የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 4 የቡድኑ አባላት ደግሞ እርምጃም ተወስዶባቸዋል።
የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀውን የጁንታው አፈቀላጤ ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
በዚህም መሰረት፣
1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣
2. ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፣
3. አበበ ገብረመድህን የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበረ፣
4. ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር፣
በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ህዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከተደመሰሱት ውስጥ ሴኩቱሬ ጌታቸው ከዚህ ቀደም በጁንታው መገናኛ ብዙሃን በኩል ጁንታው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል ብሎ ማረጋገጡ ይታወሳል።
ከተደመሰሱት በተጨማሪም 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም፣
1. ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣ የስብሃት ነጋ እህት፣
2. ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
3. ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፣
4. ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
5. ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
6. አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣
7. ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ፣
8. ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም
9. ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበረ ሁሉም በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የህወሃት ጁንታ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑንም ብርጋዴል ጀኔራሉ ገልጸዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት እነዚህ የጁንታው ቁልፍ የጥፋት ቡድን አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋናውን አቅርቧል።
ሠራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሰረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የጀመረውን ቀሪ የጁንታውን ርዝራዦችን አድኖ ለመያዝና በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አረጋግጠዋል።
ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል ፋና ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
ጊዜ ከሰው ጋራ እየገፈተረ ባፍጢሙ ለደፋው ለዛሬ ለሌለ
በትዕቢት ተይዞ ፈርኦን ለሆነ፤ ሲመከር ሲለመን አሻፈረኝ ላለ
በእነዚህ ግፈኞች የሃገር እሾኾች የተንኮል ኮረጆ
እንባቸው፤ ደማቸው ዶፍ ሆኖ ያለፈ
የስንቱ ቤት ፈረሶ ስንቶችስ ሞተዋል?
በስቃይ ሰቆቃ ዘመን የቆጠሩ እናቶች አባቶች ዛሬ ላይ የቆሙ
አይባልም ነበር ሰው ሲሞት እሰየው አሁን ግን ጨፍሩ እንዳሻችሁ ሁኑ
ወያኔ ሞታለች ብላችሁ አብስሩ።
በአለም ታሪክ ውስጥ የሾኬ ተጠልፈው ከስልጣን የወረድ፤ በጦር ተሸንፈው ያጎበደድ፤ ለመኖር የገደሉና የዘረፉ ለመኖራቸው ቃልቻ መጠየቅ አይሻም። ነበሩ። አሉ፤ ይኖራሉ። ይሁን እንጂ እንደ ወያኔ ያለ በአንድ ዘር ብቻ የተዋቀረ እብድ ቡድን በሃበሻው መሬትም ሆነ በሌላው አለም ታይቶ አይታወቅም። አሁን ይሙት ይዳን የማይታወቀው የወያኔ አፈቀላጼ አቶ ጌታቸው ረዳ ያኔ ከሶስት ዓመት በፊት እንደፈለጉ ሲፈነጩ እንዲህ ብሎ ነበር። “አማራና ኦሮሞ አንድ ሆኑ ማለት እኛ የቤት ስራችንን አልሰራንም ማለት ነው”። ባጭሩ ሲተረጎም እነርሱ ሲጫረሱ የእኛ መኖር ይረጋገጣል ነው። አይ ወያኔ በሰው ደም ታጣቢ። በትግራይ ህዝብ ነጋጂ። በራሱ የፓለቲካ ሸር የሰከረ ድርጅት። እንዲህ እንደ ሮም መንግስት ሸክላ ይሁን? እሰይ የስለት ጧፌን አስገባለሁ። ጧፉ ሲነድ የእነርሱ መቃጠል ይታየኛልና። ከዋሻ የወጣ ምንጊዜም ቢሆን መደበቂያው ዋሻ ነው። የዋሻ አስተሳሰብ እንደያዙ መሞት ግን የሞትም ሞት ነው። ገደል ስለገባቸው የሟች ጄኔራል ሚስት ሳስብ እብደታቸው ምን ያህል ሰማይ ጠቀስ እንደሆነ ያሳያል። እንዴት ሰው አሜሪካን የመሰለ ነገር አይቶ አይማርም። እንዲህ የውሻ ሞት ያስሞታት የሰው ደም ነው። እኔ የሚገርመኝ የስብሃት ነጋ ጠባቂዎች ተደምስሰው እሱ መያዙ። ሁለት እህታማቾች ይጣሉና ትልቋ አንቺ ዝም በይ እኔ እኮ ያንቺን ዳይፕር እየቀየርኩ ነው ያሳደኩሽ ብትላት ያው ቀብድ እየከፈልሽ ነዋ። እኔም አንቺ ስታረጂ የአንቺን መቀየሬ አይቀርም አለቻት። ሁላችንም ተሳስቀን ነገሩ አለፈ። አሁን ማን ይሙት የትግራይ ወጣት ልጆች ተደምስሰው ይህ ጥርሱ የወላለቀ ዲያብሎስ በነፈሱ ይያዛል። የወያኔ ጠባቂዎች ምን ቢጋቱ ነው ቀኑ እንደመሸ አለማወቃቸው? አሁን ድምጽ የጠፋው የጋዜጠኛው እና የስደተኛው ማስታወሻ ደራሲና የሻቢያ ሰላይ አቶ ተስፋዬ ገ/አብ የጋዜጠኛው ማስታወሻ በሚለው ላይ እንዲህ ብሎን ነበር። ” ሰዎች ተሰብስበው በአንድ ክበብ ውስጥ ይጫወታሉ። ብዙዎቹ የወያኔ ባለስልጣኖችና ወታደራዊ መኮንኖች ናቸው። የካራምቦላ ጫዋታ ላይ አንድ ጄኔራል ከስብሃት ነጋ ጋር ሳይግባባ ቀርቶ ስብሃት ስለተቆጣ ይገድልሃል ዝም በል ተብሎ ቁጭ ብሎ እንደ ሴት ልጅ ሲያለቅስ ትዝ ይለኛል ይለናል። በሌላው ትዝታው ደግሞ ወያኔዎች ተሰብስበው ዛሬ ማንን እንግደል በማለት አምቦ የሚገኘውን ባለሃብት የአበበች ደራራን አባት አስገድለው ገዳዪን ወታደር እንደገደሉት ይናገራል። ከዚህ የጨለማ ሃይል ጋር ነው ኦነጎች ህብረት የጀመሩት፡፡ የሙት ትውልድ ሙታንን ይከተላል፡፡ ሰፊና አለም አቀፋዊ እይታ ያለው ደግሞ ለሰው ልጆች መብት ዘርና ቋንቋን ተገን ሳያደርግ ይፋለማል፡፡ በተለይም በአለም ዙሪያ በቆዳቸው ቀለም ብቻ መከራና ሃበሳ ለሚቆጥሩ የጥቁሮች መብት ይቆማል።
በቅርቡ አንድ ሰው አስቆመኝና ከየት ሃገር ነህ? ኢትዮጵያዊ ትመስላለህ ሲለኝ አዎን ከዛው ነኝ ስለው እኔ ከአልባኒያ ነኝ አለኝ። እሺ አልኩ። ታሪክን ምን ያህል ታውቃለህ ሲለኝ የታሪክ ተማሪ አይደለሁም አላውቅም አልኩት። የእኔና የአንተ ሃገር በፋሺሽቱ ጣሊያ ሞሶሎኒ ሁለት ጊዜ ተወረናል ሲለኝ ድንግጥ አልኩ። የማውቀው የእኛውን ብቻ ነው። እናንተም ሁለት ጊዜ ተወራችሁሃል በጣሊያን አልኩት አዎን። በነጮች የቀን መለኪያ 1918-1920 ከዚያም 1939-1943 በማለት ተጫውተን ተለያየን። ለካ ወረራው ለአውሮፓም ደርሷል ብዬ በሆዴ ቤቴ ገብቼ ታሪኩ እውነት መሆኑ አረጋገጥኩ። የምንሸልለው ወንድምና እህታችንን ገድለን፤ ደሳሳ ጎጆአችን በራፍ ላይ ቆመን ወያኔ ባሰመረው የአፓርታይድ የክልል ስሪት ላይ እስከሆነ ድረስ ብዝሃነት አይኖረንም። አንድ የአንድን ቋንቋና ባህል ካለደነቀ ብቻህን ከመሰሎችህ ጋር ብትዘፍን አበው እንደሚሉት ” በሰው ሃገር የከበረና ጫካ ገብቶ የዘፈነ አንድ ናቸው” አይነት ነው። ህብረ ብሄራዊነት ያለ ክልል፤ ሰው በፈለገው እንደ ፈለገው ተንቀሳቅሶ የመኖር፤ የመስራት፤ የመማር መብት በምድሪቱ ላይ እስካልሰፈነ ድረስ የወያኔ ግባአተ መሬት ብቻውን ለምድሪቱ ሰላም አያመጣም። ሞታቸው አስተሳሰባቸውን፤ የቀበሩትን የክፋት ፈንጂ ሁሉ አፈነዳድቶና በእነርሱ የተበከሉ የዘርና የቋንቋ ሰልፈኞችን እስካላስወገደ ድረስ ችግሩ ራሱን ይደግማል። ግን የወያኔ ሞትና የመቃብር ስፍራ ለሌሎችም ስፍራ አዘጋጅ በመሆኑ የተገኘው ድል ከሁሉ በላይ ለትግራይ ህዝብ ጠቃሚ ነው። ደህና ሁን አንድ ላምስት፡ ደህና ሁን ወያኔ ሁሌ የውሸት ቋት። እፎይ እስቲ ምድሪቱ ከግርግር ትረፍ። በቃኝ!