ዛሬ የትግራይ ክልልን እንዲያስተዳድሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቀመጡት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚታወቁባቸው የሽፍትነት ዘመን ንግግራቸው መካከል “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” የሚለው ነው። ዛሬ ደግሞ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው አራተኛውን ሙሌት ቦታው ድረስ በመሄድ አክብረዋል። ያኔ ተሸጧል ሲባል አብረው ያመኑና ዜናውን ያራገቡ መልስ ሊሰጡበት የሚገባው ጥያቄ፤ 1ኛ. ግድቡ አልተሸጠም ነበር ወይም 2ኛ. የተሸጠው ተመልሷል ወይም 3ኛ ይህ አሁን ሞልቶ የሚታየው ግድብ ከተሸጠ በኋላ በአዲስ መልክ የተሠራ ነው። መልሱን ለአቶ ጌታቸውና ደጋፊዎቻቸው እንተውና ኢትዮ12 ስለ አራተኛው ሙሌት በተመለከተ የዘገበውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግሥት የመፈረም ፍላጎት … [Read more...] about “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
abay dam
ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?
የአባይ ግድብን በተመለከተ ዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ” ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲፈርሙ ተጽዕኖ እየተደረጉና ወደ ፊርማውም እየሄዱ ነው የሚል እንደምታ ያለው ዘገባ ባወጣ ጊዜ አንድ የጎልጉል ተከታታይ የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ የአጸፋ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በወቅቱ የውሃ ሃብት ባለሙያ መሆናቸውን ጠቅሰው February 6, 2020 “ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ” በሚል ርዕስ ምላሻቸውን የጻፉት ግለሰብ ያኔ የጻፉት መጣጥፍ በድጋሚ እንዲወጣላቸውና በወቅቱ ዋዜማ ሬዲዮ አለኝ ያለውን ሰነድ ይፋ እንዲደርግ ጥያቄ አቅርበዋል። ትላንት መከናወኑ ከተነገረለት 4ኛው የውሃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ጥያቄውን ማቅረቡ አሳማኝ ሆኖ ስላገኘነው ለሚዲው የጸሐፊውን መልዕክት እያደረስን መጣጥፉን ከዚህ በታች በድጋሚ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?
ዳግማዊ ዓድዋ – የዓባይ ግድብ በጸጥታው ምክርቤት
የታላቁ የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ውዝግብ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የነበረውን የአፍሪካ ኅብረት ሚና አጣጥለው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት መፍትሔ ለመሻት የሄዱት የታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ግብፅና ሱዳን፣ የጠበቁትን ሳያገኙ በዓለም አደባባይ ሚናውን ወዳረከሱት የአፍሪካ ኅብረት እንዲመለሱ ተመክረው ተሸኝተዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ላይ ሥጋት አለን ከማለት አልፈው የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳያቸው እንደሆነ ሲገልጹ የከረሙት ግብፅና ሱዳን፣ እንደ አዲስ በፈጠሩት ጥምረት በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም. ጉዳዩን ወደ ተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ወስደውት የነበረ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ ቅድሚያ ለአኅጉራዊ የመፍትሔ አማራጭ ቅድሚያ በመስጠት በግድቡ ላይ ያለው ልዩነት በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት መፍትሔ እንዲያገኝ በመወሰኑ፣ ላለፈው አንድ ዓመት በዚሁ … [Read more...] about ዳግማዊ ዓድዋ – የዓባይ ግድብ በጸጥታው ምክርቤት