ትላንት የተደገደሉትን የህወሓት ቡድን አመራሮች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው መውሰድ እንደሚችሉ ብ/ጄ ተስፋዬ አያሌው በቪኦኤ ቀርበው ተናገረዋል። አመራሮቹ የተገደሉበት ቦታ ሩቅ እና በረሃ በመሆኑ መከላከያ የሁሉንም አስክሬን መልቀም እንደማይችልም አሳውቀዋል። ሰራዊቱም በእግሩ እየተጓዘ መሆኑ ገልፀዋል። በዚህ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት ህይወታቸው እያለፈ የሚገኘውን አካላት ገበሬዎች እየቀበሯቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ብ/ጄ ተስፋዬ ፥ "የአመራሮችን አስክሬን ብንችል ብናመጣው ደስ ይለን ነበር" ብለዋል። በተጨማሪ ፥ ትላንት የተገደሉት አመራሮች ፎቶና ቪድዮ እንደሚደርሳቸው ገልፀው ካስፈለገ ይህን መስጠት ፣ በሚዲያ ማስተላለፍ ይቻላል ነገርግን በሚዲያ ሰው ገደልን ብሎ ማሳየት ከኢትዮጵያ ባህል አንፃር የማይሄድ እና የእርስ በእርስም ስለሆነ ይህን ማድረጉ ተቀባይነት … [Read more...] about ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ
seyoum mesfin
“ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ስዩም፣ አባይና አስመላሽ ተደመሰሱ፤ ደብረጽዮን 24 ሰዓት ተሰጥቶታል መከላከያ ሠራዊት ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ። ደብረጽዮን በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ካልሰጠ እንደሚደመሰስ ተነግሮታል። የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ሥምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል። አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል። የህወሐት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ … [Read more...] about “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ
አዲሱ ህወሃት በአሮጌ አቁማዳ በትግራይ መቀሌ መሽገው የ13 አመት ልጅ እየመለመሉ ስልጠና ሲሰጡ የከረሙትና ትላንት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉት ሁለቱ ሙሰኛና የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ጄኔራሎች በፎቶው የሚታዩት ናቸው! ብ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ፤ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ሲመጣ “ተደምሪያለሁ” በማለት ጊዜ ገዝቶ፤ ሚስቱንና ሶስት ሴት ልጆቹን አሜሪካ ወስዶ፤ ቤት ገዝቶ፤ አመቻችቶ፤ እንዲሁም ከመጀመሪያ ሚስቱ የወለደው ዳንኤል የተባለውን ልጁ በካናዳ እንዲኖር ያደረገው ተክለብርሃን፤ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ወደ መቀሌ ሸሸ። ሁለት ትላልቅ ህንፃዎች በመገናኛ ወደ ሃያት በሚወስደው መንገድ ያሉት (ተገትረው የቀሩ) በኦሮሚያ በርካታ መሬቶች የሸጠ፣ ለበርካታ ዘመዶቹ በሃብት ጥግ ያደረሰ ሙሰኛ ነው! ሁለተኛው ብ/ጀነራል ኃ/ሥላሴ … [Read more...] about ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ