• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመቀሌው መድረክ ትዝብት እና የሦስቱ ገፅ ግንባር ትራጆ ኮሚዴ

December 9, 2019 11:45 pm by Editor Leave a Comment

በሳምንቱ መግቢያ ላይ በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ሃሳዊው የፌዴራሊስቶች መድረክ ከተሳታፊዎች የጀርባ መደብና ባህሪያት አንፃር ሦስት ገፅታ ነበረው።

ገፅ አንድ:-የሙሰኞች ግንባር

በቀዳሚው ገፅ ፊት አውራሪዎቹ ጋባዥና ተጋባዥ በሚል እንመልከታቸው። የጋባዡን ገፀ ባህሪ የሚላበሰው አባይ ፀሃዬ ሲሆን÷ የሙሰኞችን ግንባር የሚወክለው ተጋባዥ ደግሞ የቀድሞው ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘደንት የነበረው መንበረፀሐይ ታደሰ ነው።

ሁለቱን ሙሰኞች የሚያመሳስላቸው ባህርይ ሥልጣንን የሃብት ምንጭ ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን የፈፀሙት ምዝበራ ጉዳት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑ ነው። አንዱ ፕሮጀክት አምካኝ ሌላው የፍትሕ ሥርዓቱን በአደባባይ የቀበረ መሆኑ የተለየ ያደረጋቸዋል።

አባይ ፀሃዬ 77 ቢሊዮን ብር የስኳር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክት ብር እንደ ሸንኮራ አገዳ ምጥጥ አድረጎ ኮርፖሬሽኑን ቀፎውን ያስቀረ ሰው ነው።

መንበረፀሐይ ታደሰ ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ምክትልም ሆነ ዋና ፕሬዝዳንት እያለ የፍትህ ሥርዓቱን በካሽ ወደመቀመቅ የከተተ የፍትህ ነቀዝ እንደሆነ የሥራ ፕሮፋይሉ ላይ ይነበባል።

በተለይም በ1993 ዓ/ም የስዬ አብርሃን የሙስና ክስ በተመለከተ የያኔዋ ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተጠርጣሪውን [አቶ ስዬን] በዋስ ስትለቅ ÷ ከሕግ በላይ የሆነው የመለስ ዜናዊ የብረት ክንድ በዳኛ መንበረፀሐይ ላይ አርፎ “በይግባኝ ሥም” የስዬ አብርሃ የዋስትና መብት የተከለከለው በዛሬው የፖለቲካ አክቲቪስት በያኔው ዳኛ መንበረፀሐይ በኩል ነበር።

ህወሃት ይሄን ውለታውን ቆጥሮ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ ሰበር ሰሚ ልዮ ችሎት ከዛም ወደ ምክትልና ሙሉ ፕሬዝዳንትነት ድረስ የደረሰ ሹመት ሊያገኝ ችላሏል። በአጭሩ መንበረ የህወሃት ሥርዓታዊ የአልቀልባ ልጅ ልንለው እንችላለን። በሥልጣን ዘመኑ በአንድ ጉዳይ [case] ላይ ከሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ቢዝነስ መቀበሉን ያውቅበት ነበር። ሰበር ሰሚ ችሎት ላይ ካዝናው የተራቆተውን ባለሃብት ቤት ይቁጠረው።

በመጨረሻዎቹ የሥልጣን ዘመኑ በሙስና ቅሌት መባለግ ያበዛው ዳኛ መንበረፀሐይ ታደሠ ይህ አልበቃ ብሎት ለፍትህ ሥርዓቱ ማሻሻያ በሚል የተበጀተውን በጀት በፕሮጀክት ጥናት ስም ከጀሌዎቹ ጋር ቀርጥፎ በመብላቱ ከዚህ ቀደም የዋለው ውለታ ተቆጥሮለት በክብር ለጡረታ የበቃ የህወሃት ሥርዓታዊ የአንቀልባ ልጅ ነው።

እንግዲህ በአባይ ፀሐዬ ጋባዥነት ነበር ይሄ ሰው “ፌዴራሊዝሙን እንታደገው÷ ሕገመንግሥቱንም ከመፍረስ አደጋ እንጠብቀው” ሲል በመቀሌው መድረክ ላይ ወረቀት ያቀረበው።

ትላንት እሱ ሲያጨማልቀው የኖረው የፍትህ ሥርዓት ዳግም እንዲመለስ÷ እሱ፣ አባይ ፀሐዬና መሰሎቹ ቀሪ ዘመናቸውን በተጨማሪ የሀገር ሀብት ምዝበራ ለማሳለፍ መቀሌ ከትመው ‘የእንትናቸው ማበሻ’ አድርገውት በኖሩት ሕገመንግሥት ስም ምለው ሲገዘቱ ሰንብተዋል። መቼስ ምኞት ባይከለከልም÷  ያ-ጊዜ ላይመለስ የተቀበረ መሆኑ ሊገባቸው ይገባ ነበር። እነ ሞት እምቢ – የሙሰኞች ግንባር! የሚያውቁት ሃቅ ቢሆንም በአደባባይ እንንገራቸው÷ ዛሬም የሚንከባለል የክስ መጥሪያ እንዳለ ለሙሰኞቹ ግንባር ማስታወስ ሳያስፈልግ አይቀርም።

ገፅ ሁለት:- የአኩራፊዎች ግንባር

በሁለተኛው ገፅ የሚታዮት የመድረኩ ተሳታፋዎች አኩራፊ -ምንዱባን ናቸው። ህወሃትን ተከትለው መቀሌ የሚመላለሱ ከስብሃት ነጋ ፓርቲ ቀለብ የሚሰፈርላቸው ምንዱባን ይገኙበታል። በዚህ ምድብ ውስጥ እንደ አሰፋ ወዳጆ ያሉ የአዕምሮ ስልቦች ቢኖሩም÷ በፓርቲ ደረጃ ጫሚሶዎች ከፊት ይሰለፋሉ።

የአየለ ጫሚሶ የግል ንብረት የሆነው ‘ቅንጅት’ም ሆነ የባልና ሚስት ሃብት የሆነው የመስፍን በዙ ፓርቲ – ‘መኢብን’  የራሳቸው ፖለቲካ ፕሮግራም ባይኖራቸውም “የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ነን” የሚሉ ናቸው። አየለ ጫሚሶ የ1997ቱን ቅንጅት ፕሮግራም ቃል በቃል የወረሰ በመሆኑ በምን ተዓምር ከስብሃት ነጋ ጎን ተቀምጦ “ፌዴራሊስት ነን” እንዳለ እሱና ‘ውድብ’ ብቻ ሳይሆኑ እኛም እናውቃለን።

እሱም ሆነ መሰሎቹ መቀሌ የሚያመላልሳቸው ከመጋቢት/2010 ወዲህ ያለው የማዕከላዊ መንግሥቱ አመራር ፊት የነሳቸው በመሆኑ አኩራፊ በመሆናቸው ነው ። እናም ለቀድሞው ቀለብ ሰፋሪያቸው የዋለ ያደረ ታማኝነታቸውን ይዘው ‘ውድብ አቤቱ የዕለት እንጀራችንን አትንሽን’ በሚል የመቀሌው መድረክ ላይ ታድመዋል።

ህወሃትና ጫሚሶዎች በዓላማም ሆነ በግብ ባይዛመዱ ለማዕከላዊው መንግሥት ባላቸው ወቅታዊ ኩርፊያ በአንድ እንዲሰለፉ አድጓቸዋል። ይሄን ሰልፍ ነው እንግዲህ እነደብረፂዮን ‘መስመርዩ ኃይልና’ የሚሉት እኛ ግን በስብሃት ነጋ አባባል ሰልፍ የኃይል ምንጭ ነው ከተባለ ‘ጫሚሶ ሓይልና’ ብለን እናልፈዋለን።

እናም የመቀሌው መድረክ ሁለተኛው ገፅ ሲገለጥ የአኩራፊዎች ግንባር ሆኖ ይገኛል። አኩራፊው ኃይል በከፋዮ ፍላጎት ይወሰናል ። አሁን ቤተመንግሥት ያለው አመራር ለጫሚሶዎቹ ደህና ከፋይ ቢሆን ውድብን እየረገሙ ብልፅግናን እያሞገሱ አሰላለፋቸውን ለማሳመር ያን ያህል አያስጨንቃቸውም ። የኩርፊያው ምንጭ ህዝባዊነት ሳይሆን ጥቅመኝነት ነው። ሸገር ላይ የተሻለ ከፋይ እስኪገኝ የአኩራፊዎች ግንባር ቤዙን መቀሌ ላይ አድርጎ ይቆያል።  ህወሃት በበኩሏ ግንባሩን “የፌዴራሊስቶች ኃይል’ በሚል በ”ድምፀ ወያኔ” ፕሮፖጋንዳዋን ትሰራበታለች።

አንድ ድርጅት በፖለቲካ ሃሳቢ ሲያርጥ ምን እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ህወሃትን እንግዲህ ይሄ ድርጅት የፖለቲካ ሃሳብ ለአረጡ [Climacteric] ፓርቲዎች ማሳያ ሆኖ የሚቀርብ ነው። የመቀሌው መድረክ ያስረገጠልን ሃቅ ይሄንን ነው።

ሦስተኛው ገፅ:- ፌዴ-ስኪዎች

የመቀሌው ሃሳዊ የፌዴራሊስቶች መድረክ ብዙ ጉድ ቢያሳየንም ሦስተኛው ገፅ ደግሞ ለየት ይላል። በዚህኛው ገፅ ጌታቸው ረዳ ጋባዡን ሲወክል እነ ሰለሞን ታፈሰ (የኦሮሚያው ተቃዋሚ ነኝ ባይ) ደግሞ የተጋባዡን ጎራ ይወክላል።

ሁለት ቀን ሙሉ ስለፌዴራሊዝም ሲደሰኩሩ የሰነበቱት እነ ጌታቸው ረዳ በመድረኩ ማጠናቀቂያ ምሽት የተለመደውን ባህሪያቸውን ገልጠውታል።

ጌታቸው “ፌዴራሊዝሙን እንታደገው” ሲል በዋለበት አፉ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ወስኪ ሲቀዳ አምሽቷል። ይሁን ግድ የለም ‘የግል ሕይወቱ ነው’ እንዳንል÷ የስምንት ሺህ ብር የወር ደመወዝተኛ የመቀሌ ክለቦች ቋሚ ደንበኛ እንዴት ሊሆን ቻለ?  ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል።

እሽ ለዛሬ ‘ከፌዴራሊስቶች መድረክ’ ባገኘው አበል ሊዝናና ወደ ክለብ ወጣ ብለን ራሳችንን እንዋሽለት። ውሎና ምሽቱን በዜና መዋዕል [chronicle] ስንመዘግበው ፌዴ-ስኪ ብለነዋል። [ቀን የፌዴራሊዝም ልሂቅ ነኝ ባይ ማታ የውስኪ ፊት አውራሪ በመሆኑ÷ ፌዴ-ስኪ የሚል ስያሜ አውጥተንለታል]

እናም ጌቾ ሆዬ ዕረቡ ምሽት በሚዝናናበት ክለብ የመቀሌ ወጣቶች [የመረጃ ምንጮቼ እንዳደረሱኝ መረጃ ከሆነ ራሳቸውን ‘ሳልሳይ ዓለም’ ብለው የሰየሙ ማፍያ የከተማው ወጣቶች] ፌዴ-ስኪን ማለቴ ጌታቸው ረዳን “የትግራይን ህዝብ ለውሃ ጥም ዳርጋችሁ እናንተ ውስኪ ትጠጣላችሁ በሚል” በጠረባ ጥለው በውድቅት ለሊት በወንድ ልጅ ቃሪያ ጥፊ ተፈራርቀውበታል ራሳቸውን ለ’ሳልሳዊ ወያኔ’ ያጫሉ ተብለው የተጠበቁ ወጣቶች እንደስያሜቸው ለፌዴ-ስኪው ጌቾ ‘ሳልሳዊ ዓለም’ን በጠረባና ቃሪያ ጥፊ አሳይተውታል።

‘አመል ካልገደለ አይለቅም’ እንዲሉ ጌታቸው ረዳ ነገም የተደበደበበት ክለብ ሄዶ ከመጠጣት አይመለስም ። ድርጅቱ ህወሃት ስለፌኩ ፌዴራሊዝም መድረክ ማዘጋጀት እንደማይሰለቻት መሆኑ ነው። እናም የጌቾ የዕለት ዜና መዋዕል [chronicle] ፌዴ-ስኪ ሆኖ ይቀጥላል ። እስከ መቼ? ካላችሁኝ የዐቢይ አህመድ መንግሥት በሽብር አፋፋሚ ቡድኖች ላይ የሕግ የበላይነትን እስከሚያስከብር ድረስ ÷ አልያም ደግሞ ጌቾ በአረቂ ብዛት ጉበቱን እስከሚተፋ ድረስ ከፌዴ-ስኪ ይሰውረነ!

በሦስተኛው ገፅ የሚደመሩት ሌላኛዎቹ ፌዴ-ስኪዎች ሰለሞን ታፈሰ እና የአየለ ጫሚሶ ምክትል የሆነው ግለሰብ ናቸው እነዚህ ግለሰቦች በተመሳሳይ ከፌኩ የፌዴራሊስት ኃይሎች መድረክ በኋላ ዕረቡ ምሽት አበላቸውን ጨብጠው ለመዝናናት ይወጣሉ። እንደመረጃ ምንጨ ከሆነ ክለብ ውስጥ ሰለሞን ታፈሰ የከጀላትን ሴት የአየለ ጫሚሶ ምክትል ‘ሺህ ዓመት አይኖር’ በሚል የፍትወት ፉከራ አሰምቶ ወደራሱ ሲጠቀልል ÷ ተደፈርኩ ባዮ ሰለሞን ታፈሰ በጠርሙስ አፍንጫውን ይመታዋል።

ተገዶ ለተደፈረ ፌዴራሊዝም ጥብቅና ሊቆሙ የሄዱት ሰዎች በድብድብ አፍንጫ ተሳብረው ተለያይተዋል።

የአየለ ጫሚሶ ምክትል የሆነው ተጎጅ ከሊቀመንበሩ ቀጥሎ ብቸኛው የፓርቲው አባል ነው። ለሴት ገላ የተመኘውን አበሉን በውስኪ ሞቅታ በተፈጠረ ግብግብ ለተሰበረ አፍንጫው መጠገኛ የህክምና ወጪ ለማዋል ተገዷል ። መቼስ እንደፌኩ የፌዴራሊስቶች መድረክ መቀሌ እየተመላለሰ አይታከመው ነገር ውድብ በጀት ያላት አይመስልም ።  ቢኖርም ከጌታቸው ረዳ በስተቀር የሰርክ ቁስለኛን ለማስተናገድ ‘ውድብ’ ፍቃደኛ አይደለችም ። ምክንያቱም የመቀሌው መድረክ የጤና ኢንሹራንስ መድኀን የለውም ። ዓላማው በታሪክ ፊት በአስከፊ ሁኔታ የቆሰለን ተሸናፊ ድርጅት በሿ-ሿ- መድረክ መጠገን ነበር ። ውጤቱን ለየራሳችሁ ህሊና ፍርድ ስጡ ÷ የኔን በአዲስ መስመር ወረድ ብዬ ልስጥ።

በአጭሩ የመቀሌው ፌኩ የፌዴራሊስት ኃይሎች መድረክ ሦስት ግንባር ታይቶበታል።

ቀዳሚው የሙሰኞች ግንባር

ተከታዮ የአኩራፊዎች ግንባር

ሳልሳዊው ደግሞ የፌዴ-ስኪዎች

ግንባር በሚል በሦስት ገፅ ሊታይ ይችላል።

ከዚህ መድረክ አትራፊው ማን እንደሆነ ሳስብበት ብሰነብትም ከውድብ አኳያ ኪሳራው አመዝኖብኛል። የስራ አስፈፃሚ አባሏ መፈንከቱ የሰርክ ዜና ቢሆንም እንኳ የተጋባዥ እንግዳ አፍንጫ የተሰበረበት የፌዴ-ስኪዎች መድረክ መሆኑ ከውድብ አልፎ የመቀሌን ገፅታ የሚያበላሽ መስሎ ታይቶኛል።

የምር ግን ያ-ሁሉ የፕሮፖጋንዳ ድቤ የተመታበት መድረክ የፌዴ-ስኪዎች የፍትወት ፍላጎትን ሳይመልስ መጠናቀቁ አሳዝኝ ነው – ከጌታቸው ረዳ እና ከስሜት ተጋሪዎቹ አኳያ ማለቴ ነው።

በመጨረሻም

ሞክሼዬ ጌታቸው ረዳ እና በሃሳብ ያረጡ የድርጅቱ አንጋፋ አመራሮች የፍላጎታቸው እስረኛ በሆኑበት ሁኔታ አሸናፊ መሆን የማይታሰብ መሆኑን አስረግጨ ልነግራቸው እወዳለሁ። ቀድሞ ነገር ለዚህ ሁሉ አሳፋሪ ሽንፈት የተዳረጉት የፍላጎታቸው እስረኛ በመሆናቸው ነው ። ቀን ቀን የፌዴራሊዝም ልሂቅ ነን ማለት÷ ምሽቱ ሲደራ ደግሞ የውስኪ ፊታውራሪ ሆኖ ክለብ መሰየም የፍላጎት እስረኝነት መገለጫ ነው።

ፌዴ-ስኪዎች በታሪክ ፊት የተሸናፊነታችሁ ምንጭ የገዛ ፍላጎታችሁ እስረኛ በመሆናችሁ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከእስረኝነት ነፃ አውጡ÷ ያኔ ለሃያ ስምንት ዓመት እስረኛ ያደረጋችሁትን የትግራይን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ለመጠየቅ ይገለጥላችኋል!

ኢትዮጵያ ትቅደም

ፌዴ-ስኪዝም ይውደም‼

ጌታቸው ወንድራድ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: federalist meeting, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule