• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል

December 8, 2020 01:05 am by Editor 1 Comment

ወንጀለኛው የህወሓት ጁንታ የንግድ ድርጅቶች በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸውን ምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ አዲሱ እጥፉ አስታወቁ። የሀገሪቱን ሀብት ከመበዝበር ወደ ውጭ ለማሸሽ መሳሪያ እንደነበሩም ጠቆሙ።

አቶ አዲሱ እጥፉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገ ለጹት፦ የህወሓት ጁንታው የንግድ ድርጅቶች በሀገ ሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ የከበደ ነው።ተቋማቱ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠርና በህገወጥ መንገድ በመዝረፍ የአገሪቱን ሀብት ወደውጭ ሲያሸሹ ነበር።

የንግድ ተቋማት አሰራራቸው ብቻ ሳይሆን አጀማ መራቸውም ህገ ወጥ እንደነበሩ የገለፁት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት በማናለብኝነት ሀገሪቱን ሲመዘብሩ መቆየታቸውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቀዋል።

ጁንታው የፖለቲካ የበላይነት ለመያዝ የኢኮኖሚ የበላይነት ማረጋገጥ አለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት መሆኑን የተናገሩት ባለሙያው፣ በህገወጥ ተቋማቱ አማካኝነት ይህንን እምነቱን ተጨባጭ ለማድረግ የሄደበት መንገድ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አመልክተዋል።

ተቋማቱ በተጠና መልክ የተሳሰሩና በሰንሰለት መልክ የተደራጁ ሁሉም ለአንድ አላማ የተቋቋሙ እንደሆኑ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አንዱ ተቋም የአንደኛው ግብዓት አቅራቢ በመሆን ለሌላው በመሸጥና ኢኮኖሚውን በተለያየ መልኩ በመቆጣጠር የበላይነቱን ተቆጣጥረውት ቆይተዋል ብለዋል።

የህወሓት ጁንታ በነበረው የፖለቲካ የበላይነት ተጠቅሞ የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ ሆን ተብሎ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ እንዲሆኑ ማድረጉን ያመለከቱት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ያለገደብ የባንክ ብድ ርና የውጭ ምንዛሪ ያገኙ እንደነበር ገልፀው” ይህ ደግሞ ከሌላ ህጋዊ ድርጅቶች በተለየ መልኩ ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩ እድል እንዲሰጣቸው አስታውቀዋል።

የድርጅቱ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ በ2003 ዓ.ም ለአሜሪካ ድምፅ “የህወሓት ተቋም የሆነው ኤፈርት የአገሪቱ ቁጥር አንድ ሀብታም ድርጅት ነው” ማለታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ተቋማቱ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንኮች በብድር መልክ የወሰዷቸው ገንዘቦች እንደማይመልሱና የተበላሸ ብድር እየተባለ እንደሚመክን ያስረዱት አቶ አዲሱ፣ እነዚህ ተቋማት አትራፊ መሆናቸውና እጅግ ትልልቅ ገንዘቦች ማዘዋወራቸው እየታወቀ ተቋማቱ ኪሳራ ላይ ናቸው በሚል የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ እንዲቀሩና የመንግሥት ገንዘብ እንዲመዘበር ሆን ተብሎ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።

በህጉ መሰረት አንድ ተቋም መክሰሩ ታውቆ የተበደረው ብድር መመለስ እንደማይችል ሲረጋገጥ ብድሩ ተበላሸ እንደሚሰኝ ገልፀው ፣የህወሓት ጁንታው ተቋማት ግን አትራፊ መሆናቸው እየታወቀ የተበደሩትን ገንዘብ እንዳይመልሱ የተለያዩ ምክንያቶች ያቀርቡ እንደነበር ጠቁመዋል።

ጤነኛ የንግድ ህግ ተከትለው ይሰሩ የነበሩ ተቋማት በቡድኑ ህገወጥ ድርጅቶች በደረሰባቸው ጫና ከገበያ እንደወጡና በአንፃሩ ደግሞ በቡድኑ የሚተዳደሩ ተቋ ማት በአገሪቱ ግዙፍ የገንዘብ ዝውውር የሚያደርጉና በህገወጥ መንገድ የከበሩ እንደነበሩ አስታውቀዋል። ተቋማቱ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ገንዘብ ወደውጭ በማሸሽ ሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲገጥማትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ገልጸዋል።

ከአመሰራረታቸው ጀምሮ ህገወጥ በሆነ መልኩ የተቋቋሙት የህወሓት ጁንታው የንግድ ተቋማት በአገሪቱ ላይ የፈጠሩት ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል። ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የንግድ ሥራ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ያሉት አቶ አዲሱ ተቋማቱ በ1952 ዓ.ም የወጣውን አገራዊ ህግ በሚፃረር መልኩ የተቋቋሙና በህገወጥ መልኩ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው ብለዋል።

በመንግሥት ቁጥራቸው 34 የሚሆኑ የንግድ ተቋማት ተለይተው የተገለፁ መሆኑንና ጉዳያቸው በህግ ሂደት ላይ ቢሆንም የድርጅቱ የንግድ ተቋማት ግን ቁጥራቸው ከዚያ እጅግ እንደሚበልጥና በመንግሥት በኩል በትክክል ተለይተው ከህገወጥ ተግባራቸው ሊገቱ እንደሚገባም አመልክተዋል ።ተቋማቱ ለመንግሥት ግብር በስርዓት የማይከፍሉና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መሬቶችን በመውሰድ እና መልሶ በመሸጥ ለህገወጥ ተግባራቸው መጠቀሚያ ያደርጉ እንደነበር ጠቁመዋል።

ዓለምአቀፉ የፋይናንስ ሀቀኝነት ድርጅት በፈረንጆች በ2010 ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት የጁንታው ድርጅቶች ከአገሪቱ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ በማሸሽ በውጭ ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ባንኮች ላይ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና እስካሁን ይፋ የተደረገ ሪፖርት ብቻ መሰረት በማድረግ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ከ36 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ በተለያዩ አገራት ባንኮች ላይ ማስቀመጣቸውን አስታውቀዋል።

ተቋማቱ የአገሪቱ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመሸጥና ወደውጭ በማሸሽ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ሲፈጽሙ መቆየታቸውንም የገለጹት አቶ አዲሱ፣ ተቋማቱ ገለልተኛ በሆነ መልኩ ተጣርተው አገሪቱ ላይ ያደረሱትን ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በመመርመር ተጠያቂ ሊደረጉ እንደሚገባ አመልክተዋል። (ተገኝ ብሩ፣ ኢፕድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: effort, getachew assefa, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    December 18, 2020 01:47 pm at 1:47 pm

    ውድ ጎልጒል፣
    የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት በህወኃት ላይ የያዛቸውን የዝርፊያ፣ የግድያና የቶርች መረጃዎችን በተለይ ለውጭ እርዳታ ሰጭዎች አጠናቅሮ ማሠራጨት አለበት! ይህን የሚያዘጋጅ ኮሚቴ አቋቊሞ (እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋም ቢሳተፉበት) ትልቅ ሥራ ነው። ህወኃት ኃፍረት የማያውቀው ነውና ታሪኮቹን ዘቅዝቆ ዶ/ር ዐቢይን ዲክታተር ሲላቸው እየሰማን ነው፤ ባዘጋጀው ኔትወርክ እየተበተበ ነው። ኢትዮጵያውያን ስለ ህወኃት የማያውቁት ብዙ የለም፤ መረጃ የሚያስፈልገው ለውጭው ኮምዩኒቲ ነው!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule