• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ

June 26, 2021 03:20 am by Editor 1 Comment

 በኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዷል። ተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ተሳትፈዋል። የምርጫው ሒደት ባብዛኛው ከተጽዕኖ የራቀ ነው ሊባል ይችላል። ተቃዋሚዎች በቂ የአየር ጊዜ ተሰጥቷው ፕሮግራማቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ተደርገዋል።

በርካታ ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ተካሂዷል። ለገዢው ፓርቲ እንደ በፊቱ ጊዜያት ፕሮፓጋንዳውን እንዲያሰራጭ እጥፍ ጊዜ አልተሰጠውም። ከተቃዋሚዎቹ እኩል በሚባል መልኩ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ነው የተደረገው።

ከሁሉ በላይ በደኅንነቱ መሥሪያ በጀት ተበጅቶለት ኮሮጆ ለመገልበጥ የሚሠራ ኃይል የለም። ምርጫ ቦርድም ነጻና ተዓማኒነቱን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። በምርጫው ቀን መራጩ ሕዝብ ነጸ በሚባል መልኩ ሲመርጥ ውሏል። በተለይ በከተሞች አካባቢ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚያስብል ተግባር እንዳልተፈጸመ ታይቷል።  

ማነው ምርጫውን ያሸነፈው? የፌዴራሉን መንግሥት የሚመሠርተው ማነው? በየክልሉስ?

ለልማትና ለዕድገት ነው የቆምኩትና ምረጡኝ ካለው ገዢው ፓርቲ ጀምሮ በዘር የተደራጁ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ተሳትፈዋል። የሁሉንም ማኒፌስቶ አንብቦና ተረድቶ ብቻ ሳይሆን ማንነታቸውንም ጭምር መርምሮ ሕዝብ ድምፁን ሰጥቷል።

ሕገመንግሥቱን እቀይራለሁ፤ የዘር ፖለቲካን ወደ ዜጋ ፖለቲካ እቀይራለሁ፤ ኢትዮጵያን ከክልል ክፍፍል ወደ አራት ቀጣናዊ ክፍልፍሎሽ ዝቅ በማድረግ አዲስ ካርታ እፈጥራለሁ፤ የኢትዮጵያን ወደ 50 ክልል (ሃምሳ ክልል) እከፋፍላታለሁ፤ ለአዲስ አበባ የቤት ችግር በመጪው 5ዓመታት መፍትሔ እሰጣለሁ፤ በምርጫው የምወዳደረው የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ነው፤ ኢትዮጵያ በመጪው 10ዓመት የጦር ጀቶችን አምርታ ለአፍሪካ አገራት እንድትሸጥ አደርጋለሁ፤ ወዘተ ያልተሰማ ተስፋና የምርጫ ቃልኪዳን የለም ማለት ይቻላል።

ሕዝብ ሰምቷል። ውሳኔው ምን ይሆን? የገዢውን ፓርቲ ማማለያ አሽቀንጥሮ በመጣል ድምፁን ከተቃዋሚዎቹ ለአንዱ ሰጥቶ በዝረራ እንዲያሸንፍ ቢያደርግስ? ወይም ተቃዋሚዎቹን በሙሉ “ከእጅ አይሻል ዶማ ናችሁ” በማለት ገዢው ፓርቲ መንግሥት እንዲመሠርት የዝረራ አሸናፊ ቢያደርገውስ? በዚህ ምርጫ ያልታሰበ የዝረራ ውጤት ቢከሰትስ ምን እንላለን?

ዴሞክራሲ ሰፍኖባታል በሚባልባት አሜሪካም ሆነ አንድ ፓርቲ ከራሱ ጋር ተወዳድሮ በሚያሸንፍባቸው ኮሙኒስታዊ አገራት በዝረራ (landslide) ማሸነፍ ያልተለመደ አይደለም።

የፖለቲካ ምሁራኑ በዝረራ ማሸነፍ የምርጫውን ተዓማኒነት ጥያቄ ላይ ይጥለዋል ይላሉ። እንዲያውም ከ2/3ኛ በላይ ድምፅ ማግኘት ጥርጣሬ የሚያስነሳ ነው በማለት ይናገራሉ። ምክንያቱም በነጻና ተዓማኒ ምርጫ ይህ ያልተለመደ በመሆኑ ነው ይላሉ።

ሌሎች ደግሞ አዲስ የዴሞክራሲ ፈር ሲቀድ ያልተለመደ የምርጫ ውጤት ማምጣት ሊከሰት የሚችል ነው በማለት ይሞግታሉ። በ2012 (እኤአ) በግብፅ በተደረገ ምርጫ የሙስሊም ወንድማማች ፓርቲ 70% ድምፅ ማግኘቱን ለአብነት ይጠቅሳሉ። በመሆኑም ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ባልዳበረባቸው ምርጫዎች ከ60-80% ማሸነፍ በጣም የሚጠበቅ ነው፤ የዝረራ ውጤት እንዲያውም ሊከሰት የሚችል ነው ይላሉ። እርስበርሳቸው የተከፋፈሉና ያልተደራጁ ተቃዋሚዎች ለዝረራ ውጤት ዋንኛ ምክንያት ይሆናሉ የሚል አስተያየት ይሰጣሉ።

በ2009 በሰሜን ኮሪያ ገዢው ፓርቲ በ99.98%፤ በ2014 እንዲሁ በ99.97% እና በ2019 በተካሄደው ደግሞ 99.99% “አሸንፏል”። ይህ ገዢው ፓርቲ ራሱን ብቻ ተወዳዳሪ አድርጎ ያቀረበበት የሚባል ምርጫ ውጤት ነው።

በሌላ በኩል በፈረንሳይ በ2002 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዣክ ሺራክ ተፎካካሪያቸውን ዢን-ማሪ ለፔንን በ82% በዝረራ አሸንፈዋቸዋል።

የምርጫ ዴሞክራሲ ዳብሮባታል በምትባለው አሜሪካ የዝረራ ድል በተደጋጋሚ ተከስቷል።ለፕሬዚዳንትነት በተደረገው ምርጫ በ1964ዓም ሊንደን ቢ ጆንሰን በ90.33% ሲያሸንፉ፤ በ1980 ሮናልድ ሬጋን ተፎካካሪቸው ጂሚ ካርተርን በ90.89%፤ ሪቻርድ ኒክሰን ደግሞ ጆርጅ ማክጋቨርንን በ1972 በተካሄደው ምርጫ በ96.65% አሸንፈዋል።

በቀጣይ ለዳግም ምርጫ የተወዳደሩት ሬጋን በ1984 ተፎካካሪያቸው ዋልተር ሞንዴልን በ97.58%፤ እንዲሁም በ1936 በተደረገ ምርጫ ፍራንክሊን ሩዝቬልት ተፎካካሪያቸውን በ98.49% ዘርረዋቸዋል።    

በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ የሚሆነው የአገራችን ምርጫ ውጤትስ? ማነው አሸናፊው? ውጤቱስ ምን ዓይነት ይሆን? በዝረራ የተገኘ ውጤት ከሆነ ምላሻችን ምን ይሆናል? ምርጫ ቦርድን መጠራጠር? ወይስ ውጤቱን የሕዝብ ድምፅ መሆኑን አምነን መቀበል?

ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ልምምድ የምንፈልገው ብቻ ሲያሸነፍ የምንቀበለው ሳይሆን የምንቃወመውም ሲያሸነፍ በፀጋ የመቀበል ልምምድን ይጠይቃል። ለፕሬዚዳንት ኬኔዲ ድምፁን እንዳልሰጠ የሚታወቅ ሰው በወቅቱ እንዳለው “አልረጥኩዎትም፤ ነገር ግን ቢሮውን ስለማከብር ፕሬዚዳንት ብዬ እጠራዎታለሁ” ብሏል። ተመሳሳይ ባለፀጋነት ከአገራችን የምርጫ ውጤት ይጠበቃል። የተመረጠው ወይም ያልተመረጠው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ድምፄ ዋጋ አለው በማለት በትጋት ድምጹን የሰጠው መራጭ ላይ በማድረግ ውጤቱን ማክበር ለአገር ይበጃል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial, Middle Column Tagged With: election 2013, election 2021, landslide victory

Reader Interactions

Comments

  1. Qomchei Ambaw says

    June 26, 2021 03:45 am at 3:45 am

    Why do you misinform people? The PP missed not one, not two but 34 of the intra party debates in the weeks leading the election. And surprisingly it was just a no show after the invites were sent to them. Do you ask why? Why would a political party shy away from debates? Of all time during election month? That tells you a lot but amongst other things it was certain there is another way to win the election, we wonder what that is! But then it was revealed on election day what that was – pure cheating as seen openly in many of the polling stations. Some polling stations in addis didn’t open until mid-day – cause some none-tity didn’t with the electoral register or some half cooked excuse. There were shortage ballot paper in the middle of the election – all deliberate deeds to frustrate the voting public. Keep the citizens in the queue till late night.

    So Golgool stop this half assed reporting and pretending to be neutral. Reading the stories about elections that parties won “be-zirera” it tell us that yiu are preparing the ground for what is to come.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule