መለስ ዜናዊ ከስሙ ጀምሮ ሁሉ ነገሩ የውሸት ወይም ፌክ ነው። ላደረሰብን ግፍ እንክሰሰው እንኳን ብንል በየትኛው ስሙ ነው ፍርድ ቤት የምናቆመው የነበረው? ደግነቱ ከዚህ ሁሉ በፊት ወደ ዕረፍቱ ሄዶ እኛንም አሳረፈን። መለስ የዕውቀት ችግር አልነበረውም፤ ዕድሜ ለኢትዮጵያ ከሥር መሠረቱ በነጻ አስተምራዋለች። ንጉሡም ሰው ነው፤ ነገ ሀገር ይጠቅማል ብለው ሸልመውታል ይባላል። ግን ያልታከመና ሥር የሰደደ የበታችነት ስሜት የነበረው፣ አስተሳሰቡ ደሃ የሆነ ሰው ነበር። በዚህ ደሃ አስተሳሰቡ ነበር ኢትዮጵያን ለመምራት ሥልጣን ኮርቻ ላይ የተፈናጠጠው። ሥልጣን፣ ሃብት፣ ድሎት፣ ወዘተ ቢመጣም አስተሳሰብ ደሃ ከሆነ ችግሩ ውስብስብና መፍትሔ ዓልባ ነው የሚሆነው። መለስ ኢትዮጵያን በጣም ነበር የሚጠላት፤ ለማፍረስ ይፈልግ ነበር ለማለት ብዙም አያስደፍርም። ነገርግን ልክ እንደ … [Read more...] about በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ
ginbot 20
ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
በራሳቸው ሕዝብ ላይ ሲደርስ ሰማይ የሚደፋባቸውና ዓለም ሁሉ አብሯቸው እንዲያለቅስ የሚፈልጉት ምዕራባውያን በሌሎች ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ ቅንጣት ታህል ግድ አይላቸውም። አንድ ማሳያ እንጥቀስ፤ የዛሬ 80 ዓመት አካባቢ ጃፓን የአሜሪካንን ድንበር ጥሳ ከሐዋይ ደሴቶች አንደኛዋ ላይ የሚገኘውን ወታደራዊውን የፐርል ወደብ ገና በጠዋቱ በድንገት አጠቃች፤ በወደቡ ላይ የነበሩት 8 መርከቦች ጉዳት ደረሰባቸው፤ አራቱ ሰጠሙ፤ በአጠቃላይ ወደ 20 የሚደርሱ መርከቦችና ጀልባዎች ከጥቅም ውጪ ሆኑ፤ ከ300 በላይ የሚሆኑ አውሮፕላኖች፣ ጀቶችና ሔሊኮፕተሮች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፤ ከሁሉ በላይ ከ2,400 በላይ የሚሆኑ ባሕረኞች፣ ወታደሮችና ሰላማዊ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆሰሉ። በቀጣዩ ቀን ዲሴምበር 8፣ 1941 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት … [Read more...] about ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
ግንቦት 20 በህግ የታወቀ የህዝብ በዓል ነው?
በእኛ ሀገር የሚከበሩ የህዝብ በዓላት በህግ የታወቁ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩ መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለምአቀፍ ተቋማት እንዲሁም ኢምባሲዎች እና የቆንፅላ ጽ/ቤቶችም የእኛን ሕዝብ በዓላቶች እንዲያከብሯቸው ይጠበቃል። ምክንያቱም በዓላቱን ማክበር ህዝብን ማክበር ከዚያም ሲያልፍ ሀገሪቱ ሉዓላዊ መሆኗን ማረጋገጥ ነውና። እነዚህ በዓላት የዘመን መለወጫ በዓል (መስከረም 1)፣ የዓደዋ ድል መታሰቢያ ቀን (የካቲት 23)፣ የድል ቀን (ሚያዝያ 27)፣ የዓለም የሠራተኞች ቀን፣ መስቀል (መስከረም 17)፣ ጥምቀት (ጥር 11)፣ የክርስቶስ ልደት(ታህሳስ 29/28) እንዲሁም ቀናቸው በየዓመቱ የሚቀያር ስቅለት፣ ትንሳዔ፣ ፣ኢድ አልአድሃ፣ መውሊድና ኢድ አል ፈጥር ናቸው። በእነዚህ ቀናት እንደሁኔታው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ … [Read more...] about ግንቦት 20 በህግ የታወቀ የህዝብ በዓል ነው?



