ትላንት የተደገደሉትን የህወሓት ቡድን አመራሮች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው መውሰድ እንደሚችሉ ብ/ጄ ተስፋዬ አያሌው በቪኦኤ ቀርበው ተናገረዋል።
አመራሮቹ የተገደሉበት ቦታ ሩቅ እና በረሃ በመሆኑ መከላከያ የሁሉንም አስክሬን መልቀም እንደማይችልም አሳውቀዋል።
ሰራዊቱም በእግሩ እየተጓዘ መሆኑ ገልፀዋል።
በዚህ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት ህይወታቸው እያለፈ የሚገኘውን አካላት ገበሬዎች እየቀበሯቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ብ/ጄ ተስፋዬ ፥ “የአመራሮችን አስክሬን ብንችል ብናመጣው ደስ ይለን ነበር” ብለዋል።
በተጨማሪ ፥ ትላንት የተገደሉት አመራሮች ፎቶና ቪድዮ እንደሚደርሳቸው ገልፀው ካስፈለገ ይህን መስጠት ፣ በሚዲያ ማስተላለፍ ይቻላል ነገርግን በሚዲያ ሰው ገደልን ብሎ ማሳየት ከኢትዮጵያ ባህል አንፃር የማይሄድ እና የእርስ በእርስም ስለሆነ ይህን ማድረጉ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተናግረዋል።
የህወሓት አመራሮች በእልህ እና በአልሸነፍም ባይነት እርሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ፣ በማያውቀው ጉዳይ ከነሱ ጋር የተሰለፈውን ወጣት ጠባቂዎቻቸውን እየጎዱ ነው ብለዋል።
ብ/ጄነራል ተስፋዬ ፥ “የአመራሮቹ አስክሬን እዛው ነው ያለው (ከተከዜ ወንዝ ዳርቻ) ፥ ቤተሰቦቻቸው ከፈለጉ እና እንሄዳለን ካሉ ከመቀሌ ጀምሮ እስከ ቆላ ተንቤን ያለው ሠራዊት ስላለ ከነሱ መረጃ መውሰድ እና አስክሬኑን መውሰድ ይችላሉ” ሲሉ ገልፀዋል።
ትላንት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍን ፣ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ፣ አቶ ኣስመላሽ ወልደስላሴ፣ ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ መደምሰሳቸውን እንደገለፀ ይታወሳል። (ቲክቫህ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply