በቀን 10/03/2012 ዓ.ም ተፅፎ በቁጥር 07642/2019 ወጪ የተደረገው አስገራሚ ደብዳቤ ይድረስ “ለህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ መቀሌ” በማለት ይጀምራል። ጉዳዩ፡- “ስለተጠራንበት ስብሰባ ይመለከታል” በማለት ይቀጥላል። የዚህን ደብዳቤ ትርጉምና ፋይዳ በቅጡ ለመረዳት የተፃፈበትን አውድ በአጭሩ መዳሰስ ያስፈልጋል። በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረው የላኩት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ሊቀመንበር አቶ አብዲርሃማን መሃመድ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው ዋና ጉዳዩ ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። ህወሓት በመቀሌው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው በሥልጣን ዘመኑ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የኦብነግ አመራሮች ናቸው። እንግዲህ በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ … [Read more...] about ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!
onlf
“… አንድ ኮማንዶ…”
ጊዜው የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሕመማቸውና ሞታቸው በፈረቃ ተቃዋሚንም ሆነ ደጋፊን ዥዋዥዌ ሲያጫውቱት የነበረ ጊዜ ሲሆን፤ በተቃዋሚ በኩል መለስ ሲሞቱ ቢሯቸው ክፍት ስለሚሆን፤ ስልጣን የሚጠብቃት እረኛ በማጣቷ፤ ከቤተመንግሥስት ወጥታ ስትበር በወጥመድ ለመያዝ ያሰፈሰፈ ይመስል ነበር ቢባል፤ ብዙ የሚያሳማ ግንዛቤ አይመስለኝም። በዚያው ሰሞንም ነበር ጥምረትና ኦነገ (የጄ/ል ከማል ገልቹም) አሊያንስ ፈጠሩ ተብሎ የተወራው፤ ነገር ግን ወሬውን አጣጥመን ሳንጨርስ፤ በነሃሴ 1ቀን 2004 ዓ.ም. የተቋቋመው ስብስብ (ሰንጠረዥ ‹‹ለ››) ውስጥ ሁለቱ የአሊያንስ አባል ድርጅቶች ተነጣጥለው ገብተው እናገኛቸዋለን፤ ከዚያ ወዲህም የአሊያንስ ጉዳይ ኮሽታው ይጠፋል። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about “… አንድ ኮማንዶ…”