የሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ፣ የቀድሞው የአብን ተመራጭና የአሁኑ የኢህአፓ/ትብብር እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ዶ/ር አበባው ደሳለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ በምርጫው ማሸነፍ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ብስጭትና ንዴት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ተወዳድረው ከትብብሩ እና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕዝብ የተመረጡትንም በብልጽግና ችሮታና ድጋፍ የተመረጡ፣ በምርጫ ሳይሆን በቅርጫ ያሸነፉ በማለት ወርፈዋል። ወደ ፓርላማ አለመግባት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የተከበሩ አቶ አበባው ብሔር ተኮር ከሆነው አብን ወጥተው ወደ ኢህአፓ የገቡበትን ምክንያት አስረድተዋል። “ኢህፓን የመረጥኩበት ምክንያት ደግሞ እንደሚታወቀው ጠንካራ ታጋዮች የወጡበት ፓርቲ ነው። ለተራ ጥቅም ብለው ለተራ ኢኮኖሚ ጉዳይ ብለው ህሊናቸውን የማይሸጡ … [Read more...] about ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ

