በኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዷል። ተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ተሳትፈዋል። የምርጫው ሒደት ባብዛኛው ከተጽዕኖ የራቀ ነው ሊባል ይችላል። ተቃዋሚዎች በቂ የአየር ጊዜ ተሰጥቷው ፕሮግራማቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ተደርገዋል። በርካታ ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ተካሂዷል። ለገዢው ፓርቲ እንደ በፊቱ ጊዜያት ፕሮፓጋንዳውን እንዲያሰራጭ እጥፍ ጊዜ አልተሰጠውም። ከተቃዋሚዎቹ እኩል በሚባል መልኩ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ነው የተደረገው። ከሁሉ በላይ በደኅንነቱ መሥሪያ በጀት ተበጅቶለት ኮሮጆ ለመገልበጥ የሚሠራ ኃይል የለም። ምርጫ ቦርድም ነጻና ተዓማኒነቱን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። በምርጫው ቀን መራጩ ሕዝብ ነጸ በሚባል መልኩ ሲመርጥ ውሏል። በተለይ በከተሞች አካባቢ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚያስብል ተግባር እንዳልተፈጸመ ታይቷል። … [Read more...] about ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ