የአባይ ግድብን በተመለከተ ዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ” ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲፈርሙ ተጽዕኖ እየተደረጉና ወደ ፊርማውም እየሄዱ ነው የሚል እንደምታ ያለው ዘገባ ባወጣ ጊዜ አንድ የጎልጉል ተከታታይ የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ የአጸፋ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በወቅቱ የውሃ ሃብት ባለሙያ መሆናቸውን ጠቅሰው February 6, 2020 “ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ” በሚል ርዕስ ምላሻቸውን የጻፉት ግለሰብ ያኔ የጻፉት መጣጥፍ በድጋሚ እንዲወጣላቸውና በወቅቱ ዋዜማ ሬዲዮ አለኝ ያለውን ሰነድ ይፋ እንዲደርግ ጥያቄ አቅርበዋል። ትላንት መከናወኑ ከተነገረለት 4ኛው የውሃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ጥያቄውን ማቅረቡ አሳማኝ ሆኖ ስላገኘነው ለሚዲው የጸሐፊውን መልዕክት እያደረስን መጣጥፉን ከዚህ በታች በድጋሚ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?