የታላቁ የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ውዝግብ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የነበረውን የአፍሪካ ኅብረት ሚና አጣጥለው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት መፍትሔ ለመሻት የሄዱት የታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ግብፅና ሱዳን፣ የጠበቁትን ሳያገኙ በዓለም አደባባይ ሚናውን ወዳረከሱት የአፍሪካ ኅብረት እንዲመለሱ ተመክረው ተሸኝተዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ላይ ሥጋት አለን ከማለት አልፈው የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳያቸው እንደሆነ ሲገልጹ የከረሙት ግብፅና ሱዳን፣ እንደ አዲስ በፈጠሩት ጥምረት በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም. ጉዳዩን ወደ ተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ወስደውት የነበረ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ ቅድሚያ ለአኅጉራዊ የመፍትሔ አማራጭ ቅድሚያ በመስጠት በግድቡ ላይ ያለው ልዩነት በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት መፍትሔ እንዲያገኝ በመወሰኑ፣ ላለፈው አንድ ዓመት በዚሁ … [Read more...] about ዳግማዊ ዓድዋ – የዓባይ ግድብ በጸጥታው ምክርቤት