ጊዜው የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሕመማቸውና ሞታቸው በፈረቃ ተቃዋሚንም ሆነ ደጋፊን ዥዋዥዌ ሲያጫውቱት የነበረ ጊዜ ሲሆን፤ በተቃዋሚ በኩል መለስ ሲሞቱ ቢሯቸው ክፍት ስለሚሆን፤ ስልጣን የሚጠብቃት እረኛ በማጣቷ፤ ከቤተመንግሥስት ወጥታ ስትበር በወጥመድ ለመያዝ ያሰፈሰፈ ይመስል ነበር ቢባል፤ ብዙ የሚያሳማ ግንዛቤ አይመስለኝም። በዚያው ሰሞንም ነበር ጥምረትና ኦነገ (የጄ/ል ከማል ገልቹም) አሊያንስ ፈጠሩ ተብሎ የተወራው፤ ነገር ግን ወሬውን አጣጥመን ሳንጨርስ፤ በነሃሴ 1ቀን 2004 ዓ.ም. የተቋቋመው ስብስብ (ሰንጠረዥ ‹‹ለ››) ውስጥ ሁለቱ የአሊያንስ አባል ድርጅቶች ተነጣጥለው ገብተው እናገኛቸዋለን፤ ከዚያ ወዲህም የአሊያንስ ጉዳይ ኮሽታው ይጠፋል። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about “… አንድ ኮማንዶ…”