በሳምንቱ መግቢያ ላይ በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ሃሳዊው የፌዴራሊስቶች መድረክ ከተሳታፊዎች የጀርባ መደብና ባህሪያት አንፃር ሦስት ገፅታ ነበረው። ገፅ አንድ:-የሙሰኞች ግንባር በቀዳሚው ገፅ ፊት አውራሪዎቹ ጋባዥና ተጋባዥ በሚል እንመልከታቸው። የጋባዡን ገፀ ባህሪ የሚላበሰው አባይ ፀሃዬ ሲሆን÷ የሙሰኞችን ግንባር የሚወክለው ተጋባዥ ደግሞ የቀድሞው ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘደንት የነበረው መንበረፀሐይ ታደሰ ነው። ሁለቱን ሙሰኞች የሚያመሳስላቸው ባህርይ ሥልጣንን የሃብት ምንጭ ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን የፈፀሙት ምዝበራ ጉዳት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑ ነው። አንዱ ፕሮጀክት አምካኝ ሌላው የፍትሕ ሥርዓቱን በአደባባይ የቀበረ መሆኑ የተለየ ያደረጋቸዋል። አባይ ፀሃዬ 77 ቢሊዮን ብር የስኳር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክት ብር እንደ ሸንኮራ አገዳ ምጥጥ አድረጎ ኮርፖሬሽኑን ቀፎውን ያስቀረ … [Read more...] about የመቀሌው መድረክ ትዝብት እና የሦስቱ ገፅ ግንባር ትራጆ ኮሚዴ
federalist meeting
ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!
በቀን 10/03/2012 ዓ.ም ተፅፎ በቁጥር 07642/2019 ወጪ የተደረገው አስገራሚ ደብዳቤ ይድረስ “ለህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ መቀሌ” በማለት ይጀምራል። ጉዳዩ፡- “ስለተጠራንበት ስብሰባ ይመለከታል” በማለት ይቀጥላል። የዚህን ደብዳቤ ትርጉምና ፋይዳ በቅጡ ለመረዳት የተፃፈበትን አውድ በአጭሩ መዳሰስ ያስፈልጋል። በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረው የላኩት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ሊቀመንበር አቶ አብዲርሃማን መሃመድ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው ዋና ጉዳዩ ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። ህወሓት በመቀሌው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው በሥልጣን ዘመኑ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የኦብነግ አመራሮች ናቸው። እንግዲህ በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ … [Read more...] about ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!
“አበሉን ክፈሉና መልሱት”፤ የህወሓት የመቀሌ ስብሰባ ቅሌት
የአገው ማኅበረሰብ ተወካይ አልላከም የህወሓት መሪዎች ኢትዮጵያን እናድን በሚል ማምታቻ ቃል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፌደራሊስት ኃይሎች ያሏቸውንና ጫሚሶወችን ጋብዘዋል። ከእነኚህ ተጋባዥ ሰዎች አብዛኛዎቹ 1) የሚከፈላቸውን አበል እንጂ የህወሃት ያረጀና ያፈጀ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀሳብ ምን እንደሆነ አያውቁም2) በኢትዮጵያ ፖሊቲካም ሆነ ኢኮኖሚ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ያልነበሩ ናቸው3) የህወሃት ስሪቶች እንደ መሆናቸው መጠን ወደፊትም ተጽእኖ መፍጠር ቀርቶ ቤተሰባቸውን ሊያሳምኑ አይችሉም4) እስከካሁን ባለው መረጃ ኦብነግ፣ ኦነግ፣ ሲአንና በፕሮፌሰር መረራ የሚመራው ኦፌኮ ግብዣውን ተቀብለው አልሄዱም። በአጠቃላይ ህወሃት እያደረገ ያለው አልሞትኩም፣ አልበሰበስኩም ትግል የትግራይን በጀት በአበል ስም መበተን፣ መስጠትና መቀበል ካልሆነ በቀር የሚያመጣው አንድ ውጤት የለም። … [Read more...] about “አበሉን ክፈሉና መልሱት”፤ የህወሓት የመቀሌ ስብሰባ ቅሌት