በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ ሪዞርት ሽንት ቤት ውስጥ አሳማ ያስቀምጣል። አሳማዋንም የከንፈር ቀለም (ሊፕስቲክ) ቀብቶ እንደ ሰው አስመስሎ። ዓላማው ሌላ ሳይሆን ፕራንክ ነበር። ክስተቱ የሪዞርቱን ባለቤት ፕራንክ አድርጎ ቢያልፍም ከዚያ በኋላ ግን አሳማ የከንፈር ቀለም ቢቀባ እንደ አሳማ መጮኹ (ኦይንክ ማድረጉ)፣ ጭቃ ላይ መንከባለሉ፣ አሰሱንም ገሰሱንም መብላቱ፣ … ባጠቃላይ አሳማነቱ አይቀርም ማለት ነው በሚል አባባል ተተካ። ከዚያም በ90ዎቹ ለቴክሳስ ሀገረግዢነት ይወዳደሩ የነበሩት አን ሪቻርድስ አባባሉን ተጠቀሙበት። ትልቁ ቡሽ በምርጫ ውድድር በነበሩበት ጊዜ የቡሽ አስተዳደር ለውጥ እንደማያመጣ አን ሲናገሩ “ዌል የአሳማዋን ከንፈር ሊፕስቲክ ቀብቶ ሞኒካ ነሽ ሊሏት ይቻላሉ፤ ግን አሳማነቷ ፈጽሞ አይቀየርም” ነበር … [Read more...] about “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
red terror
የኢትዮጵያውያን ህይወት ዋጋ ምን ያህል ወርዷል?
በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ ሰው ህይወት ክቡር ነው። ከዚያም አልፎ ህይወት ያለውን ነገር ሁሉ በከንቱ አለማጥፋት በተፈጥሮ ህሊናችን ውስጥ ህግ ሆኖ ስለተቀመጠም ነው የሰው ብቻ ሳይሆን የሌላም ፍጥረት ህይወቱ አለአግባብ በጭካኔ ሲቀጠፍ የሚዘገንነን። የሰውን ህይወት ለማጥፋት መጀመርያ የራስን ህሊና ፍርድ መጣስና ማቆሸሽን ይጠይቃል። ዛሬ በኢትዮጵያ በየቀኑ በጭካኔ የሚቀጠፉ ለጋ ወጣቶች፣ ማምለጥ የማይችሉ ህፃናት፣ አዛውንት አባቶችና እናቶችን ለሚመመለከት፣ ብሎም ለሚያስብ ንፁህ ህሊና ላለው እረፍት የሚነሳ ነው። በተለይ ባለፉት አምሳ ዓመታት በግፍ የጠፋው ኢትዮጵያውያን ህይወት እጅግ የሚዘገንን ነው። አዎ አባቶቻችን የውጭ ወራሪን ለመከላከልና በነፃነት ለመኖር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አምባገነን የሆኑ የየአካባቢው መሳፍንት ግዛታቸውንና ሃብታቸውን ለማስፋት በሚያደርጉት … [Read more...] about የኢትዮጵያውያን ህይወት ዋጋ ምን ያህል ወርዷል?


