የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ክልሉ ወደ ሰላም ተመልሶ የተረጋጋ ሕይወት እንዲቀጥል ለማድረግ የወሰደውን እርምጃ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ እና በቀጠናው የሚገኙ ተቋማት እንዲደግፉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሪቫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጡ መግለጫ፣ ሩሲያ ወዳጅ ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ስላለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግሮቻቸውን ለመፍታት በአፍሪካውያን ወንድሞቻቸው ድጋፍ የራሳቸውን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የሩሲያ እምነት መሆኑንም ገልጸዋል። አሸባሪው ህወሓት የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደርን ለመያዝ ባደረገው ሙከራ የሰብአዊ ቀውስን ማባባሱን እና የስደተኞች እና የሀገር ውስጥ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በትህነግ ላይ ለምትወስደው እርምጃ ልትደገፍ ይገባታል፤ የሩሲያ መንግሥት
russia-ethiopia
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ጉባኤ ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ጋር በጽ/ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት እንደምትፈልግ ተናግረዋል። በቀጣይ ዓመት በአፍሪካ ሊካሄድ ስለታሰበው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤን ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ነው አቶ ደመቀ መኮንን የገለፁት። አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ስለ ጽ/ቤታቸው ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የአፍሪካና ሩሲያ ኩባንያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር መቋቋሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዘውም የጉባኤው ዝግጅት አካል የሆነ ውይይት በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ አገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን