“አርቲስት ቴዲ አፍሮ የጥምቀት በዓልን ወደ አደባባይ ወጥቶ ማክበሩን የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል” ሲሉ ነው በርካቶች ባሰራጩት አስተያየት “ነገሩ ምንድን ነው?” ሲሉ ግራ በመጋባት ማብራሪያ የጠየቁ ቢበዙም፣ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው የነበሩ አካላት ላይ ውግዘት መድረሱን ያስታወሱም አልታጡም። የሚያደርገውን በማወቅ፣ ጊዜና ሰዓት በማስላት በሚያከናውናቸው ተግባሮቹ ስኬት የለኩት “ቴዲ ሳያውቅ ይህን ለበሰ ለማለት ያስቸግራል” ሲሉም ተድምጠዋል። የዲዛይን ችሎታ አካታ እንዳያዘች የሚነገርላት ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በጥንቃቄ እንደምትሞሽረው የሚያውቁ “ይህን እንደ ስህተት መቀበል ያዳግታል” ሲሉ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደሚሹ አመልክተዋል። ፎቶውን በማጋራት ሰፋ ያለ አስተያት ከጻፉት መካከል ቶማስ ጃጃው በቴሌግራም ገጹ “እንደ ማንኛውም በብርሃነ ጥምቀቱ እንደሚያምን … [Read more...] about የተዘቀዘቀ መስቀል?!
teddy afro
“ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
ቴዲ አፍሮን የሚወዱት ሰዎች እጅግ በርካታ የመሆናቸውን ያህል ጥቂት የማይባሉ ደግሞ አምርረው ይጠሉታል። ደጋፊዎቹ በተለይ በዘመነ ትህነግ በድፍረት የሚያዜማቸውን እያነሱ “የአንድ ሰው ሠራዊት” ይሉታል። የሚጠሉት ደግሞ ቴዲ “ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?” ቢል እንኳን “ይሄ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ፣ …” በማለት የስድብ ናዳ ያወርዱበታል። ቴዲ በትህነግ ዘመን ግልጽ ግፎች ደርሰውበታል። የሙዚቃ ኮንሰርቶቹ ያለ ምንም ካሣና ቅድመ ማስታወቂያ ቲኬት ከተሸጠ በኋላ በተደጋጋሚ ተሰርዘውበታል። የጎዳና ተዳዳሪ ገድለሃል በሚል ክስ ለእስር በተዳረገበት ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበ ቁጥር ያለማቋረጥ እያለቀሰ ንጹሕ መሆኑን ለማሳመን ሞክሯል። ከእስር የተለቀቀበት አግባብም በራሱ ብዙ ሊያስብል የሚችል ነው። በአገራችን የለውጥ መዓበል በተነሳበት ወቅት ጃዋርን ጨምሮ አክራሪና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች … [Read more...] about “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
“ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ?
ቴዲ ወደ ባህርዳር ሲያቀና "እንዘምራለን" ማለቱን ያስተውሏል! የጉዞውን አላማ እንዲያ ሲል ነበር ረቂቅ በሆነ መንገድ የገልጸው። በመዘመር እና በመዝፈን መሃል ያለውን ጥልቅ ልዩነት የማይረዳ ብቻ ነው ለሰሞኑ "አሲዮ ቤሌማ" እጅ የሚሰጠው። ከኮንሰርቱ ጀርባ ያለው "የፍቅር ጉዞ" የሚለው መሪ ቃል ውስጥም ከውቅያኖስ የጠለቀ መልዕክት አለ። ይህንን ቃል የተረዳ ብቻ ነው የተልእኮውን ስኬት ሊያበስር የሚችለው። ዝግጅቱ ኮንሰርት እንጂ ዳንኪራ አይደለም። ሁለት ወይንም ሶስት ሰዓት ብቻ የፈጀ ኮንሰርት። ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር የነገሰበት ኮንሰርት። ትንሳዔን አብሳሪ ኮንሰርት። መዝሙር ውስጥ መልዕክት አለ። የሚያንጽ፣ የሚያነቃቃ መልዕክት። መላው በጠፋበት በዚህ ወቅት፤ ኢትዮጵያ የምትሻው የተስፋ ቃል ብቻ የሚደሰኩርላትን ሳይሆን ድልድይ የሚዘርጋላትን ሰው ነው። ጥላቻ ነግሷል። በሃገራችን ስር … [Read more...] about “ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ?