የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ በዋስ መፈታታቸው ተሰምቷል። ፖሊስ ለችሎት እንዳስረዳው ወይዘሮዋ የተፈቱት ቀዳሚ ምርመራ እስኪሰማ ድረስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28 መሰረት ነው። ፋና ችሎቱን ጠቅሶ እንደዘገበው ወይዘሮ ኬሪያ ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ የሚቆዩት በሰርቪስ ማረፊያ ነው። የህግ ማስከበሩ ሲጀመር ሌሎች ሲሸሹ መቀሌ ሆነው እጃቸውን የሰጡት የቀድሞ አፈ ጉባኤ፤ እጃቸውን ከሰጡ በኋላ ክስ ሳይመሰረትባቸው መቆየቱ ይታወሳል። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንዴት ወደ መቀሌ ሄዱ? አፈጉባዔዋ ወደ መቀሌ የሄዱት ከአዲስ አበባ ተገፍተው መሆኑንን ጉዳይን በወጉ ሲከታተሉ የነበሩ ይናገራሉ። ኬሪያ ሃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ከማስታወቃቸው በፊት ከአቶ ጃዋር ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲመሠርቱ … [Read more...] about የኬሪያና የጃዋር ድብቁ ግንኙነትና አዲሱ የቤት ውስጥ እስር
keria
“ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም
ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆነችው ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጥታለች። ኬሪያ ኢብራሂም በህውሓት ከፍተኛ አመራርነት፣ በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግላለች። ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብላ ወደ መቀሌ የሸሸች ሲሆን ሾፌሯ ግን የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ እሷን መቀሌ አድርሶ ንብረቱን በሙሉ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መምጣቱ ይታወሳል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰላማዊ መንገድ እንደ ኬሪያ ኢብራሂም ሌሎችም የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። እሷም የጦርነቱ አስፈላጊነት አልታየኝም፤ ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት በማለት ተናግራለች በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ተነግሯል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about “ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም