• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

April 1, 2021 01:15 am by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መካከል በተፈጠረ መከፋፈልና ውዝግብን የተመለከቱ እግዶች፣ አቤቱታዎችና ከሁለቱም ወገን የሚመጡ ማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት ቡድኖቹን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የስነስርአትና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉትን አስተዳደራዊና ህጋዊ መንገዶች ሁሉ እንደተጠቀመና መፍትሄዎችን ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውሶ፣ በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ፓርቲው ካለበት ችግር ብቸኛ መውጫ መንገድ መሆኑን በመረዳትና በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራር ክፍሎችም ያመኑበት በመሆኑ፣ በአመራሮች መካከል ያለው ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል።

ኦነግ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በቁጥር 19/ABO/2013 በተጻፈ ደብዳቤ ድርጅቱ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ የአመራር አባላት መምረጡን በመግለጽ፣ በውስጥ ችግሩ ምክንያት የጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂድ በመቆየቱ የምርጫና የእጩ ምዝገባ ጊዜ አልፎብናል በማለት ቦርዱ የነበረበትን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለት ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲያጸድቅለት ጠይቋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የቀረቡትን ሰነዶች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ምርምሯል።

ፓርቲው ያደረገውን ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን አባላት ስም ዝርዝርና ፊርማ፣ በመጋቢት 5 ቀን 2013 ዓም ያደረገውን የድርጅቱን ብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ፣ የተሻሻለውን የፓርቲውን የመተዳደሪያ ደንብ በኦሮሚኛ የተመዘገበና በአማርኛ የተተረጎመ ሰነድ፣ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓም ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ከ500 በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን፣ ምላተጉባኤው የተሟላ መመሆኑን በማሳየት ፣ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተደረጉት ማስተካከያዎች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የተደረጋቸውን ገልጾ ጠቅላላ ጉባኤው እውቅና እንዲያገኝለት ጥያቄ አቅርቧል። ቦርዱም ሰነዶቹን መመርመሩን ገልጿል።

በመሆኑም ፓርቲው መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም የተደረገውን የጠቅላላ ጉባኤ ማስፈጸም የሚችለውን አስፈጻሚ ኮሚቴን ያቋቋመበት ስብሰባ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 23(4) በተመለከተው መሰረት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው 2/3ኛ አባላት በተገኙበት መሆን ሲገባው የተባለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ 2/3ተኛ አባላት የተገኙበት ሳይሆን ሶስት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ብቻ ያከናወኑት ምልዓተ ጉባኤው ያልተሟላ ስብሰባ ነው። ስለዚህ የጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ የተቋቋመው ኮሚቴ በደንቡ መሰረት ምልዐተ ጉባኤ ሳይሟላ የተቋቋመ በመሆኑ የጠቅላላ ጉባኤውን መጥራትና ማስፈጸም አይችልም ሲል ወስኗል።

በሌላም በኩል በፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 16.2 የጠቅላላው ጉባኤ የሚያቅፋቸውን አካላት በግልጽ የተመለከቱ ሲሆን በዚህ ጉባኤ ላይ ሊሳተፋ የሚገባቸው የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት፣ሙሉ የአባልነት መብት ያላቸው የቀድሞ የኦነግ አመራር አባላት፣ በየደረጃው ከሚገኝ መዋቅር የሚወከሉ የኦነግ አባላት፣ ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል የተለየ ድርሻ በማበርከት የሚታወቁ ሰዎች (የጉባኤተኛው 5% የማይበልጡ)፣ ከፓርቲው ጋር በቅርበት በመስራት ላይ የሚገኙ ህዝባዊ ድርጀቶች ማለትም የሴቶች ፣ወጣቶች፣ ባለሙያዎች …ወዘተ ማህበራት ተወካዩች (ብዛታቸው በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚወሰን) መሆናቸው ተመልክቶ እያለ ፓርቲው አካሄድኩት በማለት ባቀረበው የጠቅላላ ጉባኤ ተካፋዩች ዝርዝር ከፍ ብሎ የተመለከቱት የጉባኤው የሚያቅፋቸው አካላት መኖራቸው አልተመለከተም፣ በመሆኑም ተሳታፊዎቹ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ለመወከላቸው ቦርዱ ማረጋገጥ አልቻለም።
እንዲሁም በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 17.1 ተወካይ ሆኖ ለጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ አባል ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ ያገለገለና ግዳጁን በአግባቡ የፈጸመ መሆን እንዳለበት በሚደነግገው መሰረት መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የተሳተፉ አባላት ይህንን በደንቡን የተመለከተውን መስፈርት ማሟላታቸው ለማረጋገጥ የቀረበ ነገር የለም።

የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባኤ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ጠቅላላ ጉባኤ ለማከናወን ከአመራሮቹ ውዝግብ በፊት ተቋቁሟል የተባለ ኮሚቴ እውቅና ውጪ የሆነ የድርጅቱን ህገደንብ እና አሰራር የተከተለ አይደለም በማለት ለቦርዱ ተቃውሞ የቀረበበት መሆኑንም ተገንዝቧል።

ቦርዱ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ የፓርቲው አመራሮችን ፣ መዋቅሮቹን እና አባላቶቹ የተለያዩ በፓርቲው ህገ ደንብ ላይ በተቀመጡ መንገዶች በመጠቀም በጠቅላላ ጉባኤ ችግሩን እንዲፈቱ የወሰነ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን የተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ይህንን መሰረት አድርጎ የተከናወነ ጉባኤ መሆኑን አያሳይም። ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያደራጅ ኮሚቴ ያቋቋሙትም ሶሰት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ብቻ መሆናቸው ቦርዱ ጥር 19 ቀን ከወሰነው የፓርቲው አመራሮች መዋቅርና አባላቶች የተለያዩ ህጋዊ መንገዶችን በመጠቀም ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ አለባቸው ከሚለው አንጻር ሲታይ የቦርዱን ውሳኔ አያሟላም። ጠቅላላ ጉባኤው ተካሂዷል የተባለው በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ቢሆንም ኮረም አለመሙላቱንና በሦሥት ሥራ አስፈፃሚዎች ብቻ የተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል። በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት የለውም ሲል ቦርዱ ወስኗል። ውሳኔውን መሰረት በማድረግም በዚህ ጉባኤ የተመረጡትን አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል አይችልም። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ውስጥ ለመሳተፍ እና እጩዎች ለማቅረብ ያቀረቡትን ጥያቄ አሁን የተመረጠው አመራር ተቀባይነት ካለማግኘቱ ጋር ተያይዞ ቦርዱ ጥያቄውን ማየት እንዳላስፈለገው ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓም አስታውቋል። (ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics, Right Column Tagged With: election 2013, election 2021, Election Board, olf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule