
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤
አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ
አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ
ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ
ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ
ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ
ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ
ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች
ንጋቱ አንገሶም
አምደማርያም ተሰማ
እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በሀገር መከላከያ ሰራዊት በፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት አማካኝነት ተይዘው አዲስ አበባ ገብተዋል።
በተመሳሳይ እነዚህን የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” ሲሉ የምስራቅ ዕዝ 25ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ሃላፊ መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ ተናግረዋል።
አሁን አዲስ አበባ የገቡትን ከፍተኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ለማዋል የትግራይ ህዝብ መረጃ በመስጠትና መንገድ በመምራት ከፍተኛ ትብብር በማድረጉ መቶ አለቃ ስዩም አመስግነዋል። (እጸገነት አክሊሉ፤ ኢ.ፕ.ድ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply