• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ

December 2, 2022 03:13 am by Editor Leave a Comment

ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ስብሐት ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል።

ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው።

አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ አቅርቧል።

የአቶ ስብሐት ነጋ ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ መልስ ባለማቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ ብይን ሰጥቷል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለፊታችን ሮቡ ህዳር 28 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት የህወሓት አመራሮች ማለትም የድርጅቱ መስራች የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ እና እህታቸው ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና አቶ ኪሮስ ሐጎስ በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ከስር መፈታታቸው ይታወሳል። (ታሪክ አዱኛ)

Filed Under: News, Right Column Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, sebhat nega, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule