ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ምንም ጊዜ የማይቀየር፣ ሊስተባበል የማይችልና ልዩ የሆነ መለያ አላቸው። ይህም ለክህደትና ለመሸጥ፣ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ ለባንዳነት የተጋለጡ ወይም መደምደሚያቸው ባንዳነት ነው። ሌሎቹን እንተዋቸውና በአገራችን ዋና ምስክር የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) ማንሳት ይበቃል። ጥሩም መከራከሪያ የሚቀርብበት የዘመኑ አፍላ ታሪክ ነው። ቃለ ምልልሱ ከተካሄደ ቆይቷል። ሰሞኑን ግን የሩሲያ መንግሥት ቲቪ በድጋሚ ሲያሳየው ነበር። ጋዜጠኛው ቭላዲሚር ፑቲንን ይጠይቃል። ይህን የቆየ ቃለ መጠይቅ ማስተላለፍ የተፈለገው በቀድሞ ወጥ ቀቃይ የሚመራውና አሁን ቫግነር የተባለው ኢመደበኛ አደረጃጀት ከሩስያ መከላከያ ጋር የገባበትን መፈታተን ተከትሎ ነው። ጥያቄ - ይቅርታ ታደርጋለህ?ፑቲን - አዎ፤ ግን ለሁሉም አይደለም፤ጥያቄ - ይቅር ለማለት የማይቻለው … [Read more...] about ኢመደበኛነት – አገር አፍራሽ የዘመኑ ባንዳነት
russia
“ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች
እኤአ በፌብሩዋሪ 2014 በ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣውንና ምርጫው “ደህንነትና ትብብር ድርጅት” (OSCE Organization for Security and Cooperation) በተሰኘው ዓለምአቀፋዊ ድርጅት የጸደቀው የዩክሬን መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ተወገደ። ፕሬዚዳንቱ ቪክቶር ያኑኮቪች ሕይወታቸውን ለማዳን ከአገር ለቅቀው ወጡ። መፈንቅለ መንግሥቱ የተቀነባበረው በተለይ በአሜሪካ ባልሥልጣናት ነው። ትውልደ ዩክሬን የሆነችውና በወቅቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአውሮጳና ዩሬዢያ ረዳት ጸሐፊ የነበረችው ቪክቶሪያ ኑላንድ የሤራው ዋና አቀናባሪ ነበረች። አብሯት ሟቹ ሴናተር ጆን ማኬይን ሠርቷል። ፕሬዚዳንት ያኑኮቪችን ከሥልጣን ለማስወገድ ቪክቶሪያ ራሷ ከማስተባበር ባለፈ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡትን ዩክሬናውያንን ከመደገፍ አልፋ ለሰልፈኞች ብስኩት ስታድል በወቅቱ … [Read more...] about “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ጉባኤ ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ጋር በጽ/ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት እንደምትፈልግ ተናግረዋል። በቀጣይ ዓመት በአፍሪካ ሊካሄድ ስለታሰበው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤን ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ነው አቶ ደመቀ መኮንን የገለፁት። አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ስለ ጽ/ቤታቸው ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የአፍሪካና ሩሲያ ኩባንያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር መቋቋሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዘውም የጉባኤው ዝግጅት አካል የሆነ ውይይት በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ አገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን