ ችለናል በማለት አመራር አባሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
ጎልጉል
1) እስቲ ይህቺን አንቀፃችሁን እንደገና አንብቧት
“ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ ዞሮ በውል በማይታወቅ ዓላማ፣ አንድ እግራቸው ከመንግሥት ጋር በሆኑ ሃብታም ግንበኛችና የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚደጎመው የእነ ኤርሚያስ፣ ሃብታሙና ርዕዮት ዓለሙ ዩትዩብ ከትህነግ ፍልፍል ሚዲያዎች ባልተናነሰ የተከሰተው ልዩነት ብልጽግናን እንደሚበላው በእርግጠኝነት አወጁ።”
እንደ የእናንተን “ዜና” ለማስረገጥ ያልተረጋገጠ፤ ማስረጃ የሌለው ተራ የስም ማጥፋት ውንጀላ?
2) ከየት የመጣ አማርኛ ነው “ኬክ መቁረስ”? ነው ተገቢ የአማርኛ አገላለጽ ጠፍቶ ነው?
3) ይህችስ አገላለፅ
“በሌላ ዜና ጃዋር አዲስ የሬዲዮ ስርጭት ለመክፈት ያቀረበውን ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳገደው የጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮች አመልክተዋል። የዜናው አቀባዮች እንዳሉት ጃዋር . . ”
ይሄ ጓደኛና ዘመድ ጋ እየደወልን የምናገኘውን ወሬ ነው የጎልጉል “የአዲስ አበባ ምንጮች የምትሉት?” ነው የዜና መረብና የዜና አቀባይ አላችሁ?
4) ይህስ “የአቶ ለማን መመለስ አስመልክቶ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሚከተለውን ዘግቧል፤ ”
ዋሾውና የመንግሥት ፕሮፓጋንዳ መንዣው “ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት”ን ዋቢ አደረጋችሁ?
ጎልጉል በየ”ዜና”ችሁ እንደሚታየው ተደምራችኋል፤ ረጋ በሉ እባካችሁ! ትችቴም ለእናንተው መሻሻል ነው እና ቡራ ከረዩ እትበሉ፤
Every thing is a dramatic game.The Synagogue is striving to save its established system in Etiiopia.Read http://www.antichristconspiracy.com http://www.realjewnews.com
Ethiopia badly needs rule of law now. Justice for the innocent massacred Ethiopians because Jawar Mohamed. There is ample evidence in our had regarding J.M Truth be told, he need to beheld put behind the bar for his crime, than his talk of running for an office.
Many Oromos are now awakened to the fact J.M is about one thing and one thing only.He wants to carve his own plate,if he can as he is a hired gun for Alsisi.Please listen to the following message by Dr.Chala of Harvard University.
1-https://www.youtube.com/watch?v=FhzHpY12siY
2-https://www.youtube.com/watch?v=bcAVuqK9LbM