
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ።
ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ።
“ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል።
“ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር ሳይቀርብ እና ሳይነበብ ቀድሞ ለህዝብ ለሚዲያ መገለጹ ተገቢ አይደለም ማለቱ ስለማይቀር ክስ መመስረቱን ብቻ ለማሳወቅ ነው” ሲሉም ነው መግለጫው ተከፈተ የተባለውን ክስ የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ለሕዝብና ለሚዲያ እንደሚሰጡበት የሚጠቁሙት።
መግለጫው ክሱ ሰኞ ፍርድ ቤት ለሚቀርቡት ተጠርጣሪዎች ከተነበበ በኋላ በዕለቱ አለበለዚያም ተከትለው ባሉት ቀናት ሊሰጥ ይችላል።
ለዚህም ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ፤ ሁሉም የሚዲያ ተቋማት እንደሚጠሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉን አቶ ፍቃዱ ጸጋን ጨምሮ በምርመራው ላይ ተሳትፎ ያላቸው ፖሊሶች ተገኝተው ዝርዝር መረጃዎች እንደሚሰጡም ይጠበቃል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply