አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል። በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስር አውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን … [Read more...] about ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ