• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!

June 28, 2018 11:30 pm by Editor 2 Comments

ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤

በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ የደኅንነት ኃይሉን ትብትብ በወጉ ለምትረዱና ለምትገነዘቡ፤ በተለያዩ የአገሪቱ የልማት ተቋማት ላይ የሚፈጸመውን የኢኮኖሚ አሻጥር በውል ለምትከታተሉ፤ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚሸረቡ ተንኮሎችን ለምታጤኑ፤ ለውጡ እንዲኮላሽና አገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ እንድትገባ በተሸናፊነት ውስጥ ሆነው ለጥፋት የሚመደበውን በጀት ለምትሰሙ …. በጥቅሉ አሁን እየሆነ ያለውን ለምታስተውሉ አገር ወዳድ ዜጎች የጎልጉል ዝግጅት ክፍል አጭር መልዕክት አለው።

እየሆነ ባለው የለውጥ ሂደት ቀልብን ሰብስቦ በማሰብ፣ ልብን በመጠበቅ፣ በየመኖሪያና በየሥራው ቦታ፣ በአለፍንበትና ባገደምነበት ሁሉ የአገራችን ዘበኛ ልንሆን ይገባል። በተራ ብሽⶥቅና እንካ ሰላንቲያ የሚገኝ ትርፍ የለምና እንዲህ ያለውን የሰንፎች መንገድ ካልተውን ተሸናፊዎች አጀንዳና እጅ ተመልሰን እንወድቃለን።

አሁን ጊዜው ዋጋ የሚከፈልበት ነው። አሁን ጊዜው ከቀድሞው መስዋዕትነት በላይ ዋጋ ለመክፈል የምንምልበት ነው። ፍቅር ያሸንፋል ሲባል፣ ከክፉ መንገዳቸው የተመለሱትን ከነጸጸታቸው መቀብል እንጂ መግፋት አይደለምና በአገር ደረጃ ለታወጀው የሰላም መንገድ፣ የድል መንገድ፣ የዕርቅ መንገድ ክፉዎች የሚወድቁበት ወጥመድ ይህ የፍቅር መንገድ ብቻ በመሆኑ በማስተዋል እንራመድ።

በየድረገጹና በየማኅበራዊ ሚዲያ የሚታየው፣ የሚነበበው ተራ የብሽሽቅ ፖለቲካ ብስጭት ውስጥ ያሉትን የበለጠ እንዲያመርሩ፤ ያልገቡትን ደግሞ ወደዚያው እንዲገቡ የሚገፋፋ ነው ሰከን እንበል። ያለንበት ሁኔታ “ተራው የኔ ነው” የሚያስብል ሳይሆን አገር ለማዳን የምንጨነቅበት፤ የምንችለውን ሁሉ ቀንና ሌሊት የምሠራበት ነው። በርግጥ ላለፉት በርካታ ዓመታት ለአገራችን ስንለፋ ከነበርን ይህ የታየው ለውጥ ፍሬ እንዲያፈራ ይበልጡኑ የምንተጋበት ጊዜ አሁን ነው።

በስሜት እየተንቦጫረቅን ከተቀመጠው ዋንኛ የድል መንገድ የምንወጣ ከሆነ መፈረካከስ ይሆናልና በጥሞና ወደ ድልና መደመር የሚወስደንን ጎዳና አንልቀቅ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለለውጡ መቀጠል ሁላችንም በተግባር የሚጠበቅብንን እንወጣ። አሁን የጥፋት ኃይሎች ሆነው ብቅ ያሉት ያለ ከልካይ እንደመዥገር ተጣበቀው ሲጠቧት የነበረችውን አገር እንዲለቅቁ እየተደረጉ ነውና በቀላሉ ለመልቀቅ ፈቃደኞች ይሆናሉ ብሎ መገመት የዋህነት ነው። ይህ ለውጥ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመኖርን ትርጉም ፍንትው አድርጎ ያሳየ የመሆኑን ያህል ለነዚህ ኃይሎች ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው የሆነባቸው። ስለዚህ በለውጡ ሒደት በፍጥነት ወደፊት ከምንገሰግስ ይልቅ እሣት ወደ ማጥፋት እንድንሄድና በሒደትም መንገዳችንን እንድንስት እንደሚያደርጉን ጠንቅን ልንገነዘብ ያስፈልጋል።

እነዚህ የተቀናጁ፣ የተደራጁ፣ ለዘመናት ሲዘርፉት በነበረው በርካታ የገንዘብ ኃይል የሚደገፉ፣ ለአገር ደኅንነት ቅንጣት ያህል የማይጨንቃቸው ኃይሎችን በስሜት፣ በግብታዊነት፣ በበቀል፣ በእልህና በንዴት ሳይሆን አካሄዳቸውን በማጥናት፣ በብልሃትና በትጋት ነቅተን የምንታገልበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ነን። የተጀመረው የለውጥና የተሃድሶ ጉዞ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑን በመገንዘብ ለድል እናምርር።

ስለዚህ ባለሙያዎችም አገራችሁን የምትረዱበት ወቅት አሁን ነውና ኢትዮጵያን በማዳኑ የቀና መንገድ ያለ አንዳች ይጥቅም የበኩላችሁን ተወጡ። አገራችሁ ትፈልጋችኋለች፤ የትኛውም ዓይነት የሙያ ልምድ ይሆን ትምህርት በአሁኔ ጊዜ ያስፈልጋልና በሁሉም መስክ ተደመሩ። በሚዲያ ላይ ያላችሁ በማኅበራዊ ድረገጾችም ይሁን በድረገጾችና በመካነ ጦማሮች ላይ የምትሳተፉ፣ አስተያየት የምትሰጡ የብሽሽቅ ፖለቲካውን ባካችሁን አርግቡት፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚበልጠውና ይቅርባችሁ። የዓመታት ግፍ በርግጥ ብዙ እንዲባል ያስገድዳል ግን ደግሞ ውጤቱ መልሶ እኛኑ የሚጎዳ ከሆነ መተዉ የተሻለ ይሆናል። አሁን እየጎላ የመጣውን የለውጥና የመኖር ተስፋ፣ ተመልሶ ኢትዮጵያዊ የመሆን ታላቅ ዕድል ለማፈራረስ የማይማስ ጉድጓድ የለምና ሁሉም ዘብ ይቁም!!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Filed Under: Editorial Tagged With: abiy ahmed, eprdf, Left Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Lemma says

    July 1, 2018 10:26 pm at 10:26 pm

    Yibarkachihu. BeTam Teqami melikt new. TPLF is now like a grotesque rabid dog. It barks and bites at any thing, including, at last, its own tail to finish itsel off.
    Degagmachehu hizbun mikeru. Bertu Golguloch.

    Reply
  2. Ezira says

    July 2, 2018 07:27 pm at 7:27 pm

    ትክክል ነው። አንዲት የተቆጣች ድመት የመዉጫውን በር ከዘጋህባት ያላት አማራጭ ከአንት ላይ መጎመር ነው። ስለዚህ ከምንም በላይ አገራችን ኢትዮጵያን መጠበቅና ለ27 ዓመት ከተቀበረችበት መቃብር ፈንቅላ እየወጣች ነችና …ይሄንን የመቃበሯን ድንጋይ ላይዋ ላይ ልናነሳላት የምንችለው በጋራ ሆነን ጠ/ር ዶ/ር አብይ እንዳሉት በመደመርና በመደመር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይጠብቅ! ይባርክ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule