• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ቀኑ ለመራጮችና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጥሩ ነው” ወ/ሪት ብርቱካን

June 21, 2021 11:25 pm by Editor 1 Comment

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እኩለ ቀን ላይ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ቀኑ ለመራጮች፣ ለፓርቲዎችና በአጠቃላይ ለአገራችን ጥሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በመጀመርያው ዙር የምርጫ ሒደት እስካሁን አንድም የፀጥታ ችግር አልገጠመንም፡፡ አምቦ አንድ ጣቢያ ላይ ምንም የተፈጠረ ነገር ሳይኖር ለአስፈጻሚዎች በደረሳቸው መረጃ በመደናገጥ ለጊዜው ገለል ብለዋል፡፡ ነገር ግን እናስቀጥለዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከባድ ችግር የለም፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ሁሉም ሥፍራዎች እየተካሄደ ነው፡፡ ዜጎችም እየመረጡ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ጣቢያዎች በአብዛኛው በሚባል ሁኔታ በሰዓቱ ከፍተው መራጮችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ 9 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ኃላፊነት የጎደላቸው አስፈጻሚዎች በቦታቸው ባለመገኘታቸው ጣቢያዎቹ ሳይከፈቱ ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን ቦርዱ ወዲያው መፍትሔ ወስዷል፡፡ በዘጠኙ ጣቢያዎች የተፈጠረውን ክፍተት በመሙላት 27 አስፈጻሚዎች ቃል ገብተው ተሰማርተዋል፡፡ ምርጫውም እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ 

የመዝገብ መጥፋት 

አዲስ አበባ ላይ አንድ የመራጮች መዝገብ የጠፋ ሲሆን፣ ይህንን እናጣራለን ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን፣ ይህ መራጮችን ችግር ውስጥ እንደማያስገባና በአፋጣኝ መዝገብ ተልኮ ካርዳቸው እየታየ የምርጫ ሒደቱ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ 

የቁሳቁስ እጥረት

በአንዳንድ ቦታዎች የቁሳቁስ እጥረት ገጥሟል፡፡ ይህ አታሚው ከተሰጠው ትዕዛዝ ውጪ በ50/50 ያሸጋቸው የመራጮች ወረቀቶች መኖራቸው ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡ የታዘዘው 100/100 አንድ ላይ ተጣብቆ እንዲመጣ ነበር፡፡ ይህ ችግር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ አልተከሰተም፡፡ ችግሩ የተከሰተው በክልል ላይ ሲሆን፣ የጎላው ደግሞ አሶሳ ላይ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ስላለቀባቸው በአየር ኃይልና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፋጣኝ አሶሳ እንዲደርስ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ 

አሶሳ ላይ ለተፈጠረው የመምረጫ ወረቀት እጥረት መራጮች ላይ ለሚፈጠረው እንግልት ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉም ወ/ሪት ብርቱካን ተናግረዋል፡፡ 

የሲቪል ሶሳይቲ ታዛቢዎች

የሲቪል ሶሳይቲ ታዛቢዎች በየቦታው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አረጋግጠናል፡፡ አንድ ሁለት ቦታ ላይ ግን ታዛቢዎችን አናስገባም ብለው ያለመቀበል ሁኔታ በቦርዱ አስፈጻሚዎች ታይቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ለዚህ መፍትሔ ተሰጥቶ እየታዘቡ ነው፡፡ 

ያልተከፈቱ ጣቢያዎች 

በደቡብ ኡባ ደብረፀሐይ በተባለ የምርጫ ክልል አንድ ሰማያዊ ምርጫ መስጫ ሳጥን ተሰርቋል፡፡ ይህንን ፖሊስ እያጣራ ነው፡፡ ብብርና አግሊቾ ምርጫ ክልሎች ላይ (የክልል ምክር ቤት) ምርጫ ክልሎች ሆነው፣ የተወካዮች ምክር ቤትንም ይመርጣሉ፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት ሰነድ ምንም ችግር ባይኖረውም፣ የደቡብ የምርጫ ክልሎች ዲዛይን ውስብሰብ በመሆኑ አንዱ መሄድ የነበረበት ለሌላው ሄዷል፡፡ ነገር ግን ምርጫው ሳይስተጓጎል እየተከናወነ ነው፡፡

እዚህም እዚያም የምርጫ ወረቀት ያነሳቸው የምርጫ ጣቢያዎች አሉ፡፡ ከሥር ከሥር ለማድረስ የሚያስፈልገው ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ መግለጫው ከተሰጠበት እኩለ ቀን አንስቶ የጎደለው እንደሚሟላ ተገልጿል፡፡  

ቦርዱን ያሳሰበው ጉልህ ችግር 

በየምርጫ ጣቢያው የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎቻቸውን አስቀምጠው ጉዳዩን የመታዘብ፣ የማየት፣ ችግር ከጋጠመ አስመዝግበው ወደ ሕግ የመውሰድ መብት አላቸው፡፡ ይህን በተመለከተ በአብዛኛዎቹ ክልሎች ጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው ማለት ቢቻልም፣ 3 ክልሎች ላይ በተለይ በሁለቱ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ሥጋት ታይቷል፡፡  በአማራና በደቡብ ክልሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ፣ እየተደበደቡና ባጅ እየተቀሙ እንደሆነ፣ የገዥው ሲቀር ከሁሉም ፓርቲዎች አቤቱታ ተቀብለናል ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን፣ ይህ እንዲፈታ ለክልሉ አስተዳዳሪዎቸ መናገራቸውን ተስተካክሎ የፓርቲ ወኪሎች በቦታቸው ካልተገኙ የምርጫውን ተዓማኒነት አደጋ ላይ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ 

ማስተካከያ በአፋጣኝ ማድረግ እንዳባቸው፣ የታችኛው ክፍልና አንዳንዴ የሕግ አስፈጻሚዎች ተግባሩን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ቦርዱ እንደሚያሳስብና ይህንን የሚያደርጉ አሁኑኑ መታቀብ እንዳለባቸው ቦርዱ ያሳውቃል ብለዋል፡፡

በዕጩዎች ወኪሎች ላይ የሚደረግ ሕገወጥ ተግባራት በውጤቱ ላይ ችግር ስላለው፣ ይህንን የመንግሥት አካላት ተገንዝበው ችግሩን የሚፈጽሙትን ዛሬ የሥራ ቀን ስላልሆነ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ እንዲያደርጉ የጠየቁት የቦርድ ሰብሳቢዋ፣ ይህ ችግር በመለስተኛ ደረጃ በአፋርም ታይቷል ብለዋል፡፡ 

በአዎንታዊ መታየት ያለበትና ለሕዝቡም ለቦርዱም ትልቅ ድል ነው የሚባለው በአብዛኛው ጣቢያዎች ከጥቂቱ በስተቀር በሰዓት ተከፍተው በሰላም ምርጫው እየተከናወነና ዜጎችም እየመረጡ መሆኑን ነው፡፡ 

የቁሳቁስ እጥረት ያለበት ሳንካ ቢሆንም፣ የማይፈታ ችግር ስላልሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይስተካከላል፣ ቀጣዩን መግለጫ ስንሰጥ ችግሮቹ ይፈታሉ ብዬ አስባለሁ ብለዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የፓርቲ ወኪሎች በየቦታው እየተገኙ ኃላፊነታችን እንዲወጡ አስቻይ ሁኔታ እንዲጠር ጠይቀዋል፡፡ አክለውም ችግሩ በስፋት የታየበት አዲስ አበባ፣ ደቡብ ክልል በሥራቸው የሚተዳደሩ ሠራተኞቻቸውን፣ አስተዳዳሪዎቻቸውንና ተወዳዳሪዎቻቸውን ጨምሮ ከማሰናከል ተግባር እንደታቀቡ እንዲያደርጉ ቦርዱ ጥሪ ያቀርባል ብለዋል፡፡ 

የፍርድ ውሳኔ ያላረፈበት ጉዳይ ያላቸው በርካታ ሰዎች እስር ቤት ቢኖሩም፣ በእስር ቤት የተቋቋመ ጣቢያ ስለሌለ ማንም እስረኛ ሊመርጥ የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ፣ አዲስ አበባ ላይ ለገጠመው ክፍተት እንዲሟላ ተደርጎ ምርጫው እየተካሄደ መሆኑን፣ ዘግይተው የጀመሩ ጣቢያዎችን በተመለከተ ቦርዱ ውሳኔ ማሳለፍ ስለሚችል ዓይቶ ሰዓት የሚራዘምበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በመግለጽ ወ/ሪት ብርቱካን የእኩለ ቀን መግለጫቸውን አጠናቀዋል፡፡ (ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics, Right Column Tagged With: birtukan midekssa, election 2013, election 2021

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    June 24, 2021 08:09 am at 8:09 am

    እንቅፋት የሌለበት ምርጫ በየትኛውም ዓለም ላይ ታይቶ አይታወቅም። ዲሞክራሲ ማለት የሙከራ ሂሳብ ማለት ነው። ለዚያም ነው በምድር ላይ ፍጽም ዲሞክራሲ የሰፈነበት ምድር የሌለው። በጊዜው በዲሞክራሲ ስም የሚሆነውን ያየው እውቁ ፈላስፋ ፕሌቶ ዲሞክራሲን ከተጸየፉት አንድ ነበር። ወደ እኛው የመከራ ምድር ስንመለስ ደግሞ በምድሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተብሎ የተነገረን ጉድለት የለበትም ባይባልም ጅምሩ መልካም ነው። ግን ሲዘፈን ለሚያለቅስ፤ ሲለቀስ ለሚዘፍን እቡኝ ወገን ማር ነክ ነገር ሁሉ እሬት ነው። ስለዚህ መፍትሄ ሆኖ ከመቅረብ ይልቅ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዛሬም የጦር መሳሪያ ይዞ በየጫካውና ገደሉ እንዘጥ እንዘጥ እያሉ ራስን አሽብሮ ህዝብን የሚያምሱ የፓለቲካ ሙታኖች የሚራወጡባት ምድር ላይ ይህ ጎደለ ያ ተዛነፈ ማለት የመፍትሄው አካል ከመሆን ይልቅ የጠላት መሳሪያ መሆንና የህዝባችን ሰቆቃ ማባባስ ነው።
    በነጮቹ የዘመን መቁጠሪያ 1874 -1876 ክፉኛ ተደቁሳ ውርደት የተከናነበችው ግብጽ ዛሬም በሱዳን በኩል ዛቻና ማስፈራራት መጣሁ ደረስኩ ግድባችሁን አጋየዋለሁ በማለት ትራፊ ወያኔን ሌሎች ወስላቶችን አስታጥቃና አሰልጥና እንደገና አስርጎ በማስገባት የፓለቲካ ሴራዋን ተያይዛዋለች። በታንዛኒያ ጅሌስ ኔሬሬ የሃይል ማመንጫ ግድብ ፍጻሜ ላይ እንዲደርስ እርዳታ ቢጤ ጣል የምታረገው ግብጽ የሃበሻው ምድር በራሱ ወንዝ የራሱን ግድብ በራሱ እንዳይሰራ የማትፈነቅለው ድንጋይና የማትሸርበው ሴራ የለም። ለዚህም ድጋፍ እንዲሆናት ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር በሚል በዪጋንዳ፤ በጅቡቲ፤ በሩዋንዳ፤ በቡሩንዲና በሱዳን ትስስር ፈጥራለች። ያው በየቀኑ ስለ ወያኔ የሚጮኹት ምዕራባዊያንም አረንጓዴ መብራት ለግብጽ ካበሩላት ቆይቷል። እንግዲህ ይህ ምርጫ የተካሄደው በዚሁ ሁሉ የውጭና የሃገር ውስጥ ሴራ ተከቦ ነው። ስለሆነም ሙከራውን ከማድነቅ ውጭ ሌላው ሁሉ የውስልትና ፓለቲካ ነው። በመሰረቱ ምርጫው ገና አልተጠናቀቀም። በጸጥታና በሌላም ምክንያት ምርጫ ያልተካሄደባቸው ስፍራዎች ገና ይመርጣሉ። ለጳጉሜ ተብሏል። ቆይቶ ማየት ነው።
    በዚህ ሁሉ የፓለቲካ እሰጣ ገባ ውስጥ ግን ዛሬም ከበሮና ክራር እየደበደቡ ጀግና ነን ኑ ግጠሙን ወዪላችሁ፤ ሂሳብ እናወራርዳለን የሚሉ የቁም ሙቶች መቼ ነው አይናቸው ተከፍቶ የሞትን ሽታ ማሽተት የሚያቆሙት? ብቀላ ብቀላን ይወልዳል እንጂ የሚወራረድ ሂሳብ የለውም። ሽንፈትን አምኖ ተቀብሎ መኖርም ጸጋ ነው። ዝም ብሎ ሁሌ ለህዝቤ፤ ለወገኔ፤ ለዘሬ፤ ለሃይማኖቴ የሚሉ ሰንካላ ፓለቲከኞች አንድም በዚህ ጥላ ሥር ተሰልፈው የዘየድት ነገር የለም። አይበቃም እስከ አሁን የተገዳደልነው? ሰው እንዴት ካለፈው አይማርም። የኮንጎውን ፓትሪስ ሉቡንቧን ገድለው ስጋውን በአሲድ ያቃጠሉት ነጮች አሁን አንድ ጥርሱ ተገኝታለች ተብሎ እሱን እንመልስ አንመልስ በማለት ግብግብ ላይ ናቸው። ፍትህ አለበት በሚባለው የአሜሪካ ምድር Native Indians ላይ የደረሰው ሰቆቃ መፈጠርን ያስጠላል። በካናዳ አሁን ራሱ እየተቆፈረ የሚወጣው የዚያው ሃገር Indigenous people አጽም ገና ብዙ ያፋልማል። በግዛቷ ጸሃይ አትጠልቅም የተባለችው ታላቋ እንግሊዝ ማሰሮ ውስጥ እንዳለ አንድ እቃ በአንዲት ደሴት ላይ ብቻ ተለጥፋለች። ጊዜ ሁሉን ይሽራል። ያልቆሰለ፤ ያላቆሰል ምንም መንግሥት የለም። ብዙ ማለት ይቻላል። ጥያቄው እንደ ውሻ ከተከመረ ቆሻሻ ላይ ጥንብ እያወጡ ከመናከስ እውነቱ ታውቆ ክፉ ነገሮች እንዳይደገሙ ህግና ደንብ አውጥቶ በሰላም መኖር አማራጭ አይገኝለትም። ሌላው ሁሉ ነፋስን እንደመከተል ነው።
    አሁን በምድሪቱ ብርቅዬ የሆነው ዘሩን፤ ቋንቋውና ሃይማኖቱን ወደ ኋላ ጥሎ ለአንድ ሃገርና ህዝብ የጋራ ደህንነት ልክ እንደ እውቁ ቡልቻ ደመቅሳ ሰንበቶ የሃገሪቱን ደህንነትና ሰላም የሚሻ ነው። ጭራሽ ሰው የለም እያልኩ ሳይሆን የገደሏት እየበሉ የሞቱላት የሚራቡባት ያቺ ምድር አካሄዷን ማስተካከል ይኖርበታል። ያው ወ/ሪት ብርቱካን እንዳለችው ምርጫው ለሃገርም ለቁጥር ለበዙት የፓለቲካ ፓርቲዎችም (ተሳተፉም አልተሳተፉም) ትምህርት ሰጪ ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule