• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ

January 13, 2021 01:12 pm by Editor Leave a Comment

ስዩም፣ አባይና አስመላሽ ተደመሰሱ፤ ደብረጽዮን 24 ሰዓት ተሰጥቶታል

መከላከያ ሠራዊት ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ። ደብረጽዮን በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ካልሰጠ እንደሚደመሰስ ተነግሮታል።

የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ሥምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል።

የህወሐት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ የማያሸንፈውንና የማይወጣውን ውጊያ በአባት አርበኝነት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ጠቁመዋል።

ከዚህ ተግባሩ ሊቆጠብም ሆነ ከትላንት ሊማር ያልቻለው የጁንታው ቡድን በሰራዊታችን ላይ ውጊያ ከፍቶ በለኮሰው እሳት በመለብለብ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የህወሐት ቡድን አመራሮች ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ በመቀሌ በተካሄደው ዘመቻና ድምሰሳ ወቅት በ48 ሰዓት እጅ እንዲሰጡ ቢለመኑም፣ በማናለብኝነትና ትዕቢተኝነት እምቢ በማለት ወደ ጫካ መግባታቸውን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አስታውሰዋል።

በድጋሚም የአገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሽማግሌ ጭምር በመላክ እጅ እንዲሰጡ፣ ትጥቅ እንዲፈቱና ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ቢያስጠይቅም አሻፈረኝ ብለውና የያዙትን የጥበቃ ኃይል በመተማመን እንዲሁም “ተመልሰን እንነሳለን” በሚል የድሮ ብሂል ተሳስተው ያለ ዕድሜያቸው በዱር በገደሉ ተሸሽገዋል ብለዋል።

ዋሻዎችን በመጠቀምም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እይታ ውጪ ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉም ገልፀዋል።

ሆኖም ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው ጀግናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች በዛሬው ዕለት በጋራ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ቀደም ሲል ሰራዊቱን በማስመታት ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ፣ ሲያቅዱና ሲመሩ የነበሩ ቀንደኛ የጁንታው አመራሮች ከጥበቃ ሀይላቸው ጋር በነበረው ተኩስ ልውውጥ በውጊያ ላይ ከነጥበቃዎቻቸውና የጥበቃ ወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር መደምሰሳቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

 በነበረው ውጊያ ከጥበቃዎቻቸው ጋር አብረው የተደመሰሱ የጁንታው አመራሮች፣

1. ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረ እንዲሁም ውጊያውን የመረና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዘ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጠ፣

2. አስመላሽ ወልደሥላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበረ

3. አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበረ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዳ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች፦

1.  ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ

2.  ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣

3.  ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣

4.  ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ

5.  አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው  አሁንም በየዋሻው የተደበቁ የጁንታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

“ትርጉም ለሌለው የህወሐት ጠባቂ በመሆን ውድ ህይወታችሁን አትገብሩ፣ ከቻላችሁ ይዛችኋቸው፣ ካልቻላችሁ በሰላም ለሰራዊቱ እጅ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።

ከዚህ ሌላ የወንበዴው ህወሓት መሪ የነበረው ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ያለበት ዋሻ ውስጥ ከነጠባቂዎቹ በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ለመግሥት ካልሰጠ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለበት ዋሻ ውስጥ ከነጠባቂዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ እርምጃ እንደሚወስድበት አሳውቋል። (ኢዜአ)

ጎልጉል የድገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Slider Tagged With: abay tsehaye, asmelash, getachew assefa, operation dismantle tplf, sebhat nega, seyoum mesfin, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule