በወንጀል ተከስሰው በእስር ቤት የሚገኙት ጃዋር ሲራጅ መሐመድ፣ በቀለ ገርባ ዳኮ፣ ሐምዛ አዳነ ታዬ እና ሸምሰዲን ጠሃ መሐመድ ከሰኞ መስከረም 25 ቀን ጀምሮ በሚመሠረተው የአደራ መንግሥት ለመሳተፍ ከእስር እንለቀቅ ብለው ተማጽንዖ አቅርበዋል።
ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ልቅም ባለ አማርኛ ከሽነው በጻፉት ደብዳቤ መንግሥታዊ አካል ለሆነው “የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች” ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ በግልባጭ “ለፌዴራል ዐቃቤ ሕግ” እና “ለፌዴራል ወንጀል ምርመራ” ጥያቄያቸውን ልከዋል።
ተከሳሾቹ መቀሌ ከመሸገው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድብ ህወሓት እና ከሌሎች ራሳቸውን ተቃዋሚ ፓርቲ ብለው ከሚጠሩ ጋር በመሆን ከመስከረም 25 ጀምሮ የአደራ መንግሥት እንመሠርታለን ብለው በተደጋጋሚ ሲናገሩና ሲሠሩ እንደነበር ይታወቃል።
ተከሳሾቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ከዚህ በታች ይገኛል፤
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply