• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የበቀለ ገርባ የክስ ዝርዝር

August 6, 2020 07:52 am by Editor Leave a Comment

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከወር በፊት በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፣ የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና ሌሎች ወንጀሎች እንደሚከሰሱ መወሰኑን ዓቃቤ ሕግ ረቡዕ ዕለት አስታወቀ።

አቶ በቀለ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሃጫሉ ሞትን ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰው ሁከትና ግጭት፣ በራሱ በሕዝቡ የተመራ እንጂ እሳቸው ይህንን ማድረግ የሚያስችል ሠራዊት እንደሌላቸው ገልጸው፣ መንግሥት ፍርድ ቤትን በመጠቀም ተቀናቃኙን ለማጥፋት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቢያነ ሕግ ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ልደታ ማስቻያ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ተጠርጣሪው አቶ በቀለ በምን እንደሚከሰሱ ተወስኗል ብለዋል። ክስ የሚመሠረትባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን፣ ክሱም የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና በሌሎች ወንጀሎች መሆኑን አስታውቀዋል።

በዓቃቤ ሕግ የቀረበ የወንጀል ዝርዝር

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ፀጋና ዓቃቤ ሕግ ኤፍሬም ኃይሉ በችሎት ተገኝተው ተጠርጣሪው ስለሚከሰሱበት የወንጀል ዓይነት ከመናገራቸው በፊት፣ ላለፉት 35 ቀናት በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ ሲያደርግ የከረመው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተፈቀደለት ስምንት ቀናት ውስጥ የሠራቸውን የምርመራ ክንውኖች ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

መርማሪ ቡድኑ የድምፃዊ ሃጫሉን ግድያ ምክንያት በማድረግ በተጠርጣሪው አማካይነት በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረ አመፅ፣ በትራንስፖርት ዘርፍ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር 45 ገጽ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጿል። በዚህም፤

  • 7.4 ሚሊዮን ብር የመንግሥትና
  • 28 ሚሊዮን ብር የግል፣
  • በድምሩ 37,283,933 ብር ንብረት መውደሙን አስረድቷል።

በብርበራ የተገኙ የተጠርጣሪው ሁለት ሽጉጦችና ከግብረ አበሮቻቸው የተገኙ ሰባት ሽጉጦች በፎረንሲክ ተመርምረው፣ ከፋብሪካ ሥሪት ውጭ የውል ቁጥር እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ሰነድ መሰብሰቡን አክሏል።

አቶ በቀለ ወደ ሻሸመኔ ደውለው፣

  • “በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እስከሚወድቅ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል፤” በማለት፣
  • ብሔርንና ሃይማኖት መሠረት ያደረገ የአመፅና የብጥብጥ ጥሪ መመርያ በማስተላለፋቸው
  • 32 ሰዎች መሞታቸውን፣
  • 110 ሆቴሎች፣
  • 239 የመንግሥትና የግል መኖሪያ ቤቶች፣
  • 393 የግል መኖሪያ ቤቶች፣
  • 56 ሱቆች መቃጠላቸውንና መውደማቸውን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል።
  • በተጨማሪም 148 ሱቆች መዘረፋቸውንና መሰባበራቸውን፣
  • 14 ፋብሪካዎች መቃጠላቸውን፣
  • 80 የግልና ሁለት የመንግሥት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን፣
  • 42 ባጃጆች፣
  • 18 የሞተር ብስክሌቶች፣
  • 63 የግል ድርጅቶች፣
  • አንድ የእምነት ተቋም፣
  • 26 የግል ሕንፃዎች መቃጠላቸውንና መውደማቸውን ዘርዝሯል።
  • ዘጠኝ ወፍጮዎች መቃጠላቸውን፣
  • አራት የመንግሥትና የግል ባንኮች መዘረፋቸውን፣
  • በአጠቃላይ 1,128 አባወራዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰቡን መርማሪ ቡድኑ ተናግሯል።

መርማሪ ቡድኑ ለምርመራ የሰጣቸውን

  • የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የምርመራ ውጤት ማስረጃ ሰነድ መሰብሰቡን፣
  • አቶ በቀለ ከሌሎቹ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ከቡራዩ እንዲመለስና በኦሮሚያ ብልፅግና  ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲገባ ማድረጋቸውን፣
  • በጽሕፈት ቤቱ ውስጥ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የፖሊስ ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣
  • አስክሬኑ ሳይቀበር ለአሥር ቀናት እንዲቆይና ከተለያዩ አካባቢዎች በሚመጡ ወጣቶች የምኒልክን ሐውልት በማፍረስ እዚያ እንደሚቀበርና
  • የአራት ኪሎ መንግሥትን ለመፈንቀል ዕቅድ እንደነበራቸው የሚያስረዱ ጭብጥ ያለው የ27 ምስክሮች ቃል መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል።

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተሰጠው ስምንት ቀናት ውስጥ ከላይ የተገለጸውን የምርመራ ሒደት ማከናወኑንና የጊዜ ቀጠሮ ምርመራውን ማጠናቀቁን አስታውቆ፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 80 እና ተከታዮቹ ቁጥሮች መሠረት የተቀበለውን የሰዎች የማስረጃ ቃል (ምስክርነት) በፍርድ ቤት ለማረጋገጥ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ መክፈቱን በማሳወቅ፣ የጊዜ ቀጠሮው መዝገቡ ተዘግቶ ወደ ቀዳሚ ምርመራ ችሎት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የጠበቆች ምላሽ፤

አቶ በቀለ ገርባ ያቆሟቸው ስድስት ጠበቆች ግን የመርማሪ ቡድኑን የመጨረሻ ጥያቄ ተቃውመዋል። ጠበቆቹ እንደገለጹት የደንበኛቸው የምርመራ መነሻ አቶ በቀለ ባስተላለፉት ስልክ ጥሪ የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ከመንገድ ላይ በማስመለስ በኦሮሚያ ብልፅግና  ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲገባ አድርገዋል የሚል የነበረ ቢሆንም፣ የቀረበባቸው ምንም ማስረጃ እንደሌለ ገልጸዋል።

በጥቅሉ የወደመን ንብረት በመጥቀስ የቅድመ ምርመራ መዝገብ እንደከፈተ አድርጎ መናገር፣ የቅድመ ምርመራን ዓላማ የማያሟላና ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ መሆኑን አስረድተዋል። ቀዳሚ ምርመራ በዋና ምርመራ ወቅት የተገኘ አመላካች ነገር ሲገኝ የሚፈቀድ እንጂ፣ ስሜታዊ ሆኖ በተፈለገው ጉዳይ መዝገብ ዘግቶ ሌላ መዝገብ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነና ማስረጃ ስለጠፋ ብቻ ቅድመ ምርመራ መክፈት የሕግ መሠረት እንደሌለው ተናግረዋል።

ቅድመ ምርመራ ካስፈለገ መጀመርያውኑ መክፈት ይቻል እንደነበር ጠቁመው፣ አቶ በቀለ ከፍተኛ ፖለቲከኛና ሥራም ያለባቸው ሰው በመሆናቸው ፖሊስ መዝገቡን ዘግቻለሁ ስላለ ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ፖሊስ ባቀደው መሠረት ማስረጃ ስላጣ ከሕግ ውጪ ዋስትና ለማስከልከል ሌላ ምርመራ መጀመር እንደሌለበትም አክለዋል። አቶ በቀለ ከልጆቻቸው ጋር ለቅሶ ሄደዋል እንጂ ሌላ ያደረጉት ነገር የለም ብለዋል።

የአቶ በቀለ ምላሽ፤

አቶ በቀለ ራሳቸው ለፍርድ ቤቱ ከመጀመርያው እንደተናገሩት፣ መንግሥት ፍርድ ቤትን እየተጠቀመ ተቀናቃኙን ለማጥፋት እየሠራ ነው። “እኔ ይህንን ሁሉ ልሠራ የሚያስችለኝ ሠራዊት የለኝም። ሕዝብ ሲብሰው ወይም ብሶት ሲሰማው በራሱ ይነሳና ዓለም እንዲያየው ያደርጋል። በዚህ ጊዜ ሁሉም መሪ ሁሉም ተከታይ ይሆናል። ያንን አመፅና ሁከት ራሱ ነው የመራው። በሻሸመኔ ተፈጽሟል ስለተባለው ነገር እንደዚያ የማድረግ ዕቅድም ታሪክም የለኝም። ይህ መንግሥት በሕዝብ ያልተመረጠ መንግሥት ነው። ምርጫ ይራዘም ሲል ምርጫ መራዘም እንደሌለበት በመግለጽ ሕዝብ ተቃውሞውን አሰምቷል። እኔም ከእነሱ ጋር ነኝ። በደጋፊዎቼና በፖለቲካ ፓርቲዬ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የተሠራ ሥራ ነው፤” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በሙሉ የተሠራውን በእሳቸው ላይ መከመር ሙያዊ፣ ሥነ ምግባራዊ፣ ሕጋዊና ሞራላዊ አለመሆኑንም አክለዋል። የእሳቸው መታሰር አገርን የሚያረጋጋ ከሆነ ቆይቶ ወደፊት የሚታይ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ለለቅሶ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መውጣታቸውን ጠቁመው፣ ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል።

የዓቃቤ ሕግ የመልስ መልስ፤

ዓቃቢያነ ሕጉ በሰጡት ምላሽ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ማስረጃ የመስማትና የመመዘን ሥልጣን እንደሌለው ገልጸው፣ ክርክር ማድረግም ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ቡድኑ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ምን እንደሠራ ማረጋገጥና ተጠርጣሪ በምርምራ ሒደቱ ላይ ያለውን አቤቱታ ማድመጥ እንጂ፣ ክርክር ማድረግና ማስረጃ መመዘን የችሎቱ ሥራ እንዳልሆነም ዓቃቤያነ ሕጉ አስረድተዋል።

የማስረጃውን ዓይነትና ይዘት “አልተገለጸልኝም” ብሎ መጠየቅም ተገቢ እንዳልሆነም አክለዋል። ወንጀሉ ከተፈጸመበት ጊዜ አንፃር ምርመራው የተፋጠነ መሆኑን የገለጹት ዓቃቤያነ ሕጉ፣ ከሰኔ 25 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በአጭር ጊዜ ፖሊስ የምርመራ ሒደቱን ማጠናቀቁ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን ማከናወኑን የሚያሳይ እንደሆነም ገልጸዋል።

ቀዳሚ ምርመራውን በሚመለከት መርማሪ ቡድኑ ዝም ብሎ በራሱ የሚከፍተው ሳይሆን፣ የምርመራ መዝገቡ በዓቃቤ ሕግ ተመርምሮ ቀዳሚ ምርመራ እንደሚያስፈልግ ሲወስን እንደሚከፈትም ዓቃቤያነ ሕጉ አስረድተዋል።

በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ መሠረት የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ መከፈቱን አረጋግጠው፣ የመርማሪ ቡድኑ የምርመራ መዝገብ ተዘግቶ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል። አቶ በቀለ የተጠረጠሩበትና የሚከሰሱበት የወንጀል ሕግ 240 (2) እና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63 ድንጋጌ ደግሞ ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ዋስትና እንደሚከለከል በሕግ አውጭው አካል የተወሰነ በመሆኑ፣ የጠየቁት ዋስትና ተገቢ እንዳልሆነም ገልጸዋል።

የፍርድቤቱ ብያኔ፤

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የምርመራ መዝገቡን እንዲያቀርብ፣ በተከራካሪ ወገኖች የቀረበውን የክርክር ሐሳብ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለሐሙስ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ቀጥሯል። (ምንጭ፤ታምሩ ጽጌ፤ ሪፖርተር)

ተጨማሪ፤ ለሐሙስ የተቀጠረው ችሎት ጉዳዩን አዳምጦ የወሰነው እዚህ ላይ ይገኛል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: bekele gerba, chilot, jawar, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule