በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ ሪዞርት ሽንት ቤት ውስጥ አሳማ ያስቀምጣል። አሳማዋንም የከንፈር ቀለም (ሊፕስቲክ) ቀብቶ እንደ ሰው አስመስሎ። ዓላማው ሌላ ሳይሆን ፕራንክ ነበር። ክስተቱ የሪዞርቱን ባለቤት ፕራንክ አድርጎ ቢያልፍም ከዚያ በኋላ ግን አሳማ የከንፈር ቀለም ቢቀባ እንደ አሳማ መጮኹ (ኦይንክ ማድረጉ)፣ ጭቃ ላይ መንከባለሉ፣ አሰሱንም ገሰሱንም መብላቱ፣ … ባጠቃላይ አሳማነቱ አይቀርም ማለት ነው በሚል አባባል ተተካ። ከዚያም በ90ዎቹ ለቴክሳስ ሀገረግዢነት ይወዳደሩ የነበሩት አን ሪቻርድስ አባባሉን ተጠቀሙበት። ትልቁ ቡሽ በምርጫ ውድድር በነበሩበት ጊዜ የቡሽ አስተዳደር ለውጥ እንደማያመጣ አን ሲናገሩ “ዌል የአሳማዋን ከንፈር ሊፕስቲክ ቀብቶ ሞኒካ ነሽ ሊሏት ይቻላሉ፤ ግን አሳማነቷ ፈጽሞ አይቀየርም” ነበር … [Read more...] about “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ

