• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?

September 10, 2023 01:58 am by Editor Leave a Comment

የአባይ ግድብን በተመለከተ ዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ” ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲፈርሙ ተጽዕኖ እየተደረጉና ወደ ፊርማውም እየሄዱ ነው የሚል እንደምታ ያለው ዘገባ ባወጣ ጊዜ አንድ የጎልጉል ተከታታይ የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ የአጸፋ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በወቅቱ የውሃ ሃብት ባለሙያ መሆናቸውን ጠቅሰው February 6, 2020 “ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ” በሚል ርዕስ ምላሻቸውን የጻፉት ግለሰብ ያኔ የጻፉት መጣጥፍ በድጋሚ እንዲወጣላቸውና በወቅቱ ዋዜማ ሬዲዮ አለኝ ያለውን ሰነድ ይፋ እንዲደርግ ጥያቄ አቅርበዋል። ትላንት መከናወኑ ከተነገረለት 4ኛው የውሃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ጥያቄውን ማቅረቡ አሳማኝ ሆኖ ስላገኘነው ለሚዲው የጸሐፊውን መልዕክት እያደረስን መጣጥፉን ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል።

ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ

የውሃ ሃብት ባለሙያ ነኝ፤ የግድቡ ጉዳይ ቀጥታ ከሙያዬ ጋር ባይገናኝም እንደዜጋ ሁኔታውን በቅርብ እከታተላለሁ፤ ፖለቲካንም እንዲሁ። የዋዜማን ሰዎች ዋዜማ ሳትሆኑ ነው የማውቃችሁ፤ ካገር ከመውጣታችሁ በፊት ማለቴ ነው። የማውቃችሁም በግል ሳይሆን እንደማንኛውም የሚዲያ ተጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ እናንተ አታውቁኝም። አሁንም ዋዜማን እከታተላለሁ። ከዳያስፖራ ከሚመነጩት የዜና ዘገባዎችና መረጃዎች የእናንተ በተሻለ መጠን ተዓማኒነትና ሥርዓት የያዘ ነው ብዬ ስለማምን አነባችኋለሁ።

“ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” በሚል ርዕስ ያወጣችሁትን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ዘገባው እንደሚለው ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን ሰነድ ስምምነት እንድትፈርም ኢትዮጵያ ግፊት እየተደረገባት እንደሆነ፤ ይህም “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ መሆኑን”፤ ረቂቅ ሰነዱ እጃችሁ እንደገባ፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ላይ ተጽዕኖ እያደረጉባቸው እንደሆነ፣ ኢትዮጵያ ካልፈረመች ከአሜሪካ የምታገኘው ድጋፍ መስተጓጎል እንደሚገጥመው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በገደምዳሜ መጠቆማቸው” በእናንት በኩል ግምት እንዳለ፣ ወዘተ የሚያትት ነው።

ዜናው መረጃ የሚያስተላለፍ መሆን ሲገባው ግምት፣ መላምት፣ ጠማማነትና ምኞትን የሚገልጽ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህ ይልቅ ግን የዘነጋው አንድ ትልቅ እውነታ አለ – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስምምነቱ እንዳይፈረም መመሪያ ስለመስጠታቸው ነው።

ሰኞ ዕለት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በተወካዮች ም/ቤት በኩል ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ረቂቁን ተመለከቱ፣ የትራምፕን፣ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት እና የአሜሪካውን የገንዘብ ሚ/ር አነጋገሩ፤ ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ በስልክ ንግግራቸው ተረዱ፤ ረቂቁ እንዳይፈረም ትዕዛዝ ሰጡ። እንዲያውም በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚሰጣቸው የሙያ ምክር ጠቃሚ መሆኑን በመጥቀስ ምስጋና ሁሉ አቅርበው ነበር። ይህ ሊያስመሰግናቸውና እናንተም ባወጣችሁት ጽሁፍ መግለጽ የሚገባችሁ ነበር። የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም ነው ያሉት!

የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትራችን ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺም ረቡዕ ዕለት ለሚዲያ ሰዎች ሲናገሩ “በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን በወንዙ የመጠቀም መብት በዘላቂነት በማያስጠብቅ ሁኔታ አንድም ቃል ከተካተተ ኢትዮጵያ” አትፈርምም ነው ያሉት። ይህንንም ጨምረዋል፤ “የግድቡ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅን በሚመለከት ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ በተለይም ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት የሦስቱን ሀገራት ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ተካሂዷል” ነው ያሉት። መቼም ዐቢይን ባታምኗቸው ዶ/ር ስለሺን የምትጠራጠሯቸው አይመስለኝም።

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ ኢትዮጵያን ባለዕዳ የሚያደርግ ስምምነት ሊፈረም ነው ብሎ መናገሩ የሚዲያችሁን ተዓማኒነት ትልቅ ጥያቄ ላይ ጥሎታል፤ በተለይ ለእኔ። ሌሎቹንም ዘገባዎቻችሁን በጥንቃቄና በዓይነቁራኛ እንዳነብ ያስገደደኝ ሆኗል። በተለይ እናንተ ከለውጡ ጋር በተያያዘ በአገር በቀል መፍትሔ ፍለጋ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረጋችሁ ያላችሁ በዚህ መልኩ ይህንን ዘገባ ማውጣታችሁ “ውይ እንደነ እንትና ዋዜማም …” አስብሎኛል። ልድገመውና – ረቂቁ አልተፈረምም፤ እንዳይፈረም ዶ/ር ዐቢይ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። እንደ መሪ ይህ ትክክለኛና ተጠቃሽ ተግባር ነው።

እናንተ በዘገባችሁ ሌላው ያከላችሁት ነገር ኢትዮጵያ ተጽዕኖ እየተደረገባት ነው፤ እነ ዶ/ር ዐቢይም ሊፈርሙ እየተዘጋጁ ነው የሚል ነው። ለዚህም ያቀረባችሁት መላምት ኢትዮጵያ ካልፈረመች አሜሪካ የምትሰጠውን ዕርዳታ መያዣ አድርጋባታለች የሚል ነው። ሌላውና ውሃ የማይቋጥረው መላምታችሁ ትራምፕ ለፍልስጤምና እስራኤል ያቀረቡት የሰላም ሃሳብ “በመላው የዓረቡ አለም ተቀባይነት ባለማግኘቱ” ግብጽ የአረቡ ዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆኗ ይህንን ሰነድ አረቡ ዓለም እንዲቀበል ካግባባች “(ለ)ውለታዋ የህዳሴ ግድብ እንደ እጅ መንሻ” እንደቀረበላት ነው።

ይህንን በጣም የወረደ አመክንዮ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሲጀመር የትራምፕን የሰላም ዕቅድ “መላው የዓረቡ አለም” አልተቃወመውም። ሳዑዲ አረቢያ፣ አረብ ኤሜሬትስ፣ ግብጽ፣ ኳታርና ሞሮኮ ከአዎንታዊ አስተያየት እስከ ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይ ሳዑዲ አረቢያ ከመቼውም በተለየ መልኩ እስራኤልን በመደገፍ መቆሟ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል።

ሌላውና ዋንኛው ነጥብ በዚህ የፍልስጤም ተወካይ ወይም መሃሙድ አባስ በሌሎበት ትራምፕና የእስራኤሉ ጠ/ሚ/ር ኔታንያሁ ብቻቸውን ይፋ ያደረጉት “ፕላን” ፍልስጤምን ታሳቢ ያላደረገ የፖለቲካ ቁማር ነው። ኔታኒያሁ ከሙስና እና ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ትልቅ ክስ ተመሥርቶባቸው ግራ ገብቷቸዋል። ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ደግሞ አገር አቀፍ ምርጫ ይጠብቃቸዋል። ለሕዝባቸው “የሚሸጡት” የምርጫ ሸቀጥ ያስፈልጋቸዋል። ለዚህም ደግሞ እስራኤልን በጭፍን ከሚደግፍ ፕላን የተሻለ አይኖርም።  

ትራምፕ በዩክሬይን ጉዳይ ከፍተኛ ቅሌት ገጥሟቸው የውጭ ጉዳይ አመራር ላይ ዜሮ ናቸው የሚለው ቁጥር የጨመረበት ወቅት ላይ ናቸው። እጅግ ውስብስብ የሆነውን የፍልስጤምና እስራኤል ጉዳይ ለመፍታት ከመድፈር አልፎ የሰላም ዕቅድ ይዘው ብቅ ማለታቸው የውጭ ጉዳይ ፖለቲካ ላይ በሳል ናቸው ከማስባል ባለፈ ለዚህ ዓመቱ (የፈረንጆች) የአሜሪካ ምርጫ ጥሩ ደጋፊ እንዲያስገኝላቸው ታልሞ የተሠራ ነው። እሳቸውም የራሳቸውን ዕቅድ “የክፍለዘመኑ ስምምነት” በማለት የጠሩት ያለምክንያት አይደለም።

ሌላው ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ ዕቅድ ለትራምፕ የዚህ ዓመት ምርጫ ትልቅ ድጋፍ የሚያሰጣቸው ነው፤ በተለይ በ2016ቱ ምርጫ በጭፍን ለደገፏቸው የኢቫንጀሊካል (ወንጌላውያን) ክርስቲያኖች። እነዚህ ኢቫንጀሊካሎች ለእስራኤል ጭፍን ድጋፍ ያላቸው ከመሆን በተጨማሪ ለትራምፕ ምርጫ ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ አድራጊዎችም ናቸው። ያለፈውን ዓይነት ድጋፍ በዚህኛው የምርጫ ዘመቻ ለማግኘት ይህንን መሰሉ የመካከለኛው ምስራቅ ዕቅድ ማውጣት ወሳኝ ነው። በዚህ ላይ የትራምፕ ምክትል ማይክ ፔንስና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፔዎ ተጠቃሽ ኢቫንጀሊካል ናቸው።

ይህ የፖለቲካ ጥቅም ከማስገኘት ያላለፈ ምኞት ያለውንና ፍልስጤምን ያላሳተፈ ዕቅድ የተቃወሙትን አረብ አገራት ለማሳመን ከግብጽ ይልቅ ባልተለመደ ሁኔታ ለእስራኤል ልዩ ድጋፍ እያደረገች ያለችውና ዕቅዱን የደገፈችው ሳዑዲ አረቢያ የተሻለችና ዋንኛ ተመራጭ ነች።

ለማንኛውም እናንተ እጃችን ገብቷል ያላችሁትን ረቂቅ፥ የስምምነት ሰነድ ሆኖ እንዳይፈረም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መመሪያ ሰጥተውበታል። ይህ መጠቀስ የሚገባው ትልቅ ሥራ ነው። ዕቅዱን የተቃወሙትን የአረብ አገራት ለማሳመን ግብጽ የተሻለች ነች፤ ይህንንም ካደረገች የአባይን ግድብ ስምምነት እሷን እንዲጠቅም ተደርጎ እንዲወሰን ይደረጋል የሚለውም የዓለምን በተለይም የአሜሪካንና የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ያላገናዘበ ስንኩል “ትንታኔ” ነው።

ዋዜማዎች እንደ አንዳንድ ስም አይጠሬ ጭፍን ሚዲያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው።

ባለሙያው ነኝ       

ከዝግጅት ክፍሉ፤ ለዚህ ጽሁፍ የአጸፋ ምላሽ እንዲሰጡ ለዋዜማ ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል መልዕክት ልከን ነበር። ለሕዝብ የሚቀርብ ምላሽ ሳይሆን ለጎልጉል ሚዲያ ብቻ በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። የጻፉት መልዕክት ወደ ሕዝብ እንዳይቀርብ ስላሉን አንብበን አስቀምጠነዋል።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: abay dam, GERD, operation dismantle tplf, Wazema Radio

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule