“በብዙ እብዶች መካከል ጤነኛ ያብዳል” ይባላል ይህን እውነታ ኡመር ሱሌማን ነው ከ18 አመት በፊት የተናገረው። ብዙ ሰዎች የወደዱት እምቢ ካለ ወይም እነሱ የጠሉትን ከወደደ “እብድ” ወይም “ከሃዲ መባሉ አይቀርም።
በዚህ ውስጥ አልፈን ነው የመጣነው እኔ ጤንነቴን በደንብ አውቀዋለሁ የሰውም ማረጋገጫ አልፈልግም ለሰውም እንደዛው ትልቅና አስቀያሚ በሽታ ነው ያለው።
ይህን ለማከምና ለማስተካከል መታገል ትክክል ነው ግን ደግሞ ትግሉ አገር በሚያፈርስ መልኩ መሆን የለበትም። የፈለገ ችግር ቢኖር ከየመን ከሊቢያና ከሶሪያ ኢትዮጵያ ትሻላለች! የመንን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንጂ
ሩዋንዳን የዘነጋ ሰው በራሱ በሽታ ነው። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ይቸግር ይሆናል። ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ያለንንም ማስታወስ ተገቢ ነው የተሰቀለውን ለማውረድ ስትል ብብት ስር የያዝከን እንዳታጣ
————-
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ፓርላማ ላይ እውነት ተናገሩ ሚዲያዎች ጥላቻና ብጥብጥን ከመስበክ እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ጃዋር እንደሰማ “እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል” በማለት ጉድጓድ መቆፈሩን ነገረን።
በእለቱ ጃዋር ቤት ስብሰባ ነበር፤ የሆነ ሰበብም ፈጥሮ እምቢተኝነትን ተቃውሞን ለማነሳሳት ከስምምነት ላይ ተደረሰ። በዚያኑ እለት ከለሊቱ 7:30 ላይ የ ጃዋር ጠባቂዎች እንደሚቀየሩ መደወሉ ተሰማ።
ይህ የስልክ ውይይት ደግሞ በአማረ ሁኔታ ተቀድቶ ወድያውኑ ጃዋር አየር ላይ አዋላት። ይህ ሁሉ ድንገት የተፈጠረ ነው?
.
በሌላ መንገድ እንየው!!
*
ጃዋር የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጓደኛ ነው፤ ጀነራል ብርሃኑ፤ ኮሚሽነር መላኩ፤ ኮሚሽነር ከፋለውና ኮሚሽነር ደመላሽም ጋር በጣም ይቀራረባሉ ይተዋወቃሉ! ታዲያ ጃዋር ይህ ችግር ሲገጥመው ለምን ለሰዎቹ ደውሎ እርዳታ አልጠየቀም?
*
ደግሞ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እያወቀ እሮብ ጠዋት ነገሩን ለማቀዝቀዝ አልሞከረም? ጠዋት ካቃተው ማታ መግለጫ ሰጥቶ ሃሙስ የተፈጠረውን ጥፋት አላስቀረውም?
እኔ ለነጻነት እንጂ ለባርነት አልታገልኩም ትላንት ጠመንጃ ፊትለፊት ቆሜ ለህዝብ መብት ተናገርኩ የማያውቁኝ ሰዎች በስድብ አፌን መዝጋት ይፈልጋሉ! የማይሆን ነገር ነው።!!!
ሁሉም ይወቀው!!! ለጫወታ መስዋእትነትን አልከፈልኩም እስገባኝ ድረስ ኦሮሞን ከሰቆቃና ከስቃይ ውስጥ ለማውጣት ነው ዋጋ የከፈልኩት ስቃይና በደል ደግሞ ዘመድና ጠላት የለውም።
.
እኔ ኑሮዬን ያጣሁለት ኦሮሞ! የልጆቹን ደምና አጥንት ስውር እዚህ የደረሰ ኦሮሞ በማይሆን ግዜና በማይሆን ምክንያት ደሙ በከንቱ ማፍሰስ የማይሆን ነገር ነው። ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል።
ለጠፋው ህይወት ለተጎዳው ለቆሰለው ወገን ለጠፋው ንብረት
በስንት መስዋእትነት የተገነባን የኦሮሞን ህዝብ አንድነት በአንድ ቀን ያፈረሰ ማነው? ለብዙ ሰዎች ይህን ለማመን ያስቸግር ይሆናል ነገ ግን ይገባቸዋል!
.
ይህ የእኔ አቋም ነው ድርጅትንም ሆነ መንግስትን አይመለከትም! ያበደውን ደግሞ አድረን ማወቃችን አይቀርም!
ታዬ ደንደአ
©ትርጉም Hebre Zema
Leave a Reply