
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን ጨምሮ ለ20 ተጠርጣሪዎች የእስር ፍርድ ቤት በፈቀደው ዋስትና ላይ እና ፖሊስ በጠየቀው የምርመራ ቀናት ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 27/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በነበረው ችሎት በዋስትናው ጉዳይ እና ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጹሁፍ ያቀረበውን የመልስ መልስ ተቀብሏል።
ዛሬ በነበረው ችሎት ማናቸውም ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን የ6ቱ ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ተናግረዋል።
በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉ 15 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ 2ቱ በዛሬው ችሎት የተወከሉት፤ በ3 ጠበቆች መሆኑንም ገልጸዋል። ቀሪዎቹ 3 ተጠርጣሪዎች በራሳቸው የሚከራከሩ ናቸው ብለዋል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ማክሰኞ በነበረው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ ተጨማሪ 8 ተጠርጣሪዎች በሶዶ ማረሚያ ቤት በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸው ይታወሳል።
በማክሰኞው የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ወደ ሶዶ ከተማ ማረሚያ ቤት ከተወሰዱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የቀድሞው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና የዞኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ ዩሃንስ ይገኙበታል። (Ethiopia Insider)
Who is in the picture and who takes credit for it?