• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር

December 15, 2017 12:29 pm by Editor Leave a Comment

  • መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረደባቸው

ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ  እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም። ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት እንደማትሆን የሆላንድ ፍትህ ሚኒስትር አስታወቁ።

አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም።

በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት አቃቢያን ህጎቹ እና የተበዳይ ጠበቆች በውሳኔው የደስታ ስሜት ታይቶባቸዋል።

ከ29 ኦክቶበር 2017 ጀምሮ ሲታይ የነበረው ይህ የፍርድ ሂደት የከሳሽ አቃቤ ህግንና የተከሳሽ ጠበቆችን ክርክር ለወር ያህል ሲያዳምጥ ቆይቶ፣ ውሳኔ ለመስጠት ከ3 ሳምንት በኋላ ቀጠሮ ይዞ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ከሁለት አመት በላይ የፈጀው ይህ በአይነቱ ለየት የሚለው፣ የአቶ እሸቱ አለሙ የምርመራ እና የክስ ሂደት አለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ ነበር። ፍርዱ በተሰጠበት በዛሬው እለትም በርካታ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች ወደ ችሎቱ ታድመዋል።

የ63 ዓመቱ እሸቱ አለሙ ከ120 የደርግ አባላት አንዱ ሲሆኑ፣ በ1970ዎቹ ቀይ ሽብር ዘመን ደርግን ወክለው የጎጃም ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ እንደነበሩ በችሎቱ ፊት ቢመሰክሩም የተመሰረተባቸውን የጦር ወንጀል ክስ ግን ሲቃወሙ ነበር።  

አስራ ሁለት ዓመት ፈጅቶ የነበረው የኢትዮጵያው የቀይ ሽብር ወንጀል ችሎት እ.ኤ.አ 2006 አቶ እሸቱ አለሙ ላይ በሌሉበት የሞት ፍርድ መወሰኑ አይዘነጋም።

በ1991 ኢህአዴግ ሃገሪቱን ሲቆጣጠር አቶ እሸቱ አለሙ ከነበሩበት ከቡልጋርያ ወደ ሆላንድ በመምጣት የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ  በ1992 የሆላንድ መኖርያ ወረቀት ያገኙ ሲሆን ከ5 አመት በኋላም የሃገሪቱ ዜጋ ሆነዋል። ግለሰቡ  በ2015 ክመኖርያ ቤታቸው ባላሰቡበት መንገድ ተይዘው ታሰሩ። ኦክቶበር 29, 2017 – በታሰሩ ከ 2 ዓመት በኋላ – ጉዳዩ በሄግ ችሎት መታየት ጀመረ።

በሆላንድ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ክስ በነሃሴ ወር 1978፣ በ75 ወጣቶች ግድያ (በቅዱስ ሚካኤል ቤተ–ክርስትያን ውስጥ ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ) በዘጠኝ ዜጎች ላይ የተደረገ ድብደባ እና የማሰቃየት ወንጀል እና በ321 ሰዎች ላይ በደረሰ ህገ–ወጥ እስራት የሚል ነው።

ለክሶቹ ክ3000 ገጽ ያላነሰ የጽሁፍ ማስረጃዎች፣ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስልሎች፣  ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ እና ከእንግሊዝ የተገኙ ከ30 በላይ የአይን ምስክሮች ( ከነዚህ ውስት ስምንቱ ምስክሮች ከካናዳ እና ከአሜሪካ ተጉዘው በሄግ ችሎት በመገኘት ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ሶስት ባለሙያዎች (ፕ/ር ጃን አቢንክ፣ ዶ/ር ካሳ እና ክፍሉ ታደሰ) በማስረጃነት ቀርበዋል።

የሆላንድ ፍትህ ሚንስትር በአቶ እሸቱ ላይ ክሱን ለመመስረት መነሻ የሆነው፤ እ.ኤ.አ. በ1998 ‘ፍራይ ኔደርላንድ‘ (ነጻ ኔዜርላንድ) በሚል መጽሄት ስለ ተከሳሹ የወጣ ወንጀል ነክ ጽሁፍ ነው። የሆላንድ አለም ዓቀፍ የወንጀል ምርመራ ቡድን ይህንን ጽሁፍ እንደተመለከተ ከ2009 ጀምሮ የአቶ እሸቱን ስልክ በመጥለፍ መከታተል እንደጀመረ አቃቤ ህግዋ ሚስ ኒኮል ፎገለንዛግ ተናግረዋል። 

ይህ ቡድን በ2012 ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የኢትዮጵያን መንግስት መረጃ ቢጠይቅም ከመንግስት በኩል ትብብር እንደተነፈገውም አቃቤ ህግዋ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ አልተባበርም ለማለቱ የሰጠው ምክንያት ጉዳዩ በሃገር ውስጥ በቀይ ሽብር የወንጀል ችሎት ስላለቀ መቶ አለቃ እሸቱን አሳልፋችሁ ስጡን በሚል ሰበብ ነው። በሆላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት ባለመኖሩ እና በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ መሰጠቱ ተጠርጣሪውን የማስረከቡ ጥያቄ ውድቅ ሊሆን ችሏል። 

አቶ እሸቱ አለሙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በተደመጠበት ወቅት “የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት” ብለው ነበር።  ማስረጃዎች ሲቀርቡና የምስክሮች ቃል መሰማት ሲጀምር በወቅቱ አስከፊ ነገር እንደተፈጸመ ተናግረው፣ ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ይቅርታ ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ  እሳቸው በወቅቱ  በፕሮፓጋንዳ ስራ እንደተሰማሩና አንድም  ሰው እንዳልገደሉ፣ ሰው እንዲገደልም ሆነ እንዲታሰር ትዕዛዝ እንዳልሰጡም ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

“ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ  የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዳደርግ ፍርድ ቤቱ እድል ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። 120 የደርግ አባላት  ውስጥ አንዱ ሆኜ ስለተሰራው ወንጀል አዝናለሁ። ግን የቀረቡብኝ ክሶች በሙሉ አልቀበልም” ብለዋል።

“የ4 ሺህ አመት ታሪክ ያላት ሃገራችን እንዳትፈራርስ አሜሪካንን እርዳታ ብንጠይቅ እንቢ ስላሉን ነው ወደ ሶቭየት ለመሄድ የተገደድነው። በወቅቱ የተደራጀው ሃይል ደርግ ብቻ ነው። ኢህአፓ ሃገሪቱን ሊያፈርስ በእብደት የተነሳ ሃይል ነበር። አቶ ክፍሉ ታደሰ የኢህአፓ አመራር የነበሩ በመሆናቸው ሃሳባቸው ነጻና ገለልተኛ ሊሆን አይችልም” ሲሉም ኢህአፓን በፍርድ ቤት ውሎ ኮንነዋል።

ሚ/ር ሳንደር አርት፤ የአቶ እሸቱ ጠበቃ የስም መደባለቅን እንደ ለመከራከርያ አቅርበው ነበር። ወንጀሉን የፈጸሙት ተከሳሹ እሸቱ አለሙ ሳይሆኑ ሌላ እሸቱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

“የግድያውን ትዕዛዝ የያዙ ፊርማዎች የሱ ሳይሆኑ የሌላ እሸቱ ናቸው። ምስክሮቹም የተናገሩት የሚያሳምን አይደለም። የፍርዱ ሂደት ፍትሃዊ አይደለም። አቶ እሸቱ አለሙ በ2015 ከቤታቸው ተወስደው ሲታሰሩ ወንጀለኝነታቸው አስቀድሞ እንደተረጋገጠ ይተቁማል” የሚል ነበር የመከራከርያቸው ጭብጥ።

ሌላው የጠበውቃው መከራከርያ ነጥብ ደግሞ “በ1978 ጎጃም ውስጥ የርስበርስ ውግያ ባለመካሄዱ ጉዳዩ የጦር ወንጀል ሊሆን አይችልም። ተራ ወንጀል ደግሞ በዚህ ችሎት መታየት አይችልም” የሚል ሲሆን፣ ቀደም ሲል አቶ እሸቱ አለሙ በጎጃም ኢህአፓ በተደራጀ መልክ ጦርነት ከፍቶ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ የተናገሩት ቃል ይህንን መከራከርያ ነጥብ አፍርሶታል።

የተበዳዮች ጠበቃ የሆኑት ሚስ ባርባራ ፋን ስትራተን – ለእያንዳንዱ ተበዳይ 200 ካሳ ኤሮ እንዲከፈል ፍርድ ቤቱን  ጠይቀዋል። ይህ ካሳ  ምንም እንኳን መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም ጥፋቱን ለማስረገጥ የተደረግ ተምሳሌታዊ (ሲምቦሊክ) ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት የሩዋንዳ እና  አንድ የኢራቅ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶ እንዳንዳቸው በ16ና 17 አመት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 

በሆላንድ የእድሜ ልክ እስራት የሚበየነው እጅግ አስከፊ ለሆነ ወንጀል ስለሆነ የተመክሮ መብትም የለውም። በሃገሪቱ እድሜልክ የተፈረደባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

አቶ እሸቱ አለሙ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች የነበሩ ሲሆን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው በውል በማይታወቅ ምክንያት ከአመታት በፊት ጥለዋቸው ወደ አሜሪካ በመሄድ ኑሯቸውን እዚያ አድርገዋል። በ2015 ከመታሰራቸው በፊት ሆላንዳዊት የትዳር ጓደኛቸው ጋር ይኖሩ ነበር።

የአቶ እሸቱ መያዝ እና መታሰር የዚህን ትውልድ  ትኩረት ባይስብም አሁን በሃገሪቱ እየተፈጸመ ላለው ተመሳሳይ ወንጀል አይን ከፋች ነው። በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ሰርቶ ከሃገር መውጣት እና መደበቅ እንደማይቻል ትምህርት ይሆናል።  የሆላንድ ፍትህ ሚኒስትር ያሉትም ይህንኑ ነው። “ሃገራችን ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት መሆን የለባትም!”

“እሸቱን ያየህ ተቀጣ!”

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law, Politics Tagged With: alemu, derg, eprdf, eprp, eshetu, Ethiopia, Left Column, meles, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule