• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!

September 3, 2020 09:50 pm by Editor 4 Comments

መሃል ሰፋሪ አሊያም ገለልተኛ ይመስል የነበረው የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ የጃዋር ግልገል መሆናቸው የምታውቀው፤ ልክ እንደ አይን-አፋር ሴት እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሽምግሌ ምሳሌ እያበዙ ከሄዱ በኋላ በማጠቃለያው ላይ “ጃዋር መሃመድ በይቅርታ ከእስር ቢፈታ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል!” ሲሉ ነው። በእርግጥ በእስር ላይ ያለ ሰው እንዲፈታ ማሰብ፣ አማላጅ መላክ ወይም Lobby ማድረግ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ የተለመደ ነው።

በዚህ ረገድ በሰኔ15ቱ ግድያ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸው በተደጋጋሚ እንደ ማሳያ ተጠቅሷል። ነገር ግን በሰኔ 15ቱ ግድያ የተሳተፉ አካላት በስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አማራዎችን ወይም ሙስሊሞችን ለማጥፋት ታቅዶ የተፈፀመ አይደለም። በክልሉ ሆነ በፌደራል ደረጃ ስልጣን ለመያዝ ያስችላቸው ዘንድ በአማራ ክልል የሚገኙ ኦሮሞዎችን ግደሉ የሚል የዘር ማጥፋት ጥሪ አላቀረቡም። ከሁሉም በላይ የሚያስተዛዝበው ነገር ጃዋር መሃመድ ጥቅምት 12/2012 በአርሲና ባሌ ተመሣሣይ የሆነ የዘር ዕልቂት እንዲፈፀም ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ 87 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ያስገደለ መሆኑ ነው።

በመሰረቱ እንደ ጃዋር መሃመድ ላለ ሰው፤ መቻቻል ማለት መጃጃል ነው! ትዕግስት ፍርሃት ነው! ጨዋነት ማለት ሞኝነት ነው! ይቅርታ ማለት ሽንፈት ነው! ይህ ግለሰብ ቅንጣት ያህል ሰብዓዊነት እና ማስተዋል ቢኖረው ኖሮ በባዶ ሜዳ ተከበብኩኝ ብሎ የዕልቂት ጥሪ አያቀርብም። እንደው ፍፁም በተለየ ሁኔታ ጥሪውን ቢያቀርብ እንኳን በዚያ ምክንያት ንፁሃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በመገደላቸው ትንሽ …. በጣም ትንሽ የፀፀት ስሜት ይኖረዋል። በአደባባይ መፀፀቱን ለመግለጽ ቢቸገር እንኳን አመት እንኳን ሳይሞላው ከስምንት ወር በኋላ ሰኔ 22/2012 ላይ በተመሳሳይ ቦታና ህዝብ ላይ ተመሣሣይ የሆነ የዕልቂት ጥሪ በማቅረብ ከባለፈው እጥፍ የሚበልጡ ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ አያስገድልም።

እንዲህ ያለ ሰው ሰብዓዊ ርህራሄ የሚባለው ነገር ከውስጡ አንጠፍጥፎ የጨረሰ፣ በንፁሃን ሞትና ስቃይ ሃሴት የሚያደርግ፣ የዘር ዕልቂት እና ሁከት በማስነሳት የስልጣን ጥማቱን እና የጥቅም ሱሱን የሚያረካ ፍፁም ሰይጣናዊ የሆነ ፍጥረት ነው። ጃዋር መሃመድ ህሊና ቢኖረው ኖሮ ያደረገውን ሁሉ አያደርግም ነበር። መስሎት በስህተት አሊያም በአጉል ድፍረት አድርጎት ቢሆን እንኳን በጥቅምት ወር ላይ ለፈፀመው ግፍና መከራ በህግ አግባብ ተጠያቂ ሳይሆን በመቅረቱ በምድር ላይ እጅግ በጣም ትልቅ የሚባል ይቅርታ ተደርጎለታል። ይሄ ከሌሎች ሀገራት ነባራዊ አንፃር ሲታይ በችሎት ፊት ሞት የተፈረደበትን ወንጀለኛ በተከሳሾቹ ፊት ምህረት የመስጠት ያህል ከባድ ነው።

በመሆኑም ጃዋር በጥቅምት ወር ለፈፀመው ወንጀል ተከስቶ በትንሹ ዕድሜ ይፍታህ ሊፈረድበት ሲገባ ለፍርድ ሳይቀርብ በመቅረቱ በውስጡ ትልቅ ደስታን፣ በተጎጂዎች ዘንድ ትልቅ የሆነ ሰቀቀን ይችላል። በእርግጥ የጃዋርን ጥሪ ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉባቸው ዜጎች በሀዘን ሰቆቃ ውስጥ እያሉ አቶ ጃዋር ሰኔ 22 ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመጀመሪያው በእጥፍ የሚበልጡ ሰዎች በተመሣሣይ ሁኔታ ተገድለዋል። ይሄ የሚያሳየው አቶ ጃዋር መሃመድ ለሰው ልጅ ህይወት ቅንጣት ያህል ክብርና ዋጋ የማይሰጥ ሰይጣናዊ ፍጡር ከመሆኑ በተጨማሪ ሰብዓዊነትና ማስተዋል የሚባል ነገር ያልፈጠረበት፣ ይቅርታና ምህረት ስለሚባለው ነገር ፈፅሞ ግንዛቤ የሌለው፣ ልክ እንደ ትላንቱ ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እያስገደለ የፈለገውን ነገር ማድረግ እንደሚችል የሚያስብ፣ ከሰውነት ተርታ የወጣ ግዑዝ ፍጥረት ነው።

በአጠቃላይ እንደ ጃዋር መሃመድ ላለ ሰው ይቅርታና ምህረት ማድረግ ማለት በሰብዓዊነት እና ፍትህ ላይ ከማላገጥ የዘለለ ትርጉምና ፋይዳ የለውም። ለዚህ ሰው ይቅርታና ምህረት በማድረግ በሰዎች ህይወት ላይ ቁማር መጫወት የሚሻ የመንግስት አካል ካለ ከተቻለ በምርጫ ካልሆነም በአመፅ ከስልጣን ማስወገድ ትክክል እና አግባብ ነው። ከዚያ በፊት ግን ጥቅምት ላይ ላስገደላቸው 87 ሰዎች ተጠያቂ ባለመሆኑ፣ ለሀገርና ለህዝብ ሲባል በቁጭት፣ በቸልታና በይቅርታ መታለፉን እንደ ዕውቀትና ጀግንነት ቆጥሮ በቀጣዩ ሰኔ ወር በእጥፍ የሚበልጡ ሰዎችን አስገድሎ ሲፎክር የነበረ ወንጀለኛ በምህረት የተለቀቀ ዕለት የሚገባውን ፍርድና ቅጣት በመስጠት ፍትህን ማረጋገጥ ተገቢ ከመሆኑም በላይ የሞራል ግዴታ ነው። ነፃነትና ፍትህ የሚረጋገጠው በመስዋዕት ነው። የተከፈለው መስዕዋትነት ተከፍሎ ነፃነትና ፍትህ ይረጋገጣል እንጂ በንፁሃን ደም በሚቀልድ እብድ ተረግጦ መኖር የሚሻ ሰው የለም!

ስዩም ተሾመ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    September 4, 2020 02:10 pm at 2:10 pm

    ስዩም ተሾመ ቃለ ህይወት ያሰማልን ብለናል ፥ ሌላው በትናንትናው ዕለት ስለፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ያቀረብከውም ትንታኔ በእጅጉ ይበል የሚያሰኝ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ ባልተጨበጠና ባልተረጋገጠ ነገር ላይ በስሜት የምትሰጣቸውን ትንታኔዎች አቁመህ በእውነት ላይ ብቻ አስረግጠህ ብትጽፍ መልካም ነው ፥ ለማንኛውም ከዚህ በላይ ላቀረብከው ትንታኔ ከፍ ያለ ምሥጋና ይገባሃል ።

    Reply
  2. Baba says

    September 4, 2020 05:18 pm at 5:18 pm

    Seyoum Teshome is one angry man with misguided political agenda and a slave of his financiers. All he wrote above is baseless and it based on the hate he has for Jawar. Not only that Seyoum suffers from inferiority complex. All that is exhibited in his above writings. Jawar is a prisoner of conscience and the government needs to release him asap.

    Reply
    • HAYMAN says

      September 15, 2020 02:09 pm at 2:09 pm

      Mr baba may the Almigty God give you heart or mind to think for those who has been brutally killed by the words of your god Jawar mohamed justis will prevail for those who suffered and killed becouse of their Religion or Race by the Rasist words of Jawar and his assocites. Mr. Baba come to your sences dont insult peopels if they think otherwise. you will not defit them. Come to your senses.

      Reply
  3. ዘረ-ያዕቖብ says

    September 20, 2020 01:54 pm at 1:54 pm

    Under ዐብይ አህመድ እስካሁን ድረስ ለህዝብ ያሻገረውና የሠጠው ዴሞክራሲ ወይም ሠላም የለም!!! (ዘ ኢኮኖሚስት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል -Zehabesha:

    አቢይ ብቻዉን ስለፈለገ ዴሞክራሲ አይመጣም፣ ግን ከትግራይ በስተቀር አንድ ለኢትዮጵያ እናትና ልጆች የመጣ ጉዳይ ቢኖር፣ እናትና ልጅ በገዛ ቤታቸው ተማምነው እንዲኖሩ የሆነ ይመስላል፣ ማለትም የአቢይ ካድሬ በየቤቱ እየገባ እናትና ልጅን አያናክስም ማለት የሆነ ይመስላል:: ህወሓት ግን ከተወለደበት ከዛሬ 45 ዓመታት ጀምሮ በየቤተሰብ መሃከል እየገባ መናከስንና መጠራጠርን ስላሰፈነ Globally በትግራይ ህብረተሰብ ውስጥ ህብረተሰባዊ የሆነን ኑሮ የሚመራ የለም:: ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ እናቶች ከልጄ ጋራ በሰላም ተቃቅፌ ለመኖር ያበቃሄኝ አምላክ ተመስገን ማለት ያለባቸውና ከዚያም ቀጥሎ ለሌሎች ተስፋማ ለውጦች ሰላማዊ ትግላቸውን መቀጠል ያለባቸው ይመስለኛል:: Hostage ውስጥ የሚገኙት የትግራይ እናቶች ግን አሁንም፣ ለኔም እንደ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን እናቶች ከልጄ ጋር በሰላምና ካለምንም መሰላለል የምኖርበትን ጊዜ አምጥልኝ ብሎ ከመፀለይ አልፎ አንዳችም መንቀሳቀስ እንኳን ለመሞከር የማይችሉበት ሁናቴ ውስጥ ስለሚገኙ የተሻለ ቀን ብቻ ያምጣ ከማለት ሌላ ምን አለ?
    ከዚያም በላይ ደግሞ ዴሞክራሲ እንዳይመጣ ከሚያውኩት ጉዳዮች አንዳንዶችን ለመጥቀስ ያህል: (ግን ደግሞ ዴሞክራሲ ሲባል ያ ማኒፑላቲቩ ነው ወይስ ሻል ያለ አለ)
    1. ከድሮውኑ የለውጡ አውጠንጣኞች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አስበዉለት ሳይሆን፣ ለውጡን ያቀነባበሩት ቻይናን ከአፍሪቃ ለማባረር ያሉት ዜቤ ነበርና፣ አሁን ችንጉርትን ተክሎ ድንችን ለምን ወደ ገበያ አታቀርቡም እንደመለት ነገርን ቢተውሳ፣
    2. የለውጡ አውጠንጣኞች የለውጡ ሃይሎችን ሲያስተቃቅፉ ከ1965 (ፈረንጅ) እስከ ዛሬይቱ እለት ድረስ በሕረዶ ቕተሎ ባህል ብቻ አድገው ያረጁን ሃይሎችን ሲከቱበት ሌላን በማሰብ እንጂ ዴሞክራሲን በማሰብ አልነበረምና፣ አሁን ከችንኩርት ተከላ እንዴት ተብሎ ነው ድንች ገበየ እንዲቀርብ የሚጠበቀው?
    3. የኖቤል ሽልማቱ ከጉቦነት ጋራ እንጂ ከሌላ ጉዳይ ጋራ የተያያዘ አልነበረምና ስለሱ ማውራቱን ብናቆም የተሻለ ይሆናል፣
    4. አፉን ከፍቶ የመርካቶ ኪስ አውላቂነትን ሲዋደቅ ከስልጣን የተከነበለው TPLF የያልበረደለት አይነት ጎረምሳ በጥባጭነትን በሚጫወትበት አካባቢ ዘንዳ ዴሞክራሲን መርሳትና ለዴሞክራሲ ከምብሓዲሽ ትግል መጀመር ሊያስፈልግ ነው፣
    5. የአምሓራ ሓሳድነትም እኔ ደደብ ነኝና፣ እኔ ካላስተዳደርኳችሁ የሓሳድነት ሚናን ከመጫወት በስተቀር ሌላ ቀና ተግባር አይታየኝም አዲስ አበባም ሰላም አታገኝም፣ ይሄንን እርኩስ ጠባዬን ግን ራሴን አሞኝቼ ሌላውንም አሞኘሁኝ ስል፣ ጭራች የማህተመ ጋንዲ ነው እላችኋለሁኝ ባዮች እስካሉ ጊዜ ድረስ ዴሞክራሲን ለሚቀጥለው 3000 (ሶስት ሺህ) አመታትም ልንረሳው እንችላለን::
    6. የተወሰኑ ኦሮሞ ሃይሎች በአንድ በኩል በብረት ሃገሪቱን ማመስና በሌላ በኩል ደግሞ ዴሞክራሲ ብሎ መጮህ ውጤቱ አሁን ያለውን ሁናቴ አናርኪን እንጂ ሌላን አያስከትልምና እንዴት ነው የአስተሳሰብ ጉዳይ?
    7. እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር እንጂ በየሃያላን መንግስታት ዘንዳ እየተጎነበሰ አንዳችም ነገር የሚጠብቅ ከሆነ መሰረታዊ ለውጥ የሚባል ነገር አይመጣም፣ ለምን ቢባል ሃያላን ሃይሎች ንጥረ ሃብትን እንጂ የሰው ልጅን ወደው አያውቁምና
    8. ለህዝባቸው የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ሃይሎች ምናልባት ካሉ፣ ውድድር ሲካሄድ በውድድሩ ዘንዳ መሸነፍም እንዳለ ግልፅ እንዲሆንላቸው ያስፈልጋል፣ ስለሆነም በስልጣን ላይ እስካሉ ጊዜ ድረስ በህዝባቸው የሚያስመሰግናቸው እንጂ የሚያስነውራቸው ተግባራት ዘንዳ መውደቅ የለባቸውም
    9. በእንዲህ ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላም ስልጣንን በሚለቁበት ጊዜ ካለ ምንም ፍርሃት አገራቸው ውስጥ ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ ወይኔ በኋላ ወዴት ልገባ ነው ከሚለው ፍርሃት ጋራ አይነታረኩም፣ እንደ ምሳሌ ወይዘሮ ክሊንተንን እንውሰድ፣ ለነገሩ ወይዘሮ ክሊንተን ኦባማንም ሆነ ትራምፕን ማሸነፍ ይገባት ነበረ፣ ኣይተ ክሊንተም፣ ለባለቤቱ ምርጫ ፉክክር በሚደረግበት ጊዜ ወደ ሃርለም ብቅ ብሎ “ጥቁሩ ፕረዚደንታችሁ እኔ ነኝ እንጂ ኦባማ አይደለም” ያለው ነገር በተወሰነ መልኩ ሃቅነት አለው፣ እስካሁን ጊዜ ድረስ እኔ ካየኋቸው የአሜሪካን ፕረዚደንቶች የተሻለው እሱ ነበርና ነው፣ እና እርሱ ከወረደበት ጊዜና ባለቤቱም ከትሸነፈችበት ጊዜ ድረስ ካለ ምንም ስጋት በገዛ አገራቸው ተዝናንተ ይኖራሉ እንጂ ምን ልሁን ወዴት ልሽሽ ከሚል ጣጣ ጋር አይናቆቱም፣ የኛዎቹም ጠቅላላ ሂይወታችሁን አገራችው ውስጥ አዝናንቶ ከሚያኖራችሁ መልካም ተግባራት ላይ ብቻ እንጂ ከሌላ ነገር ጋራ አለመያያዝ፣
    10. የምእራብ ጋዜጠኛ ምን ጊዜም የምእራቡን ፍላጎትን ነውና የሚያስጠብቀው፣ የምእራቡ ፍላጎት ደግሞ ንጥረ ሃብትን መበዝበዝና፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ በረሃብ ሲቆላ የምእራቡ ጋዜጠኛ ግን በአመት አስር ጊዜ ቸቸለንና ሆኖሉሉ እየበረረ ፀሃይ መቆላትን ነው ቅድሚያ የሚሰጠው፣
    11. Unity in diversity

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule